Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ጥያቄዎች - spiritual questions

የቴሌግራም ቻናል አርማ spiritualquestions — መንፈሳዊ ጥያቄዎች - spiritual questions
የቴሌግራም ቻናል አርማ spiritualquestions — መንፈሳዊ ጥያቄዎች - spiritual questions
የሰርጥ አድራሻ: @spiritualquestions
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.22K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ይካሄዳል ሁላችሁ ተሳተፉ
ጥያቄ ና አስተያየት ካላችሁ በዚህ ላኩ ና አናግሩን
👇👇👇👇👇
@SendSpiritualquestionBot
" ስለዚህ በሰው ፊት #ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው #በአባቴ ፊት #እመሰክርለታለሁ፤"" (የማቴዎስ ወንጌል 10:32)
👇👇
ለሁሉም የኦርቶዶክስ አማኝ ይደርስ ዘንድ በቅንነት share አድርጉ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-28 20:46:18 ★ መረቡን ከታንኳይቱ በስተቀኝ ጣሉ ★

ስምዖንና ጓደኞቹ ዓሣ አጥማጆች ናቸው። ሌሊቱን ሙሉ ሲያጠምዱ አድረው አንድ ዓሣ እንኳን ሳይይዙ ነጋባቸው። ባዶ መረባቸውን እያጠቡ እያለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እነርሱ መጣ። አስተምሮ ከጨረሰ በኋላ ስምዖንን : "ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል መረቦቻችሁንም ለማጥመድ ጣሉ" አለው።

ስምዖን ከአምስት ዓመቱ ጀምሮ ዓሣ ሲያጠምድ ያደገ የሃምሳ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነው። ሆኖም "ጥርሴን የነቀልኩበት ሙያ ነው" ብሎ ሳይመፃደቅ "አቤቱ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም።

ነገር ግን በቃልህ መረቦቹ እጥላለሁ" አለ። የጌታን ትእዛዝ አክብረው ወደ ጥልቁ ፈቀቅ ብለው መረባቸውን ሲጥሉ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ ፣ መረቦቻቸውም ተቀደዱ። በሌላ ታንኳ የነበሩት ጓደኞቻቸውን እንዲያግዙአቸው ጠሩአቸው። ታንኳው እስኪሠጥም ድረስ መረቡ በዓሣ ተሞላ።
ይህንን ተአምር ያዩ ሁሉ ሲደነቁ ስምዖን ጴጥሮስ ግን ጌታችንን ፈራው። በዚህ ትልቅ ባሕር ውስጥ ያለውን መርምሮ ካወቀ በእኔ ልብ ውስጥ ያለውን ኃጢአትማ እንዴት ያውቅብኝ ይሆን? ብሎ ተጨነቀ ፣ የረከሰ ሕይወቱን አስቦ ራሱን ተፀየፈ።

ከኢየሱስ ጉልበት ላይ ወድቆ "ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ" አለው። ጌታ ግን "አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ" አለው።

ያቺ ዕለት ስምዖን ጴጥሮስና ጓደኞቹ ጌታ ባዘዛቸው መሠረት መረብ እየጣሉ ዓሣ ማጥመድ የጀመሩባት ዕለት ሆነች። (ሉቃ 5:3)
ይህ ከተፈፀመ ከሦስት ዓመታት በኋላ ጌታችን በመስቀል ተሰቅሎ ሞቶ ከተነሣ በኋላ ትንሣኤውን ሙሉ በሙሉ ያላመኑት ስምዖን ጴጥሮስና ጓደኞቹ ዓሣ ለማጥመድ ወደ ባሕር ሔደው ነበር።

