Get Mystery Box with random crypto!

Sofi's memo

የቴሌግራም ቻናል አርማ sofimemo — Sofi's memo S
የቴሌግራም ቻናል አርማ sofimemo — Sofi's memo
የሰርጥ አድራሻ: @sofimemo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 489
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ለእናንተ ይሁን ሶፊ ነኝ።ዝብርቅርቅ የሆነውን ማስታወሻዬን ስላነበባችሁ አመሰግናለሁ።
ያገኘሁትን Motivational voices ለናንተ አስቀምጫለሁ ይሄን ቻናል የከፈትኩት ምናልባት 1 ሰውን ከጠቀምኩ ብዬ ነው።
.
.
.
#Put_God_first.
.
.
.
❤💛💚 @bestletters

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-26 21:04:32 ሞኝ ነኝ አይደል?!

ከተቀደደው ማስታወሻ
ሶፊ

@bestletters
163 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 19:33:05 የሶፊ ደብዳቤ

ቁጥር አይታወቅም


"ብዙ ውብ የመሰሉኝ ቃላት ሊገልፁሽ ስላልቻሉ ሰርዣቸዋለሁ..."


"እሳት ሲሆን ኑሮሽ ወርቅ የሆንሽው አንቺ
ነጥረሽ እየወጣሽ ደክሜ እንዳልቀር የምታበረቺ
ምሰሶ ሳትሆኚው ጎጆ መች ይቆማል
ሙሉነት ያላንቺ እንዴት ይታለማል"

እናቴ

#Worth to share

@bestletters
239 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:04:48 ከተቀደደው ማስታወሻ
ሶፊ

Post card story by sofi

(ከ112 ሰው 61 ሰው በድምፅ ብሏል...እነሆኝ በምርጫችሁ።)

@bestletters
238 views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 21:50:56 ልነግርሽ ነበረ

ከበላይ በቀለ ወያ

"ወንዶች እብድ ሴት ይመቻቸዋል ስለተባሉ ብቻ ያበዱ ብዙ ሴቶች አሉ።"

በሶፊ

@bestletters
249 views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 20:32:47 እ ጠ ብ ቅ ሻ ለ ሁ !

ኤልያስ ሽታኹን

በሶፊ

@bestletters
317 views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 20:24:42
አንቺ ሐሳብ ውስጥ እንዳለሁት አይነት ጥሩ ሰው አይደለሁም፤ብዙ የህይወት ጉድለቶች አሉብኝ።ቃላቶቼ አንቺ ፊት አምረው እንደቀረቡት በጎ በጎ ብቻ አይደሉም፥ብዙ ሰዎችን ሰብረው ያውቃሉ።ሐሳቤም እንደምታስቢው ንፁህ አይደለም ክፉ ምኞት ይበዛዋል።ምግባሬ ቢመዘን ከሰዶም ኃጢያት ያይላል።እግዚአብሔር ቃሉን አያጥፍም እንጂ፤በእኔ ኃጢያት አለምን ለዳግም የጥፋት ውሀ በዳረኳት ነበር።

እንደምታስቢኝ አይነት ሰው አይደለሁም፥በአንቺ ዘንድ መልካም ሆኜ መታሰቤ ደስታን የፈጠረልኝ አይምሰልሽ፤ይባስ አስመሳይ የሆንኩ እየመሰለኝ በፀፀት ቆሰልኩ እንጂ...

ሁሌም እንደምታስቢኝ አይነት ሰው በሆንኩ እያልኩ እመኛለሁ፥ዳሩ ግን እንደምታስቢኝ አይነት ጥሩ ሰው አይደለሁም።


ከተቀደደው ማስታወሻ
ሶፊ (@umsofi27)
281 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 21:46:28 "ተከራያችን"

