ስንት ረከአ እንደሰገድን ግራ ቢገባን ምን እናደርጋለን አንዳንድ ጊዜ ሰላት እየሰገድን ስንት ረከአ እንደሰገድን ግራ ይገባናል ለዚህ ችግር የፊቅህ ኡለሞቻችን መፍትሄ አሰቀምጠዋል እርሱም " እርግጠኛ የሆንበትን የረከአ ቁጥር እንደሰገድን አስበን የተጠራጠርነውን ረከአ እንደ አዲስ መስገድ ነው ። ለምሳሌ: _ ዙህር ሰላት ላይ 3 ነው ወይስ 4 ነው የሰገድኩት ብለን ግራ ብንጋባ 3 እንደሰገድን ቆጥረን አንድ ረከአ እንጨምራለን ምክንያቱም 3 ነው ወይስ 4 ነው የሰገድኩት ስንል 3 መስገዳችንን እርግጠኛ ሆነናል ፣ ጥርጣሬ የተፈጠረው አራተኛው ረከአ ላይ ነው ፣ ከጥርጣሬ ተነስተን ሰግጃለው ብለን መደምደም ስለማንችል አንድ ረከአ ጭማሬ እናመጣለን ። https://t.me/sufiyahlesuna 463 viewsedited 04:13