ጌታችን በዚህ ጊዜ ከመካከላቸው ተገኝቶ "አንዳች የሚበላ አላችሁ?" አላቸው። እነርሱም የለንም አሉት። ይህን ጊዜ "መረቡን በታንኳይቱ በስተቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ" አላቸው።
መረቡን ሲጥሉ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጎትቱት አቃታቸው። (ዮሐ 21:6)
በጌታ ትእዛዝ ዓሣ ሁለት ጊዜ የሚጠመድባት ይህች መረብ በዓሣ የተመሰልን እኛን የሰበሰበች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት።
በመጀመሪያው ዙር ዓሣ የማጥመድ ሥራ የተካሔደው "ወደ ጥልቁ በመሔድ ነበር" ቤተ ክርስቲያን ከዚህች ዓለም ባሕር ውስጥ ብዙዎችን አጥምዳለች። በዚህ ዓለም በኃጢአት ዐዘቅት ውስጥ ጠልቀው የገቡትን ሰዎች ሳይቀር መረብዋ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጥልቁ ፈቀቅ ብላ አጥምዳ ሰብስባለች። በዚህ ነፍሳትን የማጥመድና ወደ መረቡ የማስገባት ሥራ ላይ የተመደቡት እነቅዱስ ጴጥሮስ ቢሆኑም ከዓሣዎቹ ብዛት የተነሣ ለብቻቸው ሊወጡት አልቻሉም።

ስለዚህ በሌላ ታንኳ የነበሩ ጓደኞቻቸውን ጠርተው መረቡን በዓሣ ሞሉት። እነዚህ በረዳትነት የተጠሩት የሐዋርያት ጓደኞች ምእመናንን ከዓለም ጥልቅ ውስጥ በትምህርት እየሳቡ ወደ መረቧ ቤተ ክርስቲያን ሲያስገቡ የኖሩ አርድእት ፣ ሐዋርያውያን አበው ፣ ሊቃውንትና ካህናት ናቸው። በጴጥሮስና በመሰሎቹ ትጋት ዛሬ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ዓሣዎች ተሞልታለች። ዓሣዎቹ በበዙ ጊዜ መረቡ ተቀድዶ ነበር። እንደዚሁም ኃጢአተኛውን ከጻድቁ ክፉውን ከደጉ ሳትለይ ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበችው ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው በዓሣዎቿ ብዛት ብዙ የመቀደድ ፈተና ገጥሟታል።

አንዳንድ ዓሣዎች ከባሕር ከወጡ በኋላ ወደ ባሕር ለመመለስ ሲታገሉ ፣ አንዳንዶቹ ባሕር ውስጥ እያሉ እንደሚዋኙት ሊዋኙ ሲሞክሩ ፣ አንዳንድ ዓሣዎች መረብ ውስጥ ገብተው ሲፋለሙ መረቡን ቀድደውት ነበር። የእኛዋ መረብ ቤተ ክርስቲያንም ይህ ዓይነቱ በዓሣዎቿ ጦስ የመቀደድ ችግር ሁሌ እንደገጠማት እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች።

ይህ ሁሉ ችግር ግን ጌታችን ዳግም እስኪመጣ ድረስ ነው። ወደነ ቅዱስ ጴጥሮስ ድጋሚ መጥቶ መረቡን ጣሉ ያለው ጌታ ስለ ቤተ ክርስቲያንም ይህን ማለቱ አይቀርም። እስቲ ሁለተኛውን የዓሣ ማጥመድ ሥራ አስተውለን እናንብበው።

መጀመሪያ "ወደ ጥልቁ ጣሉ" ያለው ጌታ ከትንሣኤ በኋላ ግን "በስተቀኝ ጣሉ" ብሏል። ከጥልቁ ብዙ ዓሣዎች የሰበሰበችው መረብ ቤተ ክርስቲያን ጌታ ዳግም ሲመጣ ድጋሚ ዓሣ ትሰበስባለች።

ያን ጊዜ ግን የምትሰበስበው "በስተቀኝ" ብቻ ነው። በዓሣዎችዋ ብዛት ስትቀደድ የኖረችው ቤተ ክርስቲያን ከትንሣኤ በኋላ ግን ዓሣዎችዋ ብዙ ቢሆኑም እንኳን አትቀደድም።
ምክንያቱም ጌታ "በስተቀኝ ጣሉ" እንዳለው ከትንሣኤ በኋላ ወደ መረቡ የሚገቡት ጌታ አስቀድሞ በቀኙ ያቆማቸው ቅዱሳን ሰማዕታት ምእመናን ናቸው። ቅዱሳን ደግሞ የቱንም ያህል በቁጥር ቢበዙ መረብዋ እንድትቀደድ አያደርጉም።

ጌታችን ዳግም መጥቶ መረብዋን ቤተ ክርስቲያን በሚያስጥልበት ጊዜ በስተቀኝ ሆነው ከሚገቡት ከነቅዱስ እስጢፋኖስ ፣ ከመጥምቁ ዮሐንስ ጋር ፣ ከሁሉም ቅዱሳን ሰማዕታት ጋር ለመገኘት ያብቃን።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