ክፍል ፰

ደራሲ፦ሶፊ


የተከራያችን ቤት በሰፊው ተከፍቷል ውስጡም ባዶ ነው።እንደ ጨው ሐውልት ደርቄ ለደቂቃዎች ቆየው። የሆነ ነገሬ ሲሰበር ተሰማኝ።ቅስሜ ይሆን? ሐሞቴ ፈሰሰ።ስለእርሷ ምንም ማወቅም መስማትም አስጠላኝ። ምንም እንዳልተፈጠረ እናቴን እቅፍ አድርጌ ሳምኳትና።ራት እየበላን ቡና ስንጠጣ..."መቼ ነው የሄደችው ?" አልኳት።
"አልነገረችህም እንዴ" አለች እናቴ በግርምት።
"አዎ እማ " አልኳት ከእንግዲህ የምዋሽበት ምንም ምክንያት የለም።
ሁኔታዬን ስታይ እናቴም ሐዘን ገባት "እናቴ ጋር ልመለስ ነው ብላ የደወልኩልህ ቀን ነው የሄደችው።ለእኔም የዛኑ እለት የሚጭንላትን መኪና እደጅ አስቁማ፤እቃ ልታወጣ ስትል ነው የነገረችኝ።ሶፎንያስ ይሄ ነበር የእኛ እና የእርሷ ቅርበት? እንደ ልጄ ነበር የማያት ከስራ ስትመጣ አብስሎ ለመብላት ይደክማታል፤ ይርባታል እያልኩ እንጀራ እየሰደድኩላት። ብቻ ሆድ ይፍጀው ባዳ ባዳ ነው።አለች እናቴ በምሬት።"
እኔ ቃል አልተነፈስኩም እናቴ ስለእርሷ ወሬ እንዳትቀጥል ቴሌቪዥኑን የምመለከት መሰልኩ።
"የሰው ልጅ ፈፅሞ ልታውቀው የማትችለው እንቆቅልሽ ነው።" የሚል አባባል ሰምቼ አውቃለሁ።የዚች ግን ይብሳል።የእርሷ ቅኔ ሰሙ እራሱ ወርቅ ነው! ትብታቧን ለመፍታት ጫፍ እንኳን አታሲዝም። ዝም ብለህ ስትጠይቅ ትኖራለህ።
፨፨፨፨የመጨረሻው መጨረሻ፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሁሉም ያልፋል ይሉ አይደል ሰዎች እውነታቸውን ነው።ሁሉም አለፈ።ትዝታዋም አልቀረ ሁሉም ተረሳ።
አመት ከመንፈቅ ሆነ
...አንድ ቅዳሜ ላይ ግን እንዲህ ሆነ።ሳምንቱን በስራ ምክንያት ሳንገናኝ የሰነበትነውን ጓደኞቼኝ አገኘዋቸው።
አንድን መፅሐፍ አንስተን እየተጨዋወትን ሳለን...አንድ ስልክ ጥሪ ተደረገልኝ...ስልኩ አውጥቼ ስመለከተው የማላውቀው ቁጥር ነው።አነሳሁት "ሶፊ" አለች ከዛኛው ጫፍ የማውቀው ድምፅ ነው ማን እንደሆነች ግን ገና አለየዋትም።"ማን ልበል?" አልኳት።
ስሟን ነገረቺኝ...እሷው ናት!
