Get Mystery Box with random crypto!

Sumeya sultan

የቴሌግራም ቻናል አርማ sumeyasu — Sumeya sultan S
የቴሌግራም ቻናል አርማ sumeyasu — Sumeya sultan
የሰርጥ አድራሻ: @sumeyasu
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.03K
የሰርጥ መግለጫ

ነጻ ሃሳብ! ነጻ ግጥም!!
ሃሳብ አስተያየት በ @Sumeyaabot አድርሱኝ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-08-02 18:28:28 ስደት በኔ እይታ
(ሱመያ ሱልጣን)
ምን መሰለሽ?!ስደት 1 ሰጥቶሽ ሁለት የምትነጠቂበት ቁማር ነው። ያስፈልገኛል ብለሽ የምታስቢውን ሊሰጥሽ ቦታ የማትሰጪያቸውን ነገሮች ይሰርቅሻል። በቀላል አማርኛ "በእጅ ያለ ወርቅ" የሆኑብሽን ነገሮች ወርቅ የመሰልሽን መዳብ ሊሰጥሽ መሰላል ያደርግብሻል። ሃገርሽን አልቅሰሽ የተለየሽበትን ገንዘብ ይሰጥሽና ስታለቅሺ አብረውሽ መሬት እየቧጨሩ ያለቀሱ ቤተሰቦችሽን ጠረን ለ አመታት ይነጥቅሻል። የተሻለ ምግብ ይሰጥሽና አብሮሽ የሚበላን ይነፍግሻል። ሲያምሽ ፣ስትወልጂ፣ ሲከፋሽ የምታወሪውን ሰው ከጎንሽ ስታጪ በውስጥሽ ማፈኑን መፍትሄ ታደርጊዋለሽ። ያዳፈንሽው ህመምሽን ግን እንዳልቀበርሽው የምታውቂው አንድ ቀን ምንም የማያስከፉ ቃላቶች የ አይንሽ ሽፋሽፍቶችን እንባሽ ሲያጥባቸው ነው ወይም የሆነ ሰው ለቅሶ ላይ እሪሪ ስትዪ ነው። ገንዘብ ሊሰጥሽ እንደ ቀልድ ከ እድሜሽ ላይ 5 -10 አመት ላጥ ያደርግብሻል። ልጅነትሽን እንደዋዛ ፤ወጣትነትሽን እንደ ተራ ይቀራመትሻል። ሊያውም ቤተሰብሽን ሳታዪ እኮ ነው። በዚህ መሃል ደግሞ ከቤተሰብሽ ወይም ጎረቤትሽ እጅግ ላንቺ የቀረበውን በሞት አትጪው!!! በቃ አታምኚም። ይምታታብሻል። ሁሉም ነገር ቢሞላልሽ እንኳን፣ ከ ትላንት በ 3 እርምጃ የቀደመ ቦታ ላይ ያለሽ ቢሆን እንኳ ጨክነሽ እንዳትገቢ የሆነ ነገር አሳስሮ ያስቀምጥሻል። ስደት ላይ ሃገርሽ ማድረግ ያልቻልሻቸውን ነገር ለማድረግ ቀመሩ (ያንቺ የግል ፍላጎት+ጠንክሮ መስራት= ስኬትሽ) ይህንን ቀመር ሲነግሩሽ ግን የሚደብቁሽ አንድ ሌላ የቀመሩ አካል(የግል ፍላጎት+ጠንክሮ መስራት=ሲኬትሽ×0 ደስታ ወይም ጊዜያዊ ደስታ)መሆኑን ነው። ምን ያስጠላል መሰለሽ?! ስደት የሚሰጥሽን እንጂ የሚነጥቅሽን እንዲሰማሽ አያደርግም። ስለዚህ ህመምሽ ስር እየሰደደ እንደሆነ አይታወቅሽም ምክንያቱም በሚሰጥሽ ነገር አፍሽን ያዘጋሻል። ደግሞ ማንም አይረዳሽም። ማስረዳትም ይደክምሻል።
ይህ ከተረዳሁት ነው የናንተን አካፍሉኝ።
@sumeyasu
3.2K views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-31 15:55:14 ጥሩ ምልከታ@https://t.me/Assefaboku
2.6K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-31 15:53:38 የትዕግስት ፍሬዎች
