Get Mystery Box with random crypto!

#አመለካከትህን_በመቀየር_ህይወትህን_ቀይር በቻይና ውስጥ እጅግ ባለጸጋ የሆነው “ጃክ ማ” ሲሆ | የስኬት ምስጢሮች

#አመለካከትህን_በመቀየር_ህይወትህን_ቀይር

በቻይና ውስጥ እጅግ ባለጸጋ የሆነው “ጃክ ማ” ሲሆን 39 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት አለው ። ጃክ ማ እንዲህ ይላል፡- ‘’ገንዘብና ሙዝን ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ ። ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አያውቁም!

አብዛኛው ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ (ቢዝነስ) እና በወር ደመወዝ መካከል ምርጫቸው ምን እንደሆነ ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ወርሃዊ ደመወዝ ያለው ስራን ይመርጣል ። ምክንያቱም ትንሽም ቢሆን የግል ስራ (ቢዝነስ) ከወርሃዊ ደሞዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣና ህይወት የሚቀይረው ይህ እንደሆነ ስለማያውቁ ነው ።

ሰዎችን ለድህነት ከሚዳርጉት ነገሮች አንዱ ከግል ስራ (ቢዝነስ) የሚመጡትን እድሎች ማየት አለመቻላቸው ነው ።
ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ በትምህርት ቤቶች የሚማሩት ስራ ማለት ሁልጊዜ ለወርሃዊ ደመወዝ መስራት መሆኑን ነው ። ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለሌሎች መስራትን ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተምረዋል! እውነት ነው የወር ደሞዝ ከድህነት ይጠብቅሃል ። ነገር ግን ሀብትን እንዳታገኝ ያደርግሃል ።

በህይወቴ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት የሚሰራ ተቀጣሪ ሰው ሀብታም ሆኖ አይቼ አላውቅም ።’’ ይላል ጃክ ማ ። እውነት ነው እኛም አገር ያለው ነባራዊ እውነታ ይሕ ነው ። ምክንያቱም ተቀጥረህ በምታገኘው የወር ደመወዝ ሀብት ፣ ጥሪት ፣ ቤትና ራስህን ለውጠህ ሌላ ሰው መርዳት አትችልም ። እርግጥ ነው የወር ደመወዝ ሲኖርህ የምትፈልገውን ማድረግ ባትችልም በገቢህ ልክ መኖርን ትለምደዋለህ ። ለማንኛውም በሥራ ፍለጋ ጊዜ ከማባከን በትንሹም ቢሆን የግል ስራ የምትጀምሩበትን የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።