"አል...ብዬ ከአፌ መለስኩት።(አምልጦኝ አልሞትሽም? ልላት ነበር።)
ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ...እንዴት ልትደውል እንደቻለች ጠየኳት እንዲሁ ሰላም ልልህ እናም ከቻልክ ላገኝህ ነው አለቺኝ።
እንደማልችል እና አሁንም ከጓደኞቼ ጋር መሆኔን ነግሪያት...ሳልሰናበታት ስልኩን ዘጋውት።አንዳንዴ "አይሆንም"ማለትን መልመድ አለብን።የሚሆነውንም የማይሆነውንም ይሆናል እያልን ነው የተቸገርነው።
ማታ ቤት በተለመደው መልኩ ከእናቴ ጋር ካሳለፍን በኋላ ከመኝታዬ በፊት ስልኬን እየጎረጎርኩ ከአመት ከመንፈቅ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሮፋይሏን ልመለከት...ብሎክ ሊስት ውስጥ ገባሁ...
ፕሮፋይሏ በመንፈሳዊ ምስሎች እና በአባባሎች ተሞልቷል...ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ።
ፕሮፋይላችን ግን እኛን ይገልፃል? በጣም የውሸት አለም ውስጥ ከመዘፈቃችን የተነሳ፤የራሳችን ምስል እንኳን እኛን መግለፅ ትቷል።
እያልኩ ከደረደረቻቸው 80 ፎቶዎች ውስጥ 27ተኛው ላይ ስደርስ ያዝ አድርጌው ቆየው።የወንድ ምስል ነበር። የእኔ አለም እወድሀለሁ የሚል ተፅፎበታል።ቅናት ቢጤ አንጨረጨረኝ።ቀጥሎ ያለውንም ከፈትኩት ራሱ ፎቶ በትልቁ ተስሎ ግርግዳ ላይ ከተሰቀለ ምስል ላይ የተነሳ መሆኑ ያስታውቃል።
29 አየሁት።ራሱ ልጅ ወደ ደረቱ አስጠግቶ አቅፏት የሚያሳይ ፎቶ ነው ከፊታቸው ኬክ እና ልዩ ልዩ ዲኮር ተቀምጧል።እንዲህ የሚል መግለጫ ፅሑፍ ተፅፎበታ "ሦስት አመት በፍቅር"
ማመን አልቻልኩም።
30ኛውን ምስል ከፈትኩት አባባል ነው "መታመን ለራስ ነው" ይላል።
"ቱ ቀጣፊ !" አልኩና ስልኩን አሽቀንጥሬ ወረወርኩት።
ፍቅረኛ እያለሽ ነበር እኔን ያ ሁሉ ነገር ውስጥ የከተትሽኝ? ከእሱም ጋር ከእኔም ጋር ነበርሽ? ፍቅረኛ እያለሽ ነው ከእኔ ጋር እንደዛ ስትሆኚ የነበረው? እሺ ከነገርሽኝ ውስጥ የቱ ነበር እውነት? ሰው እንዴት በእንባ እየታጠበ ውሸት ይናገራል?

