Get Mystery Box with random crypto!

ሱመያ ሱልጣን 'ይህችንም ቀናት በሰዎች መካከል እናዘዋውራታለን'   ሁሌ ሲከፋኝ እንደማደርገው እሷ | Sumeya sultan

ሱመያ ሱልጣን
"ይህችንም ቀናት በሰዎች መካከል እናዘዋውራታለን"
  ሁሌ ሲከፋኝ እንደማደርገው እሷ ላይ ብሶቴን ልዘረግፍ እየተንደረደርኩ በሯ ላይ ደረስኩ። አይኔን አይታ ይገባታል። እንባዬ ቤተሰብ ከሆነበት ደረቷ ለጥፋ ሰላም አለችኝ። እንደ ሁልጊዜው ጨንቆኝ ስሄድ እንደምታቅፈኝ አይነት፣ ልክ ብትለቀኝ የምበርባት የሚመስል አይነት ጭምቅ የሚያደርግ አስተቃቀፍ። እንደሁልጊዜው ሳልጠየቅ እንባዬን እያዝረከረኩ የሆንኩትን እተርካለሁ።
ለወትሮው አልቅሼ እስኪወጣልኝ በ  ፀጉሮቼ መሃል ጣቶቿን ከትታ እያርመሰመሰች "አይዞሽ፣ ያልፋል፣ አንቺ እኮ ጠንካራ ነሽ..." የመሰሳሉትን ከማለት በዘለለ በለቅሶዬ መሃል ልክ እንደዛሬው ኮስተር ብላ" ምን ሆነሽ ነው?" ብላኝ አታውቅም ነበር። ከደረቷ ስታነሳኝ  እንባ ያበሰበሰውን ሽፋሽፍቴን ገልጬ አየኋት። አሁንም ኮስተር እንዳለች ናት። አጠገቧ ያለውን "ሶፍት" እንድታቀብለኝ ከጀልኩ። "ተነስተሽ ውሰጂ" አለችኝ። ለ አይኔ ተደርቦ ያለቀሰውን አፍንጫዬን በሶፍት አባብዬ መናገር ጀመርኩ። " ዛሬዬ ትላንትናዬ ላይ ሆኜ እንዳሰብኩት አይደለም። ትላንት ላይ ሆኜ ስለ ዛሬ ሳስብ    ከ እንቅልፍ አለመንቃት ብቻ ነበር የሚያሰጋኝ። መንቃት ያጓጓኝ ነበር። ብዙ ህልም ነበረኝ። ግን እንደምታዪኝ ነኝ። በኔ እድሜ ያለ ሰው ቢኖረው የሚያሳዝነኝን አይነት ዛሬ እየኖርኩ ነው። ተስፋ የሌለው ህይወት፣ ከ እንቅልፌም ስነሳ ያው የትላንቱ አይነት ተራ ቀን እንደው ቀየር ካለም የሆነ ተጨማሪ ችግር ቢኖረው ነው። ከጓደኞቼ በታች ነኝ። ነገዬ ላይ ላጣቸው የማልፈልጋቸውን ሰዎች በራሱ ዛሬ ሸሽተውኛል።"ብዙ ማለት ፈልጌ ነበር። ለምን ተሳሰረብኝ?? እንዴት ግን "አይዞሽ "አላለችኝም? ለራሴ ጠይቃለሁ። "ያንቺ ችግር "ከ አላህ ራህመት ተስፋ አትቁረጡ" ከሚለው አንቀፅ የከፋ ነው?? " ችሮታዬ ነገርን ሁሉ ሰፋች" ከሚለው የ ቁርኣን አያት የበዛ ??
ለባሪያው ከ ደምስሩ በላይ ቅርብ ከሆነው ጌታሽ የተሻለ ረዳት ከወዴት ልታገኚ ትከጂያለሽ ሱም??"think about your favourite verse " "ይህችንም ቀናት በሰዎች መካከል እናዘዋውራታለን(3:140) " ለመንጋት ይጨልማል።  ትላንት " አላህ አፊያ ያድርገው" ያልኩትን ሰው " አላህ ይርሃመው" እያልኩ ነው። በፍጹም እንዳታዝኚ አላህ አንቺ ለራስሽ ከምታስቢው በላይ ያስባል፣ አንቺ ራስሽን ከምትወጂው በላይ ይወድሻል። ጌታሽን ከሱ ባለመከጀልሽ እንዳታስቀይሚው"
ልቤ ላይ እርግትትት ሲል ተሰማኝ።
ይህን ቃል አስታወስኩ። *ሱራህ 2, አያህ 186*
وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِى عَنِّى فَإِنِّى قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لِى وَلْيُؤْمِنُوا۟ بِى لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡
================================
@sumeyasu