በበረከቶች የተከበበው የሠው ልጅ “ትዕግስት” ማድረግን አማራጭ ስላጣ የሚተገብረው ልማድ አድርጎት እንመለከታለን። መታገስ በትንንሽ ድሎቼ ላይ ምን ያህል ዋጋ እንዳላቸው አስተውያለው; ከማያልቀው የሠው ልጅ ፍላጎቶች አንጻር ትዕግስት በማድረጉ የሚረጋገጡት ድሎች ሳይፈልግ ለትዕግስት ዋጋ እንዲሰጥ ያስገድደዋል። የዓለም በፍጥነት መጓዝ ታጋሽ ላለመሆናችን አስተዋጽኦ ቢያደርግም በዕለት ተዕለት እንቅሳሴያችን ላይ መታገስ ነገ ላይ በሚመዘገቡት ስኬቶች አሻራችን ጎልተው እንዲታዩ ሠፊ እድል ይቸራል። ይህን አስደሳች የህይወት ትዕይንት በፈካ መስኮት ለመመልከት መጀመሪያ ከተቀመጥንባት ጠባብ ክፍል ውስጥ ብርሃኑን ከመፈለግ ይልቅ እኛው ብርሃን ሆነን አቅጣጫዎችን መመልከቱ የተሻለ ነው፤ ላለፉት 3 ዓመታት ከብዙ ስኬታማ ሰዋች ጋር ተቀምጦ የመወያየቱ እድል ገጥሞኝ ብዙ ተምሬኧለው። ሚገርመው ሁሉም ስኬታማ የሆኑት ታጋሽ ስለነበሩ ብቻ ነው;
2.5K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-29 10:56:18 ርዕስ አልባ
"ጎሽ ጎሽ" እንጂ ፣"ተው ተዉ!" የሚል
የሃገር ሸምጋይ፥ በሃገር ጠፍቶ፣
"እርዳኝ!" ብሎ አለ፤ ወደ ፈጣሪው፣
በወንድሙ ላይ፣ ጦር ሊሰብቅ ወጥቶ።
የጉድ ሃገር ወግ ፣መቋጫ የጠፋው፣
ህዝብ አጨብጭቦ ፣እህቱን ሊገድል፤
መርቆ ላከው።
@sumeyasu
2.5K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-20 10:04:58 እንኳን ለ ኢድ አል አድሃ በአል በሰላም አደረሳችሁ ። ኢዱኩም ሙባረክ!!! ተቀበለላሁ ሚና ወ ሚንኩም!!
2.7K views07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-16 13:11:22 ብታምሪም አታምሪም
(ሱመያ ሱልጣን)
ያምራል ያልኩት ጥርስሽ፥
   "አወይ አደራደር"እያልኩ ያደነቅኩት፣
የ አይንሽን መዋብ ፣በ ጨረቃ ምስል፣
         ተክቼ የካንኩት፤
ዛሬ አስጠልቶኛል።
እንደውም ልንገርሽ፥
ሰልካካ አፍንጫሽ ፣
የሚያበራው ቆዳሽ፣
አድናቂሽን ሁሉ፥ ዘርሮ የጣለው፥
       ያ አበባ መልክሽ፤
ለ አይኔ ቀፎኛል።
እንደውም ልድገምሽ፣
ትላንት ውበትሽን፥ ተገርሞ ያደነቀው፣
ጸጸት ያደከመው ፣ምስኪኑ ምላሴ፣
በሙሉ አይኔ ማየት ፥መዳፈር ሚመስለው፥
            ያከበረሽ ነፍሴ፣
አዘነብሽና ፤አጣላኝ ከራሴ።
ለምን ይመስልሻል?

ቆይ ቆይ መች ጨረስኩኝ?

እንደውም እንደውም..
ባንቺ ስነሆልል፥ ካይኔ ያላደረስኳት፣
አፍንጫ ጎራዳ ፣ባለ ወዝ አልባ ፊት፣
አሁን ላይ ሳያት ግን ፤ትበልጥሽ ነበረ።
ተሰትራለቻ!!

ያከበርኩት ክብርሽ፥ ራስሽ ገፈፍሽው፣
ሱሪሽን አጥልቀሽ ፤ሻርፕሽን ገፋሽው።
ልክ እንደ ከተማው፣ እንደነዛ መንጋ፣
እንደነ አይን ክብሩ፣ እይታን ፍለጋ፤
ዝም ስንላቸው፥ ያደነቅን መስሎሽ፣
ለይበልጥ እይታ፣ ለዐእላፍ አድናቆት፤
ከሂጃቡ መገፋት፣ ከ ሱሪው መወጠር፣
                         እራሳቸውን ሆንሽ።
እራሱን ከተማው፣ እራሱን ማስጠላት፣
                               አንቺ ላይ ታይቶኛል፤
ልቤ የሰጠሽን፣ ያንን ውድ ቦታ ፤ራስሽ ሰብረሻል።
ከተማ ለመምሰል፣ አለምሽን ስትተይ፣
                               ማስጠላትን ተኳልሽ፤
በ "አጌጥኩ" እሳቤ ፣መከበርን ገፋሽ።
ግን እኮ ታምሪያለሽ!!
