Get Mystery Box with random crypto!

† ቅዱስ ፓትርያርኩ ለቤተክርስቲያንና ለሕዝብ ታምነዋል።† ለ4ኛ ጊዜ የተላከው ሽምግልና አልሠራም | Tariku Abera

† ቅዱስ ፓትርያርኩ ለቤተክርስቲያንና ለሕዝብ ታምነዋል።†

ለ4ኛ ጊዜ የተላከው ሽምግልና አልሠራም ቅዱስነታቸው ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ "እሺ መቅረት እንኳን ባይችሉ ጳጳሳትን ሹመውልን ይሄዱ"? ብለው ሊያታልሏቸው ሞከሩ እሳቸው ግን አይ በእኔ ዘመን እና በዚህ ዕድሜዬ ቤተክርስቲያንን ለሁለት አልከፍልም ። እናንተም ቤተክርስቲያንን አክብሩ ለሚያልፍ ችግር የማያልፍ መከራ ቤተክርስቲያን ላይ አንትከል አሁን ወደ መጣችሁበት ተመለሱ አሏቸው።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ቤተክርስቲያንን ለሁለት እንዲከፍሉ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ሞቴን ያስቀድመው ቤተክርስቲያን ድጋሚ አትከፈልም ብለው በአቋማቸው ጸንተው ቤተክርስቲያንን አስከብረዋል።ሁላችን ልናከብራቸው ይገባል።ኢትዮጵያ ሲገቡም በክብር እንቀበላቸው።

ቅዱስ ፓትርያርኩ በዚህ የአቋም ጽናታቸው ከውስጥ የሚገፏቸውን የብልጽግና ተላላኪ ቅጥረኛ ባንዳዎች አንገት አስደፍተዋል፤ ከውጪም ሆነው እያባበሉ የሚጎትቷቸውን የቤተክርስቲያንና የሃገር ገነጣጣዮችን አንገት አስደፍተው ተስፋ አስቆርጠዋል።ለቤተክርስቲያን ክብር በጽናት መታገል ማለት ይሄ ነው።

ለሌሎችም ሼር አድርጉት

መ/ር ታሪኩ አበራ