እሞታለሁ ያልሽኝም ውሸት ነበር ?

አጠገቤ እንዳለች ሁሉ በንዴት ጦፌ ጥያቄዎችን አግተለተልኩ።መልስ የሚሰጥ የለም።
እንቆቅልሹን ግን ጊዜ ፈታው።እንደራሷ ግራ የገባው አደረገቺኝ ለሰው ያለኝ አመለካከት ተዛባ።


አሁን እኔ ሰው ባላምን ይፈረድብኛል ?











?

እዚህ ድረስ ስላነበብከው/ሽው ከልብ አመሰግናለሁ።

@bestletters
291 views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 20:00:14 ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንኳን ለአብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ።መልካም ጾም ይሆንላችሁ ዘንድ እየተመኘው ይሄን "ኤፍራጥስ ወንዝ" ከተሰኘ የዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ መፅሐፍ ላይ የተቀነጨበ "አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?" የሚል ፅሑፍ እጋብዛችኋለሁ።
የበረከት ጾም ይሁንልን።
"አብይ ጾምንስ እንዴት ትጾማለህ?"
ሶፊ

@bestletters
229 views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 20:14:57 "ተከራያችን "

ክፍል፦፯

ደራሲ፦ሶፊ

" ምን እያልከኝ ነበር? " አለች ወደኔ እያየች

መድገም እየቀፈፈኝ እንደምንም ስሜቴን ታግዬ..."ምን ሆነሽ ነው የጠፋሽው? " አልኳት።
"ምንም አልሆንኩም...የጠፋሁበትንም ምክንያት ደጋግሜ ነግሬህ የለ ስራ ነው።" አለችና ዝም ስትል።
ከእንግዲህ ምንም መጠየቅ ትርፉ ድካም መስሎ ተሰማኝ፤አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም።ምንም ልትነግረኝ እንዳልፈለገች ሁኔታዋ ይናገራል።
"ጨከጨኩሽ አይደል?" አልኳት። መልስ አልሰጠቺኝም።
ከቢራዬ ጎንጨት ብዬ ጥያት የመሄጃ ሀሳብ አብሰለስል ጀመር።አንዳንድ ሰዎች መሄጃ ያጣን ይመስላቸዋል።ከእናቴ ጋር እያወራሁ ባመሽ በስንት ጠሀሙ፤የሚወዱኝን ጓደኞቼን ባገኝስ...ፊልም ባይ መፅሐፍ ባነብ ብዙ የምወዳቸውን ነገሮች ማድረግ እየቻልኩ።ከማይወደኝ ጋር ምን እሰራለሁ?
ይቀየራሉ ሰዎች ይቀየራሉ ማንም ባለበት አይረጋም።አፈቀርኩህ ያለችህ የወደደችህ መስሏት ይሆናል።ግራ ገብቷት ነው ግራ ያጋባችህ። ታዲያ ስትፈልገኝ ብቻ ነው የምትነግረኝ አልፈልግህም ተብሎስ አይነገርም? የምን ሽሽት ነው? እናቴም
"ስልኳ አሁንም አሁንም ይጠራል።"
ትቆያለሽ? እኔ ትቼው የመጣሁት ስራ አለ። (በልቤ እሱ ነው የሚያዋጣኝ አልኩ።) ትጠብቀኛለች። ትንሽ እቆያለሁ አለቺኝ። አስተናጋጁን ስጠራው ተወው ስወጣ እከፍላለሁ አለች። የአለማየሁ ገላጋይን "ሐሰተኛው~በእውነት ስም" የሚለውን መፅሐፍ ከጠረቤዛው ላይ አነሳሁና...ግርምት ባልተለየሁ ፈገግታ "ሰላም እደሪ አልኳት...መልእክት እየፃፈች የስልኳ እስክሪን ላይ እንዳፈጠጠች "ሰላም እደር አለቺኝ።" ደግሜ ላያት እደማልፈልግ ልቤን እያስጠነቀኩት። "ጎንበስ ብዬ ጉንጯን ሳም አደረኳት...ይሁዳስ እንደዛ አይደል ያደረገው? ለድሮ ማንነቷ አሳልፎ ሰጠዋት ?" ማን ነው ምንን አሳልፎ የሰጠው?
እኔ ምን አደረኩ ? እሷ ናት የተቀየረችብኝ።እያልኩ እራሴን ከወቀሳ ለማዳን መሯሯጥ ጀመርኩ።
እኔንማ ገድላኛለች የምወዳትን ትቼ ከእርሷ ጋር እንደሆንኩ ታውቃለች? የማልወዳቸውን ነገሮች ለእሷ ብዬ እንደማደርግ ታውቃለች? አታውቅም!
ለእሷ ብዬ ያደረኳቸው ያ ሁሉ ነገሮች ምንም ናቸው ማለት ነው። ባዶ መና ።
እሺ እንዴት ነው...እንደዛ ቀርባ አስለምዳኝ ብቻዬን የምችለው።
ብዙ የእኔ የምላቸው ነገሮች የእርሷ ስለሆኑ...እርሷን ማጣት ማለት ራሴን ማጣት መስሎ ተሰማኝና ራሴን ጨምድዶ ያዘኝ።

" ሰው የሰጡትን ቦታ ካላወቀ ምን ይደረጋል?"