@mekra_abaw
1.2K views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 08:14:30 ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። በቻናሉ ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት

ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት





ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
2.3K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 21:08:13 የፋሲካሰላምታአሰጣጥትርጉም

ምሕዛል ወቃለ ባሕ ዘትንሣኤ Paschal troparion & Greeting

(ለትንሣኤ የተቆነጠረ ሐሳብ)

ሀገርኛው የዘውትር ሰላምታችን ሰላም ላንተ ይኹን ጠላትኽን ያውድቅ ቢሰኛኽን ያርቅ! በሚል መነሻ ስብሐተ እግዚአብሔር የሚታከልበት ምኞት መግለጫና ምስጋና ማቅረቢያ ነው!

የሰላምታው መንገድ ደግሞ በሦስት ሂደት (በቃል በእጅና በአንገት) የሚከወን ነው።


መጨባበጥ (ተራክቦተ እድ ፣ ፅብጠት፣ ተጻብሖ) ☞ በእጅ የሚፈጸም ፦ በመጨባበጥ handshake በመተቃቀፍ hugging አልያም በጉንጭ በመሳሳም cheek kissing ይፈጸም የነበረውን በቀደሙቱ ዘንድ “አምኃ ቅድሳት” holy kiss & kiss of peace ⇨ ἐν ἁγίω φιλήματι, και φιλί της ειρήνης እየተባለ የሚጠራው መንገድ ነው!

በዚኽ አጋጣሚ በወቅቱ ጉዳይ መጨባበጥ መተቃቀፍና መሳሳም ለወረርሽቹ በፍጥነት መዛመት ምክንያት መሆናቸውን አውቀን
#አካላዊፈቀቅታ|ን በመጠበቅ በበሽታው የምናልፍ ሳንሆን በሽታውን የምናሳልፍ ነገንም የምናይ እንድንሆን በተከታዮቹ መንገዶች ሰላምታ የምንለዋወጥ ይሁን!


"እጅ መነሳሳት" (እማኄ) ☞ ባንገት፣ በወገብና በጕልበት የሚፈጸም ነው


የሰላምታ ቃል መለዋወጥ (በቃለ ተአምኆ) ሰላምታ በንግግር በመለዋወጥ የሚፈጸም ዋናዎቹ ናቸው!

ወደ ተቆነጠረው ሐሳብ እንለፍ ተዝካረ ትንሣኤው በሚታሰብበት ዐባይ ፋሲካ ፶ ዕለት በቤተክርስቲያናችን የሚፈጸም የተለየ ሰላምታና የዜማ ድጋም አመላለስ አለ

የጌታችን ተዝካረ ትንሣኤ በቤተክርስቲያናችን ሰፊ ቦታና ትርጉም ያለው በመሆኑ የዓመት ሢሦው (⅓) ነገረ ፋሲካን የሚያስታውስ ነው (የፋሲካ ጾም ⁵⁵ እና ዘመነ ትንሣኤ⁵⁰)

በቅዳሴው መግቢያ መስዋእቱ ከቤተልሔም ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጣ ከትንሳኤው እስከ በዓለ ፶ ጊዜው የተለየ መሆኑን ለማሳወቅ "እመቦ ብእሲ… " በሚለው መግቢያ ፈንታ "ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪነ ⇨ ሃሌ ሉያ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ድንቅ በሚሆን ጥበብ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ኢየሱስን በበፍታ ገነዙት፡፡" የሚል መልእክት በዜማ ይደርሳል!

ከዚኽ ውጪ ምሕዛል ዘትንሣኤ ወይም «የፋሲካ አመላለስ» ያልነው Paschal troparion እና ቃለ ባሕ ዘትንሣኤ «የፋሲካ ሰላምታ» ያልነው Paschal Greeting ከወትሮው በተለየ መንገድ ይፈጸማል። ሁለቱም በልሳነ ጽርእ (ግሪክ) #ክሪስቶስ_አኔስቲ / Χριστὸς ἀνέστη እየተባለ ይጠራል