አይን ትስቢያለሽ
ግን ደግሞ..
  ጌታሽ ያልወደደው፣ አለባበስ ስትለብሽ፣
  "ለኔማ አትሆኚም!"፣ብዬ ነው ያራቅኩሽ፤
  ለፈጠረሽ ካልሆንሽ ፣ለጌታሽ ካልታዘዝሽ፣
  በፍጹም ለባሪያው፣ አትሆኝም ልንገርሽ፤
ለዛ ነው የተውኩሽ፤ እንጂማ ታምሪያለሽ።
ግን ደግሞ አታምሪም።
@sumeyasu
3.1K views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-12 19:28:45 የኛም ነገ ነው
(ሱመያ ሱልጣን)
...መቼ ነው "አደግን እንዴ?" ያላቹት?በ አጠገባችሁ አብሯችሁ መድረሳ ሲሄድ ወይንም ትምህርት ቤት ወይንም አብሯችሁ ሲጫወት የምታውቁት ሰው ሲያገባ?ወይንስ ሲሞት?
"አደግን መሰለኝ ሱም በአጠገባችን የምናውቀውን ሰው መርዶ መስማት ጀመርን" ይሄንን እህቴ ስትነግረኝ የ 11ኛ ክፍል ተማሪ እያለን እኩያችን ሞቶ ከ ለቅሶ እየመጣን ነበር። ያኔ የ እኩያችን ሞት ልባችን ላይ ከ አለት የጠጠረ ህመም ነበረው። አሁን ሞት ለመድን እንዴ? ሰው ቀብረን ስንመለስ "ያንቺ መዳረሻማ ይሄ አይደለም" እያለ ለነፍሳችን ሹክ የሚላት መንፈስ አለ እንዴ?ነገር አለሙን ረስተን ድጋሚ ከክፋታችን እና ከ ኩነኔያችን ጋር የሚያወዳጀን?? "እከሌ እኮ ሞተ/ች" ስንባል "ወይኔ ትላንት አይቼው እኮ..." እያልን ትላንት ያየንበትን ሁኔታና ምን ያህል ቅርበት እንደነበራችሁ አሊያም አንድ ጊዜ ብሏችሁ የሚያውቀውን ነገር ለመርዶ ነጋሪው ለመንገር ቃላቶች ከምላሳችሁ አልተደነቃቀፉም?? "ከ ታላቄ/ታናሼ ጋር እኮ በ 1 አመት ቢበላለጡ ነው።" ብላችሁ በጊዜ መቀጨቱ አልነዘራችሁም? ገና አፈር ሳይገባ የሬሳውን ክፉነት ባሳለፋችሁት ጥሩ ነገር አልተካችሁም?? ሳይሞት እንደዛ መሆንን ለምን ከበደን?? እስቲ እንመን ዙሪያችን ለሚፈጠሩት ነገሮች ተጠያቂ እኛ ነን እንበል።የሆነ ቦታ ህዝብ ተጨፈጨፈ ሲባል "ውይ ሰው እንዴት ከፋ?ሃገራችን ተበላሸች" ምናምን አንበል። የኔ ልጅ ነው ያደረገው እንበል። ቤታችን እንደ ቀልድ የምናወራው ነገር ነው እኮ አድጎ ልጆቻችንን አሸባሪ የሚያደርጋቸው።"ሙስሊሞች እኮ ሰው ከገደሉ ይፀድቃሉ"ብላችሁ የምታሳድጉት የሌላ እምነት ተከታይ ልጃችሁ ነገ "ሙስሊም በአጠገቤ አይለፍ"ሲል ሃይማኖቱን እንደጠቀመ ያስባል። ግን እንደ ወላጅ ልጅ ይሄንን ንግግር ሲናገር እንዲህ  "ጎረቤትህ እማማ ኸዲጃ ፅድቅ ጠልተው ነው ያልገደሉህ?"ብላችሁ ብትመልሱ ልጁ ነገ ሰው ሲሞት " ክርስቲያን ሞተ፣ሙስሊም ሞተ"ሳይሆን "ሰው ሞተ ብሎ አፋር ለሞተ ወንድሙ አዲስ አበባ ሃዘን ይቀመጥ ነበር። " "ክርስቲያኖች እኮ እንደዚህ ናቸው" ብላችሁ አብራችሁ ክፉ ደግ እንዳላሳለፋችሁ በቃላት የምትዘሩት ጥላቻ ነገ ሲያድግ ሰው መሆንን አፈር ይከታል። ሁላችንም አጥፍተናል።