Get Mystery Box with random crypto!

ቃላት እውን ይሆናሉ በሰንበት ትምህርት ቤት ስማር ያገኘሁት ጠቃሚ ትምህርት፡- “ቃል ስጋ ሆነ | Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

ቃላት እውን ይሆናሉ

በሰንበት ትምህርት ቤት ስማር ያገኘሁት ጠቃሚ ትምህርት፡-

“ቃል ስጋ ሆነ በመካከላችንም አደረ፡፡” ዮሐ 1÷14

በእውናዊ ህይወት፣ ቃላት አካላዊ እውን ይሆናሉ፡፡

እያንዳንዱ የኢኮኖሚ መደብ ማንነቱን የሚያሳይበት እና ራሱን የሚገልጥበት ቃላት አሉት፡፡

ሀብታም ሰዎች ሀብታም ቃላትን ይጠቀማሉ፤

የመካከለኛ መደብ ሰዎች የመካከለኛ መደብ ቃላትን ይጠቀማሉ፤

ድሀ ሰዎች ድሀ ቃላትን ይጠቀማሉ፡፡

“የምታስበውን ነገር ታመጣለህ” ይባላል፡፡ በተመሳሳይም የምንናገራቸው እና የምንጠቀማቸው ቃላት እውን እንደሚሆኑ አምናለሁ፡፡

የድሀ ሰዎች የተለመዱ ቃላት “አልችልም፤ መግዛት አልችልም፤ አቅም የለኝም፤ አይሆንልኝም” የሚሉ ናቸው፡፡

ሀብታም ሰዎች እንዲህ ይላሉ፣ “ልገዛው የምችለው እንዴት ነው? አቅም ሊኖረኝ የሚችለው እንዴት ነው?” በአጭሩ፣ ሕይወትህን መቀየር ከፈለግክ፣ አስተሳሰብህን እና የምትናገራቸውን ቃላት ቀይር፡፡

ሀብት የመገንባት ጥበብ መጽሐፍ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል::


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?