① #ምሕዛል_ዘትንሣኤ Paschal troparion የፋሲካ አመላለስ

በእርግጥ ምሕዛል አልያም ምስትሕዛል የሚባለው በድጓው ሊቃውንቱ የሚያስተዛዝሉት ዜማ ድጋም ሲሆን መነሻውን ድጓ ያደረገው በቅዳሴው ክፍል የምናገኘው ይኽ የተዝካረ ትንሣኤ ምስትሕዛል፦
«ህየንተ ዝውእቱ ጊዜ ባርኮት እምትንሣኤ እስከ በዓለ ፶ » በሚል የገባ ሦስት ጊዜ ደጋግመን በመቀባበል የምናደርሰው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ "

በሌሎች ምሥራቃውያን (Eastern ) እና ጽባሓውያን (Orientals) ዘንድም በእጅጉ የተለመደ ነው!

በግሪክ ፓስካል ትሮፓርዮን አልያም χριστος ανεστη የሚባል በዜማ የሚደርስና የዘመነ ሐዋርያት ጭምር ጥንታዊ መገለጫ አለው ተብሎ የሚታመን ነው።

Χριστὸς ἀνέστη ἐκ νεκρῶν,

θανάτῳ θάνατον πατήσας,

καὶ τοῖς ἐν τοῖς μνήμασι,

ζωὴν χαρισάμενος!

የንባባዊ ፍቺው አማርኛ ትየባ (transliteration) ደግሞ ይኽን ይመስላል!

ክርስቶስ አኔስቲ ኤክ ኔክሮኒ ፣ ታናቶ ታናቶን ፓቲሳስ፣ ኬቲስ ኤን ቲስ ሚ’መሲ፣ ዞይን ካሪዛሜኖስ

በትርጉሙም የእኛው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ " ካለው ጋር አቻ ፍቺ አለው

Christ is risen from the dead, Trampling down death by death, And upon those in the tombs, Bestowing life!

② #ቃለባሕዘትንሣኤ Paschal Greeting «የፋሲካ ሰላምታ»

በሓ ወይም ባሕ የሚባለው የሰላምታ የቡራኬ ቃል ፍሥሓ ሰላም የሚለውን የሚገልጥ ነው!

በቤተክርስቲያናችን አበው መምህራንም ቅድመ ቃለ እግዚአብሔር ፣ ድኅረ ቃለ ቡራኬ ለ፶ው ዕለት ከምእመናን ጋር የሚለዋወጡት ሰላምታ ነው! ከዚያም አልፎ ምእመናንም ከምእመናን ጋር የትንሳኤውን የምሥራች ለማብሰርና መልካም ምኞት ለመግለጥ ያውሉታል።

አቀራረቡ በአመላለስ አገባብ የሚከወን ሲሆን ሰላምታ ሰጪና ሰላምታ ተቀባይ ይኽን ይለዋወጣሉ፤

በኢትዮጵያዊቷ የተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያናችም ከ6ኛው ምዕተ ዓመት አንስቶ አገልግሎት ላይ መዋሉን መረጃዎች ይገልጣሉ። በቅዱስ ያሬድ ምዕራፍ (ዘመወድስ) ውስጥ በፍታሕ ሊተ ሥር በመሪና ተመሪ የሚቀርብ ዛሬ ለፋሲካ ሰላምታ የምንገለገልበት የትንሣኤው ምስክርነት ቃል አለ። እንዲህ ይላል ፦

☞ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ፣ በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን ፣ አሠሮ ለሰይጣን ፣ አግዓዞ ለአዳም ፣ ሰላም ፣ እምይእዜሰ ፣ ይኩን ፣ ሰላም!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፣ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ፣ ሰይጣንን አሠረው፣ አዳምን ነጻ አወጣው ፣ ሰላም፣ ከዛሬ ጀምሮ ፣ ይሁን ፣ ሰላም

በመቀባበል እንዲህ ተጽፏል

☞ Christ is risen from the dead!
☜ By the highest power and authority!
☞ He chained Satan!
☜ Freed Adam!
☞ Peace!
☜ Henceforth!
☞ Is!
☜ Joy and Peace!

☞ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
☜ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!
☞ አሰሮ ለሰይጣን!
☜ አግዐዞ ለአዳም!
☞ ሰላም!
☜እምይእዜሰ!
☞ ኮነ!
☜ ፍስሐ ወሰላም!

