Get Mystery Box with random crypto!

ስነ ፈለክ በአማርኛ

የቴሌግራም ቻናል አርማ space_sciences — ስነ ፈለክ በአማርኛ
የቴሌግራም ቻናል አርማ space_sciences — ስነ ፈለክ በአማርኛ
የሰርጥ አድራሻ: @space_sciences
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 589
የሰርጥ መግለጫ

🔰በአይነቱ ልዩ የሆነ ቻናል‍🔊️ ስለ ጠፈር🌎 ሳይንስ ለምትወዱት እና ማወቅ ለምትፈልጉ ሁሉ የሰነ ጠፈር ሳይንስን በአማርኛ ተቀነባብሮ በልዩ መልክ ቀረበላቹ።🎊
🎯 አሰደናቂ ስለሆነው ጥንታዊ የኢትዮጰያ ስነ ፈለክ
🎯 ስለ ዩኒቨርስ እና ጋላክሲዎች 💫
🎯 9 ፕላኔቶች🌎
🎯 ህብራተ ከዋክብት☄
ይቀላቀሉት ይወዱታል ይገረሙበታል።🔲
ᴄƦᴇᴀᴛᴏƦ @Bboysis

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-30 19:19:35
ዛሬ ምሽት “ቬነስ እና ጁፒተር ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠጋግተው እንደሚታዩ” የህዋ ሳይንቲስቶች አስታወቁ!

የህዋ ሳይንቲስት እና ሶሳይቲ ፎር ፖፑላር አስትሮኖሚ ውስጥ ዋና የከዋክብት ተመልካች ፕ/ር ሉሲ ግሪን ፣ ክስተቱ ለከዋክብት አጥኚዎች ብቻ ሳይሆን ለተቀረው ማኅበረሰብም አስደናቂ ብለዋል፡፡ሁለቱ ደማቅ ፕላኔቶች ዛሬ ምሽት ለመነካካት ጥቂት እስከሚቀራቸው ድረስ ነው የሚቀራረቡት።ፕላኔቶቹ በየዓመቱ የሚቀራረቡ ቢሆንም፤ ዘንድሮ ግን ከመቼውም በበለጠ የሚጠጋጉበት ነው ተብለዋል፡፡

ይህንን አይነት ክስተት እስከ ፈረንጆቹ 2039 ድረስ በድጋሚ እንደማያጋጥምም ነው የተገለጸው። ክስተቱን ዛሬ ምሽት በዐይን ወይም በአጉሊ መነጽር መመልከት እንዳሚቻልም ነው የህዋ ሳይንቲስቶች መረጃ የሚያመለክተው፡፡

via BBC Amharic
@SPACE_SCIENCES
@SPACE_SCIENCES
847 views¤°•.s̟i̟s̟.•°¤, edited  16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 11:41:21


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ !!

መልካም የትንሣኤ በዓል !


#ETHIO_CHANNEL

@HOPESIS
@Amesi_Tech
@ZODIAC_ETHIO
@ALEKA_GEBRE_HANA
@ETHIOPIA_BOOK_STORE
@SPACE_SCIENCES
@kokeb_koteri_bot
@ethio_library_robot
723 views▁ ▂ ▄ ▅ ▆ ▇༒ًٍٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̶s ̶ɪ ̶s༒ًٍٜ۪͜͡✮, 08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 11:37:57
አድዋ ዛሬ ነው አድዋ ትላንት
መቼ ተነሡና የወዳደቁት
ምስጋና ለነሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁን ወገኖች !

ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ 126ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ !

ክብር ይሄን ህይወታቸውን ሰውተው በክብር ዛሬ ላይ ላቆሙን አባቶች !


