Get Mystery Box with random crypto!

Eventually he was dragged through the streets of Diospolis (no | Tariku Abera

Eventually he was dragged through the streets of Diospolis (now Lydda) in Palestine and beheaded. It's said that Diocletian's wife was so impressed by George's resilience that she became a Christian and that she too was executed for her faith.

በመጨረሻም ቅዱስ ጊዮርጊስን በዛሬዋ ልዳ ከተማ ጎዳና ላይ እየጎተቱ ወስደው እስዛው በፍልስጠኤም ምድር አንገቱን ሰየፉት።የንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ሚስት ግን በቅዱስ ጊዮርጊስ የእምነት ጽናት ውስጥዋ እጅግ ተማርኮ ነበርና እርሷዋም በመጨረሻ ክርስቲያን ሆነች። ስለ ክርስትናዋም ብዙ መልካም ተግባራትን ትፈጽም ነበር።

ወገኖቼ በጣም እናስተውል ሰው ወንጌል ሲገባው ቅዱሳንን ያከብራል፣ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዋጋ ከፍለው በሰማዕትነት ያለፉ የእምነት ጀግኖችን እያሰበ ሕይወታቸውን አብነት አድርጎ ይጓዛል፣ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ «የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የእምነታቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሏቸው ያለው።»ዕብ 13፥7
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰማዕታትን የተጋድሎ ሕይወትና ወንጌልን በሕይወታቸው እንዴት እንደተረጎሙ ትውልዱ በየጊዜው እያሰበ እንዲኖር ቀናት በቅዱሳን ስም ሰይማ ተጋድሎና ታሪካቸውን ስታስተምር መኖሯ ከትክክል በላይ ትክክል ነው። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እግዚአብሔር ሁሌም በክብር ይጠብቅሽ። ዛሬ አንዳንድ ሰዎች ወንጌል ገብቶናል፣ እውነት በርቶልናል እያሉ ቅዱሳንን ሲያቃልሉና ሰማዕታትን ሲያብጠለጥሉ ይውላሉ፤ ነገርግን ስለ ክርስትና አንዲትም መከራ በሕይወታቸው አልተቀበሉም። በግል በሥጋ ድካማቸው የሚመጣባቸውን መከራ ስለ እምነታቸው እንደተቀበሉት አድርገው ይጠመዝዙታል ይሄ በጣም ስህተት ነው።እውነት ወንጌል የበራላችሁ ከሆነ እስቲ እስላም መስኪድ ሄዳችሁ ስበኩ፣እስቲ ጠንቋይ ቤት ያሉትን የማምለኪያ መሰዊያዎች ሄዳችሁ አፍርሱ፣ፌስቡክ ላይ ተጥደው እየዋሉ ቅዱሳንና ሰማዕታትን የሚነቅፉ፣ የቤተክርስቲያንን ክብር ለማዋረድ የሚወራጩ ሰዎች መንፈሰ እግዚአብሔር የተለያቸው የአጋንንት መንፈስ በልባቸው ሰልጥኖ ምላሳቸውን የተከራያቸው የጥፋት ልጆች ናቸው እግዚአብሔር ልባቸውን ይፈውስ።

ወገኖቼ የክርስቶስ ፍቅር ሲገባን እንደነ ቅዱስ ጊዮርጊስ እሳትና ስለቱን ሳንፈራ ስለ ወንጌል እንመሰክራለን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የአማልክት አምላክ፣የጌቶች ጌታ ፣የነገሥታት ንጉሥ መሆኑን ሳንፈራና ሳናፍር እንመሰክራለን።የሰማዕታት ደም የእምነት ዘር ነው ጥቂት ፈሶ ብዙ ምርኮን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ያስገባል።

የሰማዕቱ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

" ...ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የፃድቅን ዋጋ ይወስዳል ማንም ከነዚህ ታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀ መዛሙርቱ ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም ..." (ማቴ.10፥41)

እባካችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉት በየጉሩፑም ለጥፋት

ለበረከት ሁኑ።

መ/ር ታሪኩ አበራ