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው፤ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ.....
See more
[@mekra abaw
1.1K views18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 20:31:58 ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። በቻናሉ ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት

ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት





ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
975 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 14:12:12 ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም

"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል
ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ
ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና፤ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ
ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና"
፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳
ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን። በዓሉን የሰላም የፍቅርና የበረከት ያድርግልን።

ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ

@mekra_abaw
@mekra_abaw
1.1K views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 13:58:02 9/08/14 ዓ.ም
መዝሙር ዘሆሳዕና
"ወእንዘ ሰሙን"

በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚሰበክ ምስባክ።

ዲ/ን - ዕብ 9÷11- ፍ ም
ን/ዲ - 1ጴጥ 4÷1-12
ን/ካ - ግብ፡ሐዋ 28÷11-ፍ ም

የዕለቱ_ምስባክ - መዝ 8÷2
እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ
በእንተ ጸላኢ
ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ

ትርጒም
ጠላትን ለማሳፈር ቂመኛንና ግፈኛንም ለማጥፋት ከህፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ::

ወንጌል፦ ዮሐ 5÷11-31
ቅዳሴ: ዘጎርጎርዮስ
በቴሌግራም
@mekra_abaw
በዩቲዩብ ማግኘት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
1.3K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 11:42:21 #urgencynews
መረጃ እንጠቁማችሁ

ኢትዮ ቴሌኮም ቲክቶክ ገጹን follow ላደረጉና ስልካቸውን በውስጥ መስመር ለላኩ ወርሃዊ ያልተገደበ ጥቅል እየሸለመ ነው።

የቲክቶክ አካውንት ካለህ ምን ትጠብቃለህ


https://www.tiktok.com/@ethiotelecom?lang=en
ቻናላችን ይኸው
https://t.me/+ieH42z8ELW40ODdk

እንዴት እንደሚደረግ ካላወክ ቻናሉን join ብለህ ተረዳ
1.2K views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 08:19:00 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ

የቸብቸቦ መዝሙራት
▓⇨→audio ⇨ግጥም
የበገና መዝሙራት
▓⇨→audio ⇨ግጥም
የቅዱሳን መዝሙራት
▓⇨→audio ⇨ግጥም
የንግስ መዝሙራት
▓⇨→audio ⇨ግጥም
የምስጋና መዝሙራት
▓⇨→audio ⇨ግጥም
የንስሐ መዝሙራት
▓⇨→Audio ⇨ግጥም
የሠርግ መዝሙራት
▓⇨→audio ⇨ግጥም
ወቅታዊ መዝሙራት
▓⇨→audio ⇨ግጥም
ለአገር የተዘመሩ
▓⇨→audio ⇨ግጥም


@ortodoxmezmur21
@ortodoxmezmur21


▓⇨→ሌሎችንም ለማግኘት... @ortodoxmezmur21
1.2K views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 06:25:56 መልካም ዜና መልሱን በትክክል ለመለሰ በ 02/08/2014 የ100ብር ካርድ ተዘጋጅቷል ጥያቄው

1, ኒቆዲሞስ ማነው ጌታ ኒቆዲሞስን ምን አለው
ከኒቆዲሞስ ምን ትማራለህ/ሽ/

መልሱን በትክክል ለመለሱ #የዩቲዩብና የ #ቴሌግራም አባሎቻችን የ ካርድ በነገው ዕለት

ቻናላችን @Spiritualquestion

YouTube Sibuh tube

ተሸላሚ ለመሆን መልሱንና የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያደረጋችሁትንscreen shot @habmisget ይላኩልን ከዚህ በፊት ሰብስክራይብ ካደረጋችሁ መልሱን ብቻ
1.2K views03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 13:23:38 113332 2-1132 33354 /54/
14 225451 /1/ 14 22 4-2 54 /54/
14 225451 14 22 4-2 /42/
/ኧኸ - 14/
አጥንትን የሚያለመልም ምድራዊ ያላይደለ ማኅሌታይ ያሬድ ከገነት አዕዋፍ የቀሰመው ሰማያዊ ዜማ አንዱን እንሆ ኑ አብረን እናዚም ጥናቱ ነገ ይጀምራል

ሌሎች የ ሆሳዕናን መዝሙሮችን ለማግኘት ስቡሕ ቲዩብን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCfWtKqb7qsxjXey4kN_tykg?sub_confirmation=1
በቴሌግራም
@mekra_abaw
1.1K views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