Get Mystery Box with random crypto!

ጠያቂ :_ የዳዕዋ ሰው ሆኖ አቂዳ ማስተማርንና መማርን አንዳንድ አህባቦች ከ20 አዳብ ጋር ይጋጫል | ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

ጠያቂ :_ የዳዕዋ ሰው ሆኖ አቂዳ ማስተማርንና መማርን አንዳንድ አህባቦች ከ20 አዳብ ጋር ይጋጫል ይላሉ ፣ ይህን እንዴት ይመለከቱታል?

ዶክተር ሱለይማን አልዓይዲይ: የዳዕዋ ሰው ቁርአን አይቀራምን ?

ጠያቂ: _ ይቀራል

ዶ/ር ሱለይማን: የዳዕዋ ሰው ሀዲስ አይማርምን? በተእሊም ወቅት አያነብምን?

ጠያቂ: ያነባል

ዶ/ር ሱለይማን: ቁርአንና ሀዲስ ላይ ሙተሻቢሃት ( ትርጉማቸው ግልፅ ያልሆኑ አሻሚ) ቃላት አሉ ፣ ማንኛውም እነዚህን ሙተሻቢሃት የሚያነብ ሙስሊም ሶስተኛ የሌላቸው 2 አማራጮች ብቻ ናቸው ያሉት: _

ሀ) የእነዚህን ሙተሻቢሃት ጥሬ ትርጉም በመያዝ አሏህን በተጅሲም መግለፅ ።

ለ) አቂዳውን በስርአት ተምሮ እነዚህን ሙተሻቢሃት ቀደምት ኡለሞች በተረዱት ትክክለኛው መንገድ ተረድቶ ራሱን ከተሽቢህና ከተጅሲም መጠበቅ ።

በያናቶቻችን ፣ ታእሊሞቻችን፣ ዳዕዋዎቻችን ወዘተ ላይ ጥልቅ የሆኑ አቂዳዊ ጉዳዮችን አናነሳም በመድረሳዎቻችንና መስጂዶቻችን ላይ ግን የአህለሱና ወልጀመአ አቂዳ የሆነውን የአሻዒራና ማቱሪዲያን አቂዳ ያለ ምንም ፍርሃት እናስተምራለን ።

* በዚህ የሸይኹ ሃሳብ ላይ እኔም ሃሳብ ላዋጣ ፣ ዳዕዋ ልዩነት ባለባቸው ነጥቦች ላይ መመርኮዝ እንደሌለበት የቀደምት አሊሞችም እይታ ነው ፣ በተለይ ጥልቅ አቂዳዊ ጉዳዮችን በብዙሃኑ ህዝብ ፊት መፈትፈትን እስከ ሃራምነት ያደረሱ ኡለሞች አሉ ከነርሱ መካከል አንዱ ኢማም አልገዛሊይ ናቸው ።

https://t.me/sufiyahlesuna