Get Mystery Box with random crypto!

የጃፓን ወጣቶች ከወላጆቻቸው ያነሰ የአልኮል መጠጥ ተጠቃሚ ሆነዋል፤ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ጃፓን ወ | ጣፋጭ ህይወት/Tafach hiwot

የጃፓን ወጣቶች ከወላጆቻቸው ያነሰ የአልኮል መጠጥ ተጠቃሚ ሆነዋል፤ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ጃፓን ወጣቶቿ እንዲጠጡ ጠይቃለች

በጃፓን ወጣቱ ትውልድ ከወላጆቹ ያነሰ አልኮል ይጠጣል፤ ይህም ደግሞ መንግስት ማግኘት ያለበትን ገቢ እያስቀረና እየጎዳ መሆኑ ተነግሯል።የጃፓን የብሔራዊ የታክስ ኤጀንሲ ይህንን አካሄድ ለመቀልበስ አዳዲስ አሰራር ጀምሯል።

ቪቫ በተሰኘው አዲስ ዘመቻ መጠጥን የበለጠ ማራኪ ለማድረግ እና ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ እቅድ ተነድፏል። እድሜያቸው ከ20 እስከ 39 ዓመት ያሉ ሰዎች ሾቹ ፣ ውስኪ ፣ ቢራ ወይም ወይን ያሉ መጠጥን ከእኩዮቻቸው ጋር እንዲጠጡ የሚያስችል እቅድ ተነድፏል።

የታክስ ኤጀንሲ በቅርብ ያዋጣው አኃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በ2020 ጥቅም ላይ ያዋለው አልኮል እ. ኤ.አ በ1995 ከነበረው ያነሳ ነው።ከአልኮል መንግስት የሚያገኘው የግብር ገቢም ባለፉት ዓመታት ቀንሷል። እንደ ጃፓን ታይምስ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. በ1980 ከጠቅላላ ገቢው 5 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2020 ግን ወደ 1.7 በመቶ ቀንሷል።

Via ዳጉ ጆርናል