Get Mystery Box with random crypto!

Tebazu Bekele Official

የቴሌግራም ቻናል አርማ tebazushows — Tebazu Bekele Official T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tebazushows — Tebazu Bekele Official
የሰርጥ አድራሻ: @tebazushows
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 910
የሰርጥ መግለጫ

251916091904
251934140013

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-21 00:45:45 Channel photo updated
21:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 23:58:59 አስደሳች ዜና
አላማችን ትውልዱን ከሀሰት አስተምህሮ መታደግና እውነተኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሮትን በማስተማር በየአመቱ GO በሚል መሪ ቃል ትውልዱን ወደ አለም ሁሉ በወንጌል እንዲደርሱ ማሰማራት ነው።
በዚህ አገልግሎት ከእኛ ጋር ለማገልገል ከፈለጉ በዚህ ስልክ ቁጥሮች በመደወል መመዝገብ ይችላሉ!!
+251916091904
+96170286091
ይመዝገቡ!!
በአንድ ነፍስ አንድ ነፍስ!
https://t.me/gotoworld1
https://t.me/gotoworld1
176 viewsTebazu Bekele, edited  20:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 08:20:34 "፤ በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።"
(የያዕቆብ መልእክት 1: 12)
Join Us
@gototheworld1
@gototheworld1
573 viewsedited  05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 20:18:06 "፤ ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፥ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 54: 13)
Join Us
@tebazushows
@tebazushows
517 views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 14:27:42 ኢየሱስ ዳግመኛ ይመጣል? 

መጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ የሚያወራው ስለ ክርስቶስ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ስለማንም ታሪክ ቢያነሳ የሚያመለክተው ስለ ክርስቶስ። ለዛ ነው ኢየሱስ ስናገር መጽሐፍት ሁሉ ስለ እኔ ይናገራሉ ያለው። 

ሙሉ ታሪክ ስለ ክርስቶስ ይናገር እንጂ ታሪኮቹ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ በእግዚአብሔር አምሳያ የተጠፈጠረውን የሰውን ልጅ የማዳን ጉዞ ያመለክታሉ። 

ከዚህ በመቀጠል በኖኅ መርከብ ታሪክ ላይ ስለ ክርስቶስ ምስል የሚናይበት ይሆናል። አጠቃላይ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች የአዲስ ኪዳን ጥላ ናቸው። ሙሉውን ነጸብራቅ የሚናገኘው በአዲስ ኪዳን ውስጥ ነው። 

ክፍል አንድ በሰው ልጅ አመጽ ምክንያት እግዚአብሔር በኖኅ ዘመን እንደተቆጣና በቁጣውም ምክንያት ምን ለማድረግ እንደቆረጠ በጥቅቱ ለማየት ሞክረናል። ለማስታወስ ያኪል 

“አጸያፊነቱም የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው ይሄ ተግባር የእግዚአብሔርን ቁጣ እጅግ ጨመረ። እግዚአብሔርም የሰውን ልጅ በመፍጠሩ በጣም ተጸጸተ።”

  ምክንያቱም የሰው የልቡ ሀሳብ ምኞትም ሁልግዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ ስላየ። ከዛ የተነሳ እግዚአብሔር በልቡም አዘነ። 

እግዚአብሔር የጽድቅ ረሃብተኛ አምላክ ነው። አካሄዱን ከእርሱ ጋር የሚሄድ ሰው ብቻ የእግዚአብሔርን ልብ ያሸንፈዋል። ከእርሱ ጋር የሚሄድ ባይኖር ብቻውን የሚቆም አምላክ ነው። 

በኖኅ ዘመን በዓለም የሚኖር ሰው ሁሉ አመፀኛ ሲሆን 

“እግዚአብሔርም  ኖኅን አለው። አንተ ቤተሰቦችን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ፤ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይቼሃለሁና።”

ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፥ ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ። ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ አጠፉለሁና።ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ።

በአዲስ ኪዳን ላይ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ካደረገው ጋር ታሪኩን ሲናይ በጣም በተለየ መንገድ ነው። 

በኖኅ ዘመን ሰው ሁሉ አመፀኛ ሳለ አመፀኞችን ሁሉ ለማዳን አልሄደም። ይልቅ በጽድቅ የሄደውን ኖኅንና ቤተሰቦቹን ብቻ በራሱ የጽድቅ መንገድ አዳነ። 