#ETHIO_CHANNEL

@HOPESIS
@Amesi_Tech
@ZODIAC_ETHIO
@ALEKA_GEBRE_HANA
@ETHIOPIA_BOOK_STORE
@SPACE_SCIENCES
@kokeb_koteri_bot
@ethio_library_robot
871 views▁ ▂ ▄ ▅ ▆ ▇༒ًٍٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̶s ̶ɪ ̶s༒ًٍٜ۪͜͡✮, 08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-28 00:09:18 ገራሚ አፕ ልጋብዛቹ...

ከዋክብቶችን ፣ ፕላኔቶችን፣ ጠፈር፣ ሶላር ሲስተም፣ አስትሮሎጂ እና የሳተላይት እንቅስቃሴ ማወቅ ከፈለጋቹ ይቺን ገራሚ አፕ እንድታወርዷት እጋብዛቹሃለው። አብዛኞቻቹ ታውቋታላቹ STELLARIUM ትባላለች።

★ በማንኛውም ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ትክክለኛን የከዋክብትን እና ፕላኔቶችን የሰማይ መገኛቸውን በቀላሉ ያሳያቹሃል።

★ የበርካታ ኮከቦች፣ ኔቡላዎች፣ ጋላክሲዎች፣ የኮከብ ስብስቦች እና ሌሎች የጠለቁ የሰማይ ቁሶች ስብስብ መመልከት እና መረጃ ይሰጣቹሃል።

★ ዓለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያን ጨምሮ ሰው ሰራሽ ሳተላይቶችን በዚ ሰዓት በየት በኩል እያለፉ እንደሆነና እንቅስቃሴያቸውን መከታተል ትችላላቹ።

★ ዋና ዋናዎቹን የፀሐይ ስርዓት ፕላኔቶችን እና ሳተላይቶቻቸውን በ3D እይታ ያገኛሉ።

ማታ ላይ ወታችሁም ስልካቹን ወደ ሰማይ በማረግ ብቻ የትኛው ኮከብ እንደወጣ ማወቅ እና ኮከቡንም በዓይናቹ መመልከት ትችላላቹ።

ብቻ ምናለፋቹ አስትሮሎጂ ምትወዱ ሰዎች ትወዱታላቹ

Size = 141Mb ነው
Share

CHANNEL
@zodiac_ethio
@zodiac_ethio

ሼር ኮከብ ቆጣሪ ቦት ▼
◉⇲ @kokeb_koteri_bot ⇲◉
◉⇲ @kokeb_koteri_bot‌‌

መወያያ ግሩፕ
◉⇲ @zodiac_group ◉⇲
◉⇲ @zodiac_group ◉⇲
641 views▁ ▂ ▄ ▅ ▆ ▇༒ًٍٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̶s ̶ɪ ̶s༒ًٍٜ۪͜͡✮, 21:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-06 20:50:48
የሰሜኑ ኮከብ ከኛ ፀሐይ 4000 እጥፍ ጊዜ ደማቅ ነው።

ብዙ ጊዜ በስተሰሜን በኩል ደምቆ የሚታየው ኮከብ ከኛ ዓለም 434 የብርሃን ዓመትን እርቆ ይገኛል ከኛ ፀሐይ ደግሞ 4000 እጥፍ ጊዜ ደማቅ እንደሆነ ይነገራል።

በነገራችን ላይ አሁን ላይ የምናየው የዚህ ኮከብ ገፅታ በ1587 የነበረውን ገፅታ ነው አሁን ያለበትን ገፅታ ለማወቅ ደግሞ ከዚህ በዋላ 434 ዓመታትን መጠበቅ ይኖርብናል ወይም እንድ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር 2455 ላይ ይሆናል የምናየው ይሄ ማለት አሁን ላይ የምናየው ኮከብ ምን አልባትም ፈነዳድቶ ጠፍቶ ይሆናል
@SPACE_SCIENCES
@SPACE_SCIENCES
@SPACE_SCIENCES
720 views▁ ▂ ▄ ▅ ▆ ▇༒ًٍٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̶s ̶ɪ ̶s༒ًٍٜ۪͜͡✮, edited  17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 08:42:58
እንኳን ለ ብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ ።

