Get Mystery Box with random crypto!

       ፋቂው(ሱመያ ሱልጣን) ተንገጫገጭ ልቤ፥ ድከሚ፣ ባትቺ፣ ከወዲም ከወዲያም፣ ውድቀትን ሸም | Sumeya sultan

       ፋቂው(ሱመያ ሱልጣን)
ተንገጫገጭ ልቤ፥ ድከሚ፣ ባትቺ፣
ከወዲም ከወዲያም፣ ውድቀትን ሸምቺ።
ድከሚ ፣ባትቺ ፥ወዲያም ተንከራተች፣
ያቀረብሽው ሃሳብ ፣ከሄድሽበት ይተች።
ተንገጫገጭ ልቤ፥ ድከሚ፣ ባትቺ፣
ከወዲም ከወዲያም፣ ውድቀትን ሸምቺ።
እዚም ያጣጥሉሽ ፣እዚያጋም ያንቅሩሽ፣
ይሆናል ያልሽውን፤ አይሆንም ይበሉሽ።
ተንገጫገጭ ልቤ፥ ድከሚ ፣ባትቺ፣
ከወዲም ከወዲያም፥ ውድቀትን ሸምቺ።
ግዴለሽም ነፍሴ፣ ጥቂት ተንገዳገጅ፣
                     እንዲያውም ውደቂ፣
ይጉዱት አንቺነትን!፣ ቃሉ እስኪወጣሽ፣
አልችልም እስክትይ፤ " 'ችላለሁ እስክትፍቂ።
ፋቂዋ፣
ያን "እችላለሁ"ን ፣ባልችልም ተኪዋ።
ፋቂዋ፤
ያ'መታት ህልምሽን፣ ካፈር ደባልቂዋ ።
ፋቂዋ፤
ለ"እችላለሁ" አቀንቃኝ፣ ያንን ምላስሽን፣
                       አትችልም በይዋ።
ፋቂዋ፤
ብድግ በይና፥ ከቀበሩሽ ሰዎች፥
ኮቴን ተከትለሽ፣
ጥለውሽ ሲሄዱ ፣በይ በራስሽ ተነሽ።
ያኔ ተመልከቺ፣ ራስሽን አቅኚው፣
ከተቀበርሽበት፣ አንገትሽን አውጭው፤
ከቀባሪዎችሽ ፣አንዱንም አታይው፤
ድሮስ መቅበር ፣እንጂ መዳረሻሽማ፣
                          መቼ ሲገዳቸው?!
በይ አሁን ተነሺ!፣ የተጣለብሽን፣
    የቀብሩን አፈር ፣ከላይሽ አራግፊ፤
ከዛ ወደፊት ግፊ!!!!
በይ ግፊ!!!!
ተንገጫገጭ ልቤ፣ ድከሚ፣ ባትቺ፣
ከወዲም ከወዲያም፣ ውድቀትን ሸምቺ፤
ከፍታ ለመውጣት፣ ከታች ሆነሽ ቧጥጪ።
@sumeyasu