 በአዲስ ኪዳን ግን ሙሉ ታሪኩን ሲናጠና ከሰው ልጆች ምንም አይነት የጽድቅን ሕይወት አልፈለገም ምክንያቱም የሰው ልጅ ጽድቅ የመርገም ጨርቅ ስለሆነ። በዛ ምክንያት የዓለም ሁሉ ሕዝብ የሚድንበትን ብቸኛ መንገድ አዘጋጀ እሱም በልጁ በክርስቶስ ብቻ በማመን የሚገኝ የጽድቅ ሕይወት ነው።  

 በእርግጥ በኖኅ ዘመንም ኖኅ ጻድቅ ሆኖ ሳለ የመዳኛ መንገድ እግዚአብሔር ነው ያዘጋጀው እሱም መርከብቱን እንዲሰራ ነገረው። 

ያቺ መርከብ ብቻኛ የመዳኛ መንገድ ነበረች። መርከብቱም የዛሬውን ብቸኛ የመዳኛ መንገድ የሆነውን ክርስቶስን ትውክላለች።

 መርከቢቱ ተሰርታ ሲታልቅ በመኃሉ ላይ አንድ በር ብቻ ነበራት። ኖኅና ቤተሰቦቹ እንዲሁም የተመረጡት እንስሳት የገቡበት። ያቺ በር ወደ መንግስተ ሰማይ መግቢያ በር ክርስቶስ ብቻ መሆኑን ትወክላለች። 

“በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል። ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።”  ዮሐ 10:9 – 10

 “በመጨረሻም ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ገቡ፤ እግዚአብሔርም በስተ ኋላው ዘጋበት።” ዘፍ 7:16

የምህረት ግዜ ገደብ አለው። አንድ ቀን ዛሬ የተከፈተው በር የምዘገባት ግዜ ይመጣል። 

ግዜው ከመቼም ይልቅ የክርስቶስ መምጫው የቀረበበት ግዜ ላይ ነን። ቃሉ ከነገረን ምልክቶች ሁሉም ማለት ይቻለል ፍፃሜውን አግኝቱሃል። አሁን የቀረው የእርሱ መምጣት ብቻ ነው። ለኛ በክርስቶስ ላመነው ይመጣልናል፤ ላላመኑት ደግሞ ይመጣባቸዋል። 

በኖኅ ዘመን የጥፋት ውሃ እስኪመጣ ሰወች ያገቡ ይጋቡ ነበር። የየእለት ተግባራቸውን ያደርጉም ነበር። የመንቂያን ድምጽ የሰማው ኖኅ ግን መርከብቱን ይሰራ ነበር። 

ዛሬም እንደ ኖኅ ዘመን ወንጌል እየተሰበከ ነገር ግን ብዙወች ልባቸውን ከእግዚአብሔር ያራቁበት ግዜ ነው። 

 እንደ ክርስቲያን ከመቸም ግዜ በላይ ሙሹራዋ ባሏን ተዘጋጅታ እንደምትጠብቅ ተዘጋጅተን የሚንጠብቅበት ግዜ አሁን ነው።  የክርስቶ ዳግም ምጻት በእርሱ ያላመኑት ላይ ሊፈርድ እና በእርሱ ያመነውን ደግሞ ሊወስደን ነው።  

የክብር ታስፋችን ኢየሱስ ይመጣል። 

የጌታ ሰላምና ፀጋ ይብዛላቹ።
@tebazushows
@tebazushows
612 viewsedited  11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 16:09:44 ተክሎ ፡ መሄድ ፡ የአንተን ፡ ፍለጋ
ምነኛ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ቢበዛልኝ ፡ ፀጋ
አስከብሬህ ፡ ልለፍ ፡ እንደ ፡ አባቶቼ
ዓለም ፡ እና ፡ ትርፏን ፡ ሁሉን ፡ ንቄ ፡ ትቼ (፪x)

አዝ፦ ክርስትናን ፡ መኖር ፡ ዋጋ ፡ በመክፈል ፡ ነው
ግን ፡ የለብስኩት ፡ ሥጋ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነው
ከጐኔ ፡ በመቆም ፡ ካላበረታኸኝ
ታውቃለህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ (፪x)

ዘወትር ፡ በፀሎት ፡ በፊትህ ፡ ልደፋ
በውስጤ ፡ ያኖርከው ፡ እሳቱ ፡ እንዳይጠፋ
ገና ፡ ላገልግልህ ፡ በኃይል ፡ ተሞልቼ
ጉብዝናዬን ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ (፪x)

አዝ፦ ክርስትናን ፡ መኖር ፡ ዋጋ ፡ በመክፈል ፡ ነው
ግን ፡ የለብስኩት ፡ ሥጋ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነው
ከጐኔ ፡ በመቆም ፡ ካላበረታኸኝ
ታውቃለህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ (፪x)