መልካም በዓል
#ETHIO_CHANNEL

@HOPESIS
@Amesi_Tech
@ZODIAC_ETHIO
@ALEKA_GEBRE_HANA
@ETHIOPIA_BOOK_STORE
@SPACE_SCIENCES
@kokeb_koteri_bot
@ethio_library_robot
761 views▁ ▂ ▄ ▅ ▆ ▇༒ًٍٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̶s ̶ɪ ̶s༒ًٍٜ۪͜͡✮, 05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 11:09:42
አለማትን የሚያድነው ቴሌስኮፕ እና አሳዛኙ ታሪክ

"kepler" በሚል የተሰየመው ቴሌስኮፕ ከኛ ሶላር ሲስተም ውጭ ያሉ አለማትን እንዲፈልግ ወደ ጠፈር የተላከ ሲሆን ከብዙ ግኝቶቹ በዋላ ከስራ ውጭ ሁኗል።

ይሄ ቴሌስኮፕ የናሳ ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ደግሞ የሒሳብ ሊቁ እና አስትሮነመር ከሆነው "johannes kepler" ነው ይሄ ሳይንቲስ ሒሳባዊ በመሆነ መንገድ የኛ አለም ፀሐይን ስትዞር ፍፁም(perfect) ክብ በመስራት እንዳልሆን ማወቅ የቻለ ሳይንቲስ ነው ለዚህም ስራው ይመስላል ናሳ በሳይንቲስቱ ስም ቴልስኩፑን የሰየመው።

በነገራችን ላይ የኛ አለም ፀሐይን ፍፁም በሆነ ክብ ብትዞራት ኑሮ በኛ አለም ላይ ወቅት ብሎ ነገረ የለም።

የሆነው ሁኖ ቴሌስኮፕ መሬትን እየትሽከረከረ ስራውን የሚሰራ ሲሆን ከ3 ዓመት በፊት ግን በአጋጠመው የኢነርጂ እጥረት ምክንያት ኦርቢቱን በማጣቱ ከስራ ውጭ ሁኗል አስገራሚው ነገረ ይሄ ቴሌስኮፕ ከስራ ውጭ የሆነበት ቀን "johannes kepler" የተሰኘው ሳይንቲስት በ1630 ከሞተበት ወር እና ቀን ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ነው ይሄም ሳይንቲስቱ የሞተበት እና ቴሌስኮፑ ከስራ ውጭ የሆነበት ቀን እና ወር "November 15" ነው ።

ቴሌስኮፑ በስራ በቆየበት ወቅት ከ530,506 በላይ ክዋክብቶችን እና ከ2,662 በላይ አለማትን ማግኘት ችሏል ቴሌስኮፑ ካገኛቸው አለማት መካከል የውሃው አለም ፣ የገሀነቡ አለም ፣ የዳይመንዱ አለም ፣ የጨለማው አለም እንዲውም የብርጭቆ ዝናብ የሚዘንብበት አለምን ያጠቃልላል።
@SPACE_SCIENCES
@SPACE_SCIENCES
@SPACE_SCIENCES
751 views▁ ▂ ▄ ▅ ▆ ▇༒ًٍٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̶s ̶ɪ ̶s༒ًٍٜ۪͜͡✮, edited  08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 21:37:32
የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
#ETHIO_CHANNEL

