Get Mystery Box with random crypto!

የሴቶችኝ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት ይገባል አሉ የስልጤ ዞን ሴቶ | ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION

የሴቶችኝ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት ይገባል አሉ የስልጤ ዞን ሴቶችና ህፃናት መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ጀሚላ ሁሴን!

ሀላፊዋ ይህን ያሉት በሴቶች ተጠቃሚነትና የስርአ-ፆታ የቴክኒክ ኮሚቴ የ2015 በጀት አመት የግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም በገመገሙበት ወቅት ነው።

ጥር 02/05/2015 ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን፦ወራቤ

ለመድረኩ መወያያ የሚሆን ሰነድ በየተቋሙ የተገኙ ቴክኒክ ኮሚቴዎች በሴቶችና ህፃናት ተጠቃሚነትና ስርአተ ፆታ ዙሪያ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ሴቶችን በሁለንተናዊ የልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በገጠርና በከተማ በሁሉም ዘርፍ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የሚስታወሉ ደካማ ጎኖችን ማለትም ከስደት ተመላሾችን ወደ ስራ እንዲገቡ ከማድረግ ጋር ሰፊ ርብርብ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

ሴቶች ከንቃተ ህግ፣ከስብዕና ግንባታ፣ከአገልግሎት አሰጣጥ መሰል ስራዎች ላይ የተጠቃሚና የተሳታፊዎች ቁጥር እያደገና በዘርፉም ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሴቶች በኢኮኖሚው ዘርፍ ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት ተግባራዊ ባደረገው የሌማት ትሩፋት ላይ የተሻሻሉ የወተትና የስጋ እንዲሁም እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን የሚያራቡ በሌሎችም የግብርናው መስኮች ላይ ተደራጅተው በመስራት ውጤታማ መሆን እንዲችሉ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

ዩቲዩብ https://youtube.com/channel/UCWabC0m4vTgkxscUVkFKBwQ

ፌስቡክ https://m.facebook.com/siltezone/?_rdr

ቴሌግራም https://t.me/szcommunication2012