ባላደራነቴን ፡ ችላ ፡ እንዳልለው
የወንጌልን ፡ ዕንቁ ፡ ለራ ፡ እንዳልጥለው
ታማኝ ፡ አድርገህ ፡ ቆጥረህ ፡ በቤትህ ፡ የሾምከኝ
ከፈተናዎቼ ፡ ፀጋህ ፡ ያሾልከኝ/ያስመልጠኝ (፪x)

ሰርክ ፡ እናይሳነኝ ፡ መንጋህን ፡ በመገብ
በሸክላ ፡ ዕቃ ፡ ውስጥ ፡ የከበረ ፡ መዝገብ
ያስቀመጥክ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እንደ ፡ ኃይልህ ፡ ብዛት
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ሕይወቴን ፡ አግዛት (፪x)

አዝ፦ ክርስትናን ፡ መኖር ፡ ዋጋ ፡ በመክፈል ፡ ነው
ግን ፡ የለብስኩት ፡ ሥጋ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነው
ከጐኔ ፡ በመቆም ፡ ካላበረታኸኝ
ታውቃለህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ (፪x)
467 views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 22:49:49 "፤ አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 15: 9)
@tebazushows
@tebazushows
376 views19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 08:43:50 #ዘመኑን ግዙ
+ Follow

እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ኤፌሶን ሰዎች 5፡15-16

ብዙ ሰዎች የሚሳሳቱትና ከስኬት የሚወድቁት ቀኖቹ ለእነርሱ እንደሚሰራላቸው ባለማስተዋል በማሰብ ነው፡፡ ሰዎች ዘመኑ መልካም እንደሆነ ነገር ዘና ሲሉና በማስተዋል ካልነቁ እግዚአብሄር ወዳየላቸው የክብር ደረጃ መድረስ ያቅታቸዋል፡፡

ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው፡፡ በጥንቃቄ ሳንኖር ቀኖቹ በራሳቸው ዝም ብለው ለእኛ ይሰራሉ ብለን ከጠበቅን አንሳሳታለን፡፡ ቀኖቹ በራሳቸው ለእኛ በጎነት አይሰሩም፡፡

መልካሙ የምስራች ግን እነዚህን ክፉ ቀኖች ለእኛ እንዲሰሩ ማድረግ መቻላችን ነው፡፡ እነዚህን ክፉ ቀኖች መግዛት የሚቻልበትና ለእኛ ስኬት እንዲሰሩ የሚደረግበት መላ አለ፡፡

ክፉ ቀኖች ለእኛ እንዲሰሩ ብሎም እግዚአብሄር ወዳየልን የህይወት አላማ መድረስ የምንችለው በጥበብ ጥንቃቄ ስንመላለስ ነው፡፡

የእግዚአብሄር ቃል በሚሰጠን ጥበብ ከተመላለስን እነዚህን ክፉ ቀኖች ገልብጠን ለእኛ በጎነት እንዲሰሩ ማድረግ እንችላለን፡፡ በሚበልጥ በእግዚአብሄር ጥበብ ከኖርን ክፋታቸው በእኛ ላይ እንዳይሰራ አድርገን ከሁኔታዎች ሁሉ በላይ መኖር እንችላለን፡፡

ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡15

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ
Join ያድርጉ!
@tebazushows
@tebazushows
393 viewsedited  05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 22:53:57 አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ
ክፍል-አንድ(1)
‘በጻድቁና በክፉው መካከል ያለውን ልዩነት ታያላችሁ።’—ሚል. 3:18

መዝሙሮች፦ 127, 101

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

ስለ ራሳችን ይበልጥ ሚዛናዊ የሆነ አመለካከት ለማዳበር ምን ሊረዳን ይችላል?

ሌሎችን በምንይዝበት መንገድ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ምን ሊረዳን ይችላል?

ባሕርያችንን ለማሻሻል ምን ማድረግ እንችላለን?

1, 2. በዛሬው ጊዜ ያሉ የአምላክ ሕዝቦች ምን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል?