@HOPESIS
@Amesi_Tech
@ZODIAC_ETHIO
@ALEKA_GEBRE_HANA
@ETHIOPIA_BOOK_STORE
@SPACE_SCIENCES
@kokeb_koteri_bot
@ethio_library_robot
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
672 views▁ ▂ ▄ ▅ ▆ ▇༒ًٍٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̶s ̶ɪ ̶s༒ًٍٜ۪͜͡✮, edited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-06 08:49:24
አንስታይን እንደበየነው (postulation) በ ጠፈር ውስጥ የብርሃን ፍጥነት ባማናቸውም ተመልካቾች (ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ) ዘንድ አንድ ነው፣ በዚህ ምክንያት በተንቀሳቃሽ ሳጥን ውስጥ የሚፈጠጥ ኩነት የሚወስደው የጊዜ ቆይታ ከሳጥኑ ውስጥ ላለ ተመልካችና ከሳጥኑ ውስጥ ላለ ተመልካች አንድ አይደለም ብሏል። ለምሳሌ እሚንቀሳቀሰው ሳጥን ውስጥ ለ5 ደቂቃ ያክል ቦምብ ቢፈነዳ (ኩነት) ፣ የማይንቀሳቀሰው ከውጭ ያለ ተመልካች ቦምቡ ለ5.5 ደቂቃ እንደፈነዳ ሊያስተውል ይችላል። ሌላ ታዋቂ ምሳሌ ብንወስድ፣ ሁለት መንትያ እህትማማቾች ቢኖሩና አንዱዋ በመንኮራኩር ከመሬት ተነስጣ በብርሃን ፍጥነት በሚጠጋ ፍጥነት ጠፈርን አሥሳ ከስልሳ አመት በኋላ ብትመለስ፣ መንትያዋን አርጅታ ስታገኛት፣ ተመላሿ ግን ገና ወጣት ናት። የዚህ ምክንያቱ፣ አንስታይ እንዳስረዳ፣ የተንቀሳቃሽ ነገሮች ሰዓት ዝግ ብሎ ሲሄድ የማይንቀሳቀሱ ግን ቶሎ ስለሚሄድ ነው። ባጠቃላይ፣ የሚንቀሳቀሱ ተመልካቾች ከማይንቀሳቀሱ ተመልካቾች ጋር የተለያየ ጊዜ ለአንድ አይነት ኩነት ይለካሉ።
ምንጭ:- Wikipedia
@SPACE_SCIENCES
@SPACE_SCIENCES
819 views▁ ▂ ▄ ▅ ▆ ▇༒ًٍٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̶s ̶ɪ ̶s༒ًٍٜ۪͜͡✮, edited  05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-06 20:59:15
ኡራኑስ

ኡራኑስ መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፕላኔት ከ ፀሐይ ባለው ርቀት 7ኛ ( ሰባተኛ ) ነው። ከበፊቱ ኣጣርድ ፣ ቬነስ ፣ መሬት፣ ማርስ ፣ ጁፒተር እና ሳተርን የተባሉ ፕላኔቶች ይገኛሉ። ከበስተኋላው ደግሞ ነፕቲዩን እና ትንሹ ፕሉቶ ይገኛሉ። ይዘት ይህ ፕላኔት በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች በግዝፈቱ የሶስተኛነትን ደረጃ ይይዛል። ግዙፍ የ ጋዝ ክምችት እንደሆነ ይታመናል። በ ረጨቱ ውስጥ የጋዝ ክምችት የሆኑት ፕላኔቶች ጁፒተር ፣ ነፕቲዩን ፣ ሳተርን እና ራሱ ኡራኑስ ናቸው። በዚህም የተነሳ ጆቪያን ወይም ጁፒተርን መሳይ እየተባለ ይጠራል። በአብዛሃኛው ሃይድሮጅን እና ሂሊየም ከተባሉ ንጥረነገሮች የተሰራ ነው። በአጠቃላይ ክብደኡ ደግሞ የአራተኛነትን ደረጃ የያዘ ነው።
#facts
@SPACE_SCIENCES
@SPACE_SCIENCES
829 views▁ ▂ ▄ ▅ ▆ ▇༒ًٍٰٰٰٰٰٰٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜٜٜٖٜٖٖٖٖٖٖٖ͜͡ ̶s ̶ɪ ̶s༒ًٍٜ۪͜͡✮, edited  17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