Get Mystery Box with random crypto!

#ጁሊያና (በስሙር ድርሰት ተወዳጅ ብራዚላዊት ገፀባህርይ) ጁሊያና ሳቋ ብቻ ሳይሆን ቁጣዋ ሁሉ | Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

#ጁሊያና

(በስሙር ድርሰት ተወዳጅ ብራዚላዊት ገፀባህርይ)

ጁሊያና ሳቋ ብቻ ሳይሆን ቁጣዋ ሁሉ ልዩ ውበት አለው።

ማርቆስ ከእርሷ ለመራቅ ቢሞክርም አልሆነለትም። ገና ሲያያት ልቡ ቀለጠ።

ከዚች ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ከሚዘምሩላት የላቲን ኮከብ፣ የብራዚል ጨረቃ፣ የሳኦ ፓውሎ ፀሐይ መራቅ ኩነኔ መስሎ ታየው። ህሊናው ወደ ፈትለ ልቡ ወደ ጁሊያና ጎን ወግነው ጦርነት ገጥመዋል።

ነፍሱ አብዝታ ተጨነቀች።

የትኛውን ማዳመጥ እንዳለበት ግራ ገብቶታል። ጁሊያናን መሸሽ በአየርላንድ ውስጥ የሕይወት ኬሚስትሪውን ሙሉ በሙሉ እንደሚያዛባው ጠንቅቆ ተረድቷል። ድንገት ወዷታል። ልቡ ፈትለን ሽሮ ጁሊያናን አንግሷል።

ጁሊያናን ሲቀርብ በዓለም ላይ ያለን ሁሉንም ነገር የጨበጠ ይመስለዋል።

#ከስሙር_መጽሐፍ_የተቀነጨበ

#ስሙር
#ሉባር
#ሰርድዮን

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ፡፡


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)

Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?