ጌታችንን በ አፋችን እያቆለጳጰስን በ ስራችን እናስቆጣዋለን።ሰደቃ(ምፅዋት) ስንሰጥ ወይም ለሰው በጎ ስንውል በጭንቅላታችን ከዛ ሰው የምናገኘውን ምስጋና ሂሳብ እንሰራለን።እስቲ ልባችንን እናንፃ ተውበት(ንሰሃ)እናድርግ። ጌታዬ እኮ እንኳን እርሱን ብቻ አምኜ ቀርቶ የካደውንም ሰው ፀሎት ይሰማል።እስቲ ማረን እንበለው። እያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሰው ቢነግረን "እረ በፍጹም" ብለን የምንምልበትን ክፋት ተሸክመናልና እናጥራው ።በዚህ ሁኔታችን ጌታችንን ተገናኝተን ከከሳሪዎች አንሁን።
@sumeyasu
4.7K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-22 20:50:58 "ሱም አሁን ያንቺ ባል ምን አደረገ? ያው የ ጫቱን ነገር አምነሽ መቀበል ነው። በዛ ላይ ደግሞ እንደውም እቤት መቃሙ ጥሩ ነው እኮ። የ ሰላቱንም ጉዳይ እንደሆነ እኛም አንቺም እንመክረዋለን። እንደው ያንቺ እኮ ይሄ ብቻ ነው ። ያቺ እላይ ሰፈር የሆነ ጊዜ በ ቀውጢው ያገባችው ሲትራ እንኳ ባልየው ብታዪ ይመታታል ሁላ እሷ እንኳ እየኖረች ነው። ሄለንም እንደዛው..." ምናምን እያሉ የየቤቱን የ ትዳር ገመና እኔን ለማባበል ወይም ለማጽናናት ጓደኞቼ ያዩ የሰሙትን ይለፍፉልኛል። ይሄን ጠልቼ አይደል እንዴ እኔስ "ምክንያት?" ስባል ይፋ በወጣው ጉዴ ብቻ ሌሎች ህመሞቼን የሸሸግኩት?!
....
ውሳኔዬ ልጆቼን ከ አባታቸው ጋር እንዳይኖሩ ቢያግድም፣ እናት እና አባቴን"የፈታችው ልጅ ወላጆች ቢያስብልም"፤ ባለቤቴን "ሚስቱ የተወችው "ቢያሰኝም እኔን "ፈት" የሚል ቅጽል ቢያሰጥም፤ በኔና በሱ መልስ የሌለው ጭቅጭቅ የብላቴናዎቼን  አእምሮ ላለመበረዝ ስል ወሰንኩ። "ለ ልጆቻችሁ ስትሉ እንኳን..." ለሚለኝ መልሴ" ቢያንስ አባታቸው ጥሩ አባት እንጂ ባል መሆን እንዳልቻለበት አይተው እንዲያድጉ አልፈለግኩም።" ነዉ ። "እንዲህ አይደረግም!" "እንዲህ አድርጉ!" ብሎ በ አባትኛ በገሰጸበት አፉ ሚስቱን ሲሰድብ፤ እነሱን ለማቀፍ የሚዘረጋውን እጁ እኔ ላይ ታጥፎ ሲማታ እንዲያዩት ስለማልፈልግ ለልጆቼ ስል ነው የተፋታሁት። ቀላል አልነበረም። አሁን ልጆቼ የ 10 እና የ 7አመት ከ 6 ወር እድሜ ላይ ናቸው ከሱ ጋር ከ ከተለያየን አመታት አልፈውናል። ጎምዛዛ ቀናትን በሰላሜ እና በልጆቼ ደስታ ረትቼዋለሁ። ግን ቀላል አልነበረም።አሁን ስለ ትዳር ሲነሳ የመከሩኝ ሰዎች ሁሉ "ጥሩ አደረግሽ ከማይሆን ትዳር መለያየቱ እጅግ የተሻለ ነው። የሰው አፍ ፣ የ ኢኮኖሚ ጥገኝነቱ፣የልጆቼ ጥያቄ እነዚህ ያስጨንቃል እንጂ አንዳንድ ትዳርማ ብንንን ብለሽ ጥፊ ያስብላል እኮ።