Get Mystery Box with random crypto!

## ከአንድ በላይ ማግባት የመፈቀዱ ጥበብ አላህ የሚፈቅድልን ነገር ሁሉ ጥበብ አለው ሲከለክለ | ሷሊሆች ለሷሊሆች ብቻ ናቸው ሀቢብና رسول صلى الله عليه وسلم

## ከአንድ በላይ ማግባት የመፈቀዱ ጥበብ


አላህ የሚፈቅድልን ነገር ሁሉ ጥበብ አለው ሲከለክለንም እንዲሁ ነገር ግን እኛ ሁሉን ላናቅ እንችላለን እስኪ የተወሰኑ ከአንድ በላይ ማግባት የተፈቀደባቸውን ጥበቦች እንመልከት

1. የሙስሊሙን ቁጥር ማብዛት ፦ ከአንድ በላይ ባገባ ቁጥር ብዙ ልጅ የመወለድ እድሉ እየሰፍ ይሔዳል ይህ ደግሞ የሙስሊሙን ማህበረሰብ እያጠናከረው ይሔዳል

2. ብዙህ ቦታ ላይ የሴቶች ቁጥር ከወንዶች ይበልጣል በመሆኑም አንድ ወንድ ከአንድ በላይ አያግባ ካልን ያለ ባል ሚቀሩ ብዙ ሙስሊም ሴቶች ይኖራሉ

3. አንዳንድ ወንዶች ስሜታቸው በጣም ጠንካራ ሆኖ በአንድ ሴት ማይረኩ አሉ እነዚህን ወንዶች ከአንድ በላይ እንዳያገቡ ከከለከልናቸው ወደ ዝሙት መሄዳቸው የማይቀር ነው። ልክ ዛሬ ላይ ከሀዲያኖች ዘንድ እንደምናየው አንድ ያገባል በጎን ግን በድብቅ ከብዙ ሴቶች ይገናኛል

4. ሴቶች የወር አበባ ላይ ሲሆኑ እና የወሊድ ደም ላይ በሚሆኑ ግዜ ከነሱ ጋር መገናኘት አይቻልም። በዚህ ግዜ ደግሞ ስሜታቸው ከፍተኛ የሆኑ ወንዶች ከአንድ በላይ ማግባት ከከለከልናቸው ይቸገራሉ። ስሜታቸውን ለማርካት ወደ ሀራም ሊሄዱ ይችላሉ

አንዳንድ ካህዲያን ከአንድ በላይ ማግባት በእስልምና መፈቀዱን ተሞርክዘው እስልምናን ለመተቸት ሲሞክሩ ይስተዋላል ነገር ግን ከአንድ በላይ ማግባት ከዚህ በፊት በነበሩ ህዝቦች ላይም ቢሆን የሚታወቅ የነበረ ተግባር ነው። የነብያቶች አባት የሆኑት ነብዩላሂ ኢብራሂም እና የበኒ ኢስራኢሎች አባት የሆኑት ነብዩላሂ ያእቁብ ከአንድ በላይ ሚስት ነበራቸው ነብዩላሂ ሱለይማን በጣም በርካታ ሚስቶች ነበሯቸው።ይህ ደግሞ በራሳቸው መጽሀፍ ላይ ያለ እውነታ ነው።

መልዕክቱ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ሸር ሸር አድርጉት

--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------

በቴሌግራም ይ ላ ሉን!


@Lewetatoch_mekir
@Lewetatoch_mekir