Get Mystery Box with random crypto!

#ደስታ_ባንተ_ይደሰት! በዚህች ምድር ያለ -የሰው ልጅ ሁሉ ለማግኘት የሚጥረው #ደስታ ነው። | Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

#ደስታ_ባንተ_ይደሰት!

በዚህች ምድር ያለ -የሰው ልጅ ሁሉ ለማግኘት የሚጥረው #ደስታ ነው።

ደስታንም ለማግኘት ከፈለግክ፣ እርግጠኛ የምትሆንበት አንድ መንገድ አለ።

እሱም ሀሳብህን መቆጣጠር ነው።

ደስታ ከውጭ ሁኔታ የሚታይ አይደለም።

የሚያምር ልብስ ብትለብስ፣ ያማረ ቤት ቢኖርህ፣ አዲስ መኪና ብትገዛ፣ ቆንጆ ፍቅረኛ ብትኖርህ፣ አቋምህ የተስተካከለ ቢሆን... ውስጥህ ሰላም ያለው ሀሳብ ከሌለ ደስተኛ ልትሆን አትችልም።

ስለዚህ ደስታ የውስጥ ስሜት እንጂ ከላይ የሚታይ አይደለም።

ደስታህን የምታገኘው ሀሳብህን መቆጣጠር ስትችል ነው።

ለሁሉም ነገር ጊዜ እንዳለው ሲገባህ

ትግስት መራራ፣ ፍሬዋ ግን ጣፋጭ እንደሆነ ስታውቅ

ለምትሰራው ስራ ለቤተሰብህ፣ ለጓደኞችህ፣ በዙሪያህ ላሉ ሰዎች ሁሉ ፍቅር ሲኖርህ

አዎንታዊ እና አርቆ አሳቢ ስትሆን

ከውጪህ ይልቅ ውስጥህን በአእምሮ እውቀት፣ በልብ ፍቅር ለማሳመር ስትሻ…

አንተ ብቻ ሳትሆን ደስታም ባንተ ይደሰታል!

#ራስን_መምራት_መጽሐፍ በጠብታ ማር ደራሲ ዴል ካርኒጌ

#2ተኛው ዕትም በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል::


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?