በርግጥ ጥሩ ትዳር አይጠፋም።" ይሉኛል። ምክሬን ለሚፈልጉ አሁንም ቢሆን የተሳካ ትዳር የለም እና ልዩነትን አምኖ መቀበል እና ለማስተካከል መሞከሩ ይበጃል። ፍቺን ለሴት ልጅ በተለይ ለ ወላድ አልመክርም። ያለፍኩት ጉዞ ሲወራ እንዳጠረው ሳይሆን በርግጥም ከሰው ምላስ በሚሰነዘሩ መልካም ያልሆኑ ቃላቶች ሥሰበር፣ ቤተሰቦቼ ቤት ተመልሶ ላለመግባት ተከራይቼ ለመኖር በ ኢኮኖሚ መንገዳገድ፣ የተደበልኩትን መርሳት አለመቻል፣ "ባባ ጋር መች ነው የምንሄደው?" ከሚል የልጆች ጥያቄ ጋር የነበረውን ጉዞ ለማንም አልመኝም። ግን ትዳሩ ላይ ስምምነት ከሌለ ለመለያየት ልጆቻችሁን ምክንያት እንዳታደርጉ። "መጣሁላት ደግሞ ልትጨቀጭቀኝ ነው" የሚል መሰላቸት ከ አባታቸው ፊት ከሚያነቡ መወሰንሽ መስዋእትነትሽ ነው።።።።።
"ደግሞ ዛሬ ምን ሊለኝ ይሆን ?በምን ልመታ ይሆን?"የሚል ስጋት ፊትሽ ላይ ከሚያዩ እመኚኝ ጨክኖ መወሰኑ ይሻላል።እና ወሰንኩ።።።።።
ለልጆቼ ብዬ በታመመ እና መዳን በማይችል ትዳር ውስጥ ከምሞት ለልጆቼ ስል ተፋታሁ።።።
@sumeyasu
3.3K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-19 10:27:40 ..."ትዳር እኮ ብዙ ተችሎ ነው የኔ ልጅ እኔ እና አባትሽ ስንቴ ተጋጭተን ስንቴ እርቅ አውርደን ነው። ትዳር ላይ አጠፋሽም አለማሽም ባልሽ" ተሳስተሻል!" ካለሽ "ይቅር በለኝ" ማለት የሚስትነት ግዴታሽ ነው" እናቴ ንግግር ውስጥ ህመሜ ሽው ሲል ታየኝ። ያልተናገርኩት ግን የኖርኩት ህመሜ አገረሸብኝ።ግን አሁንም አልናገርም። የ 2 ልጆቼ አባት ነው። መልካሙን እንጂ ጉድፉን ቤተሰቦቼ ቤት አውርቼ አላውቅም። ለምንስ አወራለሁ?ቢጠሉትስ?ለ ልጆቼ ስለሱ መጥፎ ቢያወሩስ?ጥላቻም እኮ ይጋባል።ልጆቼ አባታቸውን ጠልተው እንዲያድጉ አልፈልግም። በኔ እድል እነሱ ስለ አባት ሲነሳ እንዲነዝራቸው ወይም እንዲሸማቀቁ አልፈልግም።ስንለያይም በጥሩ መንፈስ እንዲሆን ነው ቤተሰቦቻችን ፊት ብዙ እንከኑን የማላወራው። እኔ የታመምኩትን ለምን ለ ልጆቼስ አስተላልፋለሁ? ስለዚህ በደሌን ለብቻዬ እንድታመም እና ብቻዬን እንድሽር "አፋቱኝ!"አልኩ። "ሰላቱን በ ስርዓት አይሰግድም። ከሰገደም ቤት ውስጥ ነው የሚሰግደው። እሱንም በሚቅመው ጫት ተጠምዶ በሚተርፈው ሰአቱ ነው።ለ አላህ ያልሆነ ለኔ አይሆንም።"ይህን ነው ስለ ፍቺ ጥያቄዬ መልስ የሰጠሁት። ከትዳሬ የመጀመርያ ቀን የተጀመረው ይሄን ባህሪ ከዛሬ ነገ ይለወጣል በሚል ብኩን ተስፋዬ በብዙ ጥበብ ላስተምረው ብታገልም " ድሮም ሴቶች ትንሽ ስታውቁ.."አለ። የ 4 እና 1አመት ከ6 ወር ልጅ አሉን። "ለነሱ ስንል እንስማማ"ይለኛል። ለቤተሰቦቼ የነገርኩት ምክንያት ብቻ መሰለው እንዴ የኔ ምክንያት? ወይስ ደጋግሜ ሳወራው ያ ብቻ ነው በደሌ ብሎ አሰበ?