በሕክምና መስክ የተሰማሩ በርካታ ባለሙያዎች ተላላፊ በሽታ የያዛቸውን ሰዎች ያክማሉ። እነዚህ ባለሙያዎች ለሕመምተኞቹ እንክብካቤ የሚያደርጉት ሊረዷቸው ስለሚፈልጉ ነው። ይህን ሲያደርጉ ግን በሽታው ወደ እነሱም እንዳይጋባ መጠንቀቅ ያስፈልጋቸዋል። በተመሳሳይም ብዙዎቻችን የምንኖረውና የምንሠራው አምላክ የማይወዳቸውን ባሕርያት ከሚያንጸባርቁ ሰዎች ጋር ነው። በመሆኑም የእነዚህ ሰዎች አመለካከትና ዝንባሌ እንዳይጋባብን መጠንቀቅ ይኖርብናል።

2 በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ከፍተኛ የሥነ ምግባር ውድቀት ይታያል። ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በላከው ሁለተኛ ደብዳቤ ላይ ከአምላክ የራቁ ሰዎች ስለሚያሳዩአቸው ባሕርያት ጠቅሷል፤ ጳውሎስ ወደዚህ ሥርዓት መጨረሻ እየተቃረብን በሄድን መጠን እነዚህ መጥፎ ባሕርያት ይበልጥ እንደሚታዩ ጠቁሟል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5, 13⁠ን አንብብ።) እንደነዚህ ዓይነት ባሕርያት እየተስፋፉ መሄዳቸው በጣም እንደሚረብሸን የታወቀ ነው፤ ያም ሆኖ እንዲህ ያሉት መጥፎ ባሕርያትና ዝንባሌዎች ወደ እኛም ሊጋቡ እንደሚችሉ ማስታወስ ይኖርብናል። (ምሳሌ 13:20) በዚህ ርዕስ ውስጥ፣ በመጨረሻው ዘመን በሚኖሩ ሰዎች ባሕርያትና የአምላክ ሕዝቦች በሚያሳዩአቸው ባሕርያት መካከል ያለውን ልዩነት እንመረምራለን። በተጨማሪም ሰዎች አምላክን እንዲያውቁ በምንረዳበት ጊዜ የእነሱ መጥፎ ባሕርይ እንዳይጋባብን መከላከል የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

3. በ2 ጢሞቴዎስ 3:2-5 ላይ የተዘረዘሩትን ባሕርያት የሚያንጸባርቁት ሁሉም ሰዎች ናቸው?

3 ሐዋርያው ጳውሎስ “በመጨረሻዎቹ ቀናት ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን እንደሚመጣ” ጽፏል። ከዚያም በዚህ ዘመን በሚኖሩ ሰዎች ላይ የሚታዩ 19 መጥፎ ባሕርያትን ዘርዝሯል። እዚህ ላይ የተጠቀሱት ባሕርያት በሮም 1:29-31 ላይ ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ናቸው፤ እርግጥ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በጻፈው ደብዳቤ ላይ በሌሎች የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የማይገኙ ተጨማሪ መጥፎ ባሕርያትን ጠቅሷል። ጳውሎስ የዘረዘራቸውን ባሕርያት የሚያንጸባርቁት ሁሉም ሰዎች አይደሉም። የክርስቲያኖች ባሕርይ ከዚህ በጣም የተለየ ነው።—ሚልክያስ 3:18⁠ን አንብብ። ክፍል ሁለት(2) ይቀጥላል!
ለቻናሉ አዲስ ከሆኑ Join በማድረግ ይቀላቀሉት
@tebazushows
@tebazushows
466 views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 21:02:34 ብዙ ክርስቲያኖች #የማይወዱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
****
1.  #ኀጢአት የሚያደርግ ሁሉ ዐመፅን ያደርጋል፤# ኀጢአትም ዐመፅ ነው። እርሱ #ኀጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፤ በእርሱም #ኀጢአት የለም። በእርሱም የሚኖር #ኀጢአትን አያደርግም፤ #ኀጢአት የሚያደርግ ግን እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም። ልጆች ሆይ፤ ማንም #እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ እርሱ ጻድቅ እንደሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው። 1ዮሐ 3:4-7

2.
#ኀጢአትን የሚያደርግ #ከዲያብሎስ ነው። ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያ አንሥቶ #ኀጢአትን የሚያደርግ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም #የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነው።1ዮሐ 3:8

3. ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ #ኀጢአትን አያደርግም፤ የእርሱ ዘር በውስጡ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደም #ኀጢአትን ሊያደርግ አይችልም።  የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፦ ጽድቅን የማያደርግ፣ ወንድሙንም የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። 1 ዮሐ 3:9-10

4. ከመንፈስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ
#ከሥራም የተለየ እምነት የሞተ ነው።ያዕ 2:26

5.  እንግዲህ በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።ያዕ 2:24

6.ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ
#ኀጢአት እንደማያደርግ ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ እንደሚጠብቀው፣ ክፉውም እንደማይነካው እናውቃለን።እኛ ከእግዚአብሔር እንደሆንን፣ መላው ዓለምም በክፉው ሥር እንደሆነ እናውቃለን።1ዮሐ 5:18-19

7.ሌሎችም.......
@amlikoleyesus
396 viewsedited  18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