Get Mystery Box with random crypto!

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመስጠት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ ነው - የወራቤ ከ | ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመስጠት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ ነው - የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመስጠት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት አስታውቋል።

ከቀጣዩ ማክሰኞ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ለሚሰጠው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ፈተናውን በጥብቅ ዲሲፕሊን ለመምራት እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ለማስቻልም ሂደቱን ለማስፈጸም የተዋቀረው ግብረሃይል በዛሬው ዕለት መክሯል።

የቅድመ ዝግጅት ስራው አንዱ አካል የሆነው የሱፐርቫይዘሮች፣ፈታኝ መምህራን፣የፀጥታ ሃይሎች እና የሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በነገው ዕለት እንደሚከሄድ ተጠቁሟል።

መረጃው የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ኮምኒኬሽን ነው!