Get Mystery Box with random crypto!

★ መንግሥት እጅህን ከቤተክርስቲያን ላይ አንሳ !! ★ † ለፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የክብር | Tariku Abera

★ መንግሥት እጅህን ከቤተክርስቲያን ላይ አንሳ !! ★

† ለፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የክብር አቀባበል እንዳይደረግ መንግሥት ክልከላ እያደረገ ነው።†

★ ትናንት ማክሰኞ ዕለት የቅዱስ ፓትርያርኩ ቢሮ በመንግሥት ደህንነቶች ተከቦ ያመሸ ሲሆን የቅዱስ ፓትርያርኩን ልዩ ፀሐፊና ፕሮቶኮል እንዲሁም አንዳንድ ሠራተኞችን ለማሰር ቀኑን ሙሉ ሲሯሯጡ ውለዋል። ወደ መንበረ ፓትርያርክ ዘለው በድፍረት በመግባት የተወሰኑ ሰዎችን አፍነው የወሰዱ ሲሆን እስከ ሌሊቱ ስድስት ሰዓት ድረስ ግቢው ውስጥ ሲሰልሉ አምሽተዋል።★

★ በዳንኤል ክብረት ፣በ"ቄስ"በላይ መኮንንና በአባ ሕጻን አስተባባሪነት በቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ እየተዶለተ ያለው ከፍተኛ አድማና ሴራ ፓትርያርኩን ከሥልጣናቸው በማፈናቀል ለብልጽግና ፓርቲ የሚላላክ ቅጥረኛ ፓትርያርክ ቤተክርስቲያን ላይ አምጥቶ ለመጫን የሚፈጸም እኩይ ሴራ በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያን አጥብቀን ልንቃወም ይገባል።★

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለሕክምና ወደ ውጭ እንደ ሚወጡ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ዳንኤል ክብረት በግልጽ ፓትርያርኩ ከኢትዮጵያ ከወጡ አይመለሱም ብሎ የሐሰት ሟርት ተናግሮ በኤርፓርት ከፍተኛ መጉላላት እንዲደርስባቸውና የቤተክርስቲያንን ክብር በሚያዋርድ መልኩ በድብቅ ካሜራ የቀረጹትን ወሬ ለፕሮፓጋንዳ ፓትርያርኩ ጽላትና መስቀል ይዘው ሊወጡ ሲሉ ተያዙ ብለው ሕዝብን በፓትርያርኩ ላይ ለማነሳሳት የሐሰት ዜና ቢያሰራጩም ያሰቡት ሴራ ከንቱ ሆኖ ሳይሳካላቸው በመቀርቱ በዚህ የተበሳጩት የመንግሥት ቅጥረኛ ተላላኪዎችና የቤተክርስቲያን የውስጥ ባንዳዎች አሁን ደግሞ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሕክምናቸውን ጨርሰው በሰላም መምጣታቸውን በማስመልከት ሕዝብ የደስታ አቀባበል እንዳያደርግ ከፍተኛ የማጨናገፍ ተግባር እየፈጸሙ ነው።ይህ ሁሉ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ብሔራዊ ክብርና ሉዓላዊነት የሚዳፉር አጸያፊ ተግባር በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያን ለማንም ሳይሆን ለሃይማኖቱ ክብር ሲል ይህንን መንግሥታዊ ነውረኛ ተግባር ጠንክሮ ሊቃወምና ሊታገል ይገባል።

መላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆናችሁ ምዕመናን፣ካህናት፣የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣የቤተክህነት ሥራተኞችና ማኅበራት ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት ጷግሜ 1 ቀን በመሆኑ እንኳን ደህና መጡ ለማለት ሁላችሁም ወጥታችሁ እንድትቀበሉና ለአንድ ቤተክርስቲያንን ለሚወክል መንፈሳዊ አባት የሚደረግ የክብር አቀባበል እንድታደርጉ ከወዲሁ እናሳስባለን።መንግሥትና የውስጥ ባንዳዎች ይህ እንዳይደርግ ስለሆነ እየተሯሯጡ ያሉት እናንተ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችና ምዕመናን ከወዲሁ ነቅታችሁ የአድመኞችን ሴራ በእግዚአብሔር ኃይል ታከሽፋ ዘንድ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

መ/ር ታሪኩ አበራ

ለሌሎችም ሼር በማድረግ ሕዝባችንን እናንቃ በየጉሩፑም ለጥፋት።