Get Mystery Box with random crypto!

የእሳትና ድንገተኛ አደጋን ለመከላከል ወደ ሥራ የገቡት ሮቦቶች የኒው ዮርክ ከተማ የእሳትና ድንገ | Techopia Tube

የእሳትና ድንገተኛ አደጋን ለመከላከል ወደ ሥራ የገቡት ሮቦቶች

የኒው ዮርክ ከተማ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ቢሮ ስፖት የተባሉትን የቦስተን ዳይናሚክስ ውጤት የሮቦት ውሾች በአባልነት ማካተቱን አስታወቀ፡፡

ሮቦቶቹ አስቸጋሪ የሆኑ የነፍስ አድን ሥራዎችን በማገዝ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡ በነፍስ አድን ሥራዎች ሂደት ለሰው ልጆች ተደራሽ በማይሆኑ መልክዓ ምድር እና ሁኔታዎች ውስጥ ምስል እና መረጃዎችን በመሰብሰብ ውጤታማ ሥራን ለማከናወን ያግዛሉ፡፡

በተጨማሪም በፍንዳታ እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚፈጠሩ አደገኛ ጋዞች በአየር ውስጥ ያላቸውን መጠን መመዘን እንደሚችሉም ዴይሊ ሜይል አስነብቧል፡፡

እነዚህ እያንዳንዳቸው ሰባ አምስት ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ የሮቦት ውሾች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በሰው ልጅ ቁጥጥር ስር እንደሚሆን ዘገባው አመላክቷል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሲንጋፖር፣ ቻይና እና ሕንድ ሮቦቶችን በሕግ ማስከበር እንዲሁም በነፍስ አድን ሥራዎች ውስጥ ማሳተፍ እየተለመደ መጥቷል፡፡

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!!
━━━━━━━━━━━━━━━
:@techopiatube2
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬ Share ▬▬▬▬▬


EAII