ይቀጥላል
@sumeyasu
2.9K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-17 12:22:27 ለምን ባሌን ፈታሁ?
ሱመያ ሱልጣን
...ፊት ለ ፊቴ ሲቆም ምን እንዳስደነገጠኝ አላውቅም። የሆነ ስሜት ርብሽ አደረገኝ። "ይቅርታ አድርጊልኝ!"ይለኛል። ቃሉን ሲጠራው ቁስሌ ላይ ሚጥሚጣ እንደነሰነሰ አይረዳም። ለቃሉ አርፍዷል። እሱ ይሄን ቃል እስኪለው እኔ ስንት ለሊት አለቀስኩ?እሱ 4 ፊደል ለመጥራት እኔ ስንቴ ታመምኩ?ተግባሩ ከጎዳኝ በላይ" ልተወው?ሰው ምን ይለኛል? ልጆቼስ? ቤተሰቤስ ?እድሜዬስ?ልጅነቴስ?" የሚል የ ሃሳብ ትርምስ ጭንቅላቴን ያተራመሰው ይበልጥ ነበር ።" ይቅርታ!"ሲለኝ አብረን በኖርንበት ሰአት በሆነ ባልሆነው  ግጭት ሲፈጠር ጀርባዬ ላይ በሚያርፈው የቦክስ ውርጅብኝ የሚፈታው ነገር ከ ፊቴ ድቅን አለብኝ። አብረን ስራ ውለን ገብተን ማታ ተጨናንቄ በምሰራው ምግብ  ያልተገባ አስተያየት ሲሰጠኝ የሚነደውን አንጀቴን ትዝ አስባለኝ። ይቅርታው ሊያመጣ ከሚችለው ሰላም በላይ የረሳሁትን ህመም አስታውሶ ድጋሚ አደማኝ።የመቻል አቅሙ የከዳኝ ፈልጌው አልነበረም ።በቃ ራሱ ነው እየወጋ ለዚህ ያበቃኝ። ግን ልቻል ብል ይሆን ነበር?5 አመት ሙሉ መመታት? አብረን ስራ እየዋልን ገብተን ብቻዬን ሁለት ልጆቼ ጋር እና የሚበላ ለማዘጋጀት ሲንጎዳጎድ መልኬን በማጣቴ መሰደብ ይቻላል? እንዴት አላማ ከሌላቸው እንደ አብዛኛው የ ከተማ ሴት ጋር በ አንድ ሚዛን አስቀምጦ በመኳኳል የተጨማለቀ እነሱነትን ቤቴን ብዬ የተጎሳቆልኩትን እኔን ያወዳድራል?
"ልጆቻችንን አብረን እናሳድግ" ብሎ ሽማግሌ ሰብስቦ ቤተሰብ ጋር ላከ።
"ተይ እንጂ የኔ ልጅ ዛሬ ገና ቢያስቀይምሽ" አለያዩኝ" ይባላል እንዴ?ተይ ደግ አይደለም ለኛም ክብር አስቢ እንጂ እንዲያ በ ሰፈሩ ድል ያለ ድግስ ደግሰን ድረንሽ አሁን ተፋታች ቢሉ ምን ይባላል" አባቴ 5 አመት ሙሉ ስቆስል እንደነበር አያውቅም። እኔ አልናገርማ። ገመናዬን ለ ቤተሰቦቼ አውርቼው አላውቅማ። "ዛሬ ገና ቢያስቀይምሽ" ቢለኝ ይገርማል ታድያ?የ ሰርጌ ቀን ማግስት ከነጓደኞቹ ተሰብስቦ ሲቅም እንደዋለ እኮ አልተናገርኩም። ሰላቱን ሲሻው እንደሚሰግድ ሲለው እንደሚተው አልተነፈስኩም። ከዛሬ ነገ ይሻላል ብዬ ነዋ።
ይቀጥላል ።
@sumeyasu
2.8K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