ቤት ስገባ እናቴን ሰላም ብቻ ብያት ትንሽ ራሴን እዳመመኝና ማረፍ እንደምፈልግ ነግሬያት ወደ መኝታ ክፍሌ ገብቼ...ሳስብ አደርኩ።
በመጨረሻም የመጣልኝ ሀሳብ ራሴን በሳምንት ነገሮች መጥመድ ነው።ከስራ በተጨማሪ ኦንላይን አጫጭር ትምህርቶችን መማር ጀመርኩ።
ሳልደውል እሷም ሳትደውልልኝ...ሶስት ሳምንት ሞላ በዛው ሳምንት እኔ ክፍለ ሀገር ለስራ ጉዳይ ሄድኩ 1 ወር የሚያስቆይ ስለነበር ደስ እካለኝ ነው የሄድኩት።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ወሩን ሙሉ ያለምንም እረፍት አሳለፍኩ።ደውላልኝ አታውቅም እኔም አልደወልኩላትም። ልመለስ አካባቢ እናቴ ድንገት ስለእርሷ ጠየቀችኝ ስለ እርሷ አንስታብኝ ስለማታውቅ ግራ ተጋባው። "ደውላልህ ታውቃለች" ብላ ነበር የጠየቀቺኝ።
"አዎ እማ ተደዋውለን ነበር ምነው አዲስ ነገር አለ?" ብዬ ጠየኳት ልቤ ፈራ እያለ። "አይ እንዲያው ነው" አለቺኝ ድምጿ ላይ ግን የሆነ ነገር እንዳለ ተረዳው።"ምንድነው እማ? አመማት እንዴ ?" አልኩ ይበልጥ እየተጨነኩ። "ኧረ እንዲያውም" አለች። "በጣም ትቀራረቡ ስለነበር ዝም መባባላችሁ አሳስቦኝ ነው።" ለዚህ መልስ ስለሌለኝ ዝም አልኩ። ሌላ ሌላ ነገር ስናወጋ ቆይተን ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ።ያልተዋጠልኝ ነገር አለ። ሁለት ቀን አይደለች ስሄድ እደርስበታለሁ ብዬ ተፅናናሁ።
፨፨፨፨፨የመጀመሪያው መጨረሻ፨፨፨፨፨፨፨፨
ከሁለት ቀን በኋላ ወደቤት ለመሄድ በለሊት ነበር የተነሳሁት እንደተለመደው በመስኮት በኩል ተቀምጬ ወቅቱ የአብይ ፆም በመሆኑ "ሕማማት" የሚል ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ የፃፈውን መንፈሳዊ መፅሐፍ የአምላካችንን ሕማም በሚገርም ብዕር ስለተከተበ በፍፁም ተመስጦ በአይነ ህሊና ተጉዤ..."ይሁዳ ሊሸጠው ሲያስማማ እንዴት አምላክህን አሳልፈህ ትሰጣለህ? እርሱ እኮ መምህርህ ነው እያልኩ እሞግታለሁ። አይነ ስውራንን ሲያበራ፥የተመለከቱ አይኖችህ እንዴት የአምላክህን ጌትነት ጋረዱብህ? አንካሶችይሁዳን ሲዘሉ፤ሽባ ሲተረተር ድዊያን ሲድኑ፤እንዳልተመለከትክ እግሮችህ እንዴት አምላክህን ለመክሰስ ተራመዱ እያልኩ። ወቀስኩ። በይሁዳ ውስጥ ራሴንም ወቀስኩ።መፅሐፉ ክርስቶስን ወደ ይሁዳ ለፍርድ እያንገላቱ ሲወስዱት በህሊና ወሰደኝ ጲላጦስ ፊት እያንገላቱ አቆሙት እኔን ጌታ ሆይ እያሉ የእየሩሳሌም ወዛዝርት ሲያለቅሱ ሳይ አብሬያቸው ላለቅስ ዳዳኝ...ከጲላጦስ ሄሮድስ ክርስቶስን እያንገላቱ ተቀባበሉት~በሁሉ የሚፈርድ እርሱ ላይ ይፈርዱበት ዘንድ አንዳች በደል አጡበት።ያዳናቸው ከሰሱት፤38 አመታት በደዌ ዳኛ ተይዞ የነበረው መፃጉህ ከእዚህ እስራቱ ያዳነውን አምላክ፤መላእክት ከመለኮታዊ ግርማው የተነሳ ፊቱ ስለሚያስፈራቸው በክንፍ የሚሸፈኑለትን የሚፈት የሚንቀጠቀጡለን አምላክ በጥፊ መታው።በሁሉ ላይ ለሚፈርድ ለእርሱ ፍርድን አጓደሉበት።"

በተመስጦ እያነበብኩ ቆየሁ። ልደርስ አካባቢ እናቴ ደወለች። እየመጣሁ ነው እማ አልኳት።ከሁለት ቀን በፊት የነበረው ሁኔታ አሳስቦኝ መፅሐፉን ወደ ሻንጣዬ መልሼ መብሰልሰል ጀመርኩ። ከባሱ እንደወረድኩ ታክሲ ለመያዝ ስጣደፍ አንድ የስራ ባልደረባዬ ክላክስ አድርጎ መኪናውን በእኔ አቅጣጫ ሲያቆም ተመለከትኩ።ጎንበስ ብሎ በመስኮቱ አጮልቆ እያየ "ሶፊ ወደ ሰፈር ነህ?" አለኝ። አዎ አልኩት እኔም አንገቴን በመስኮቱ አጮልቄ። እኔም ወደዚያው ነኝ ና እንሂድ አለኝ። ከፍቼ ገባው።እያወራን።ቤት አካባቢ ስንደርስ አቆመ።እንዲገባ ብለምነውም እንቢ አለኝ።ተሰናብቼው ለወሬ እየጓጓው ወደ ቤቴ አመራው የጊቡውን በር አልፎ ወደ ውስጥ ስገባ ያየውትን ማመን አቃተኝ።

ይ~ቀ~ጥ~ላ~ል።


@bestletters
227 views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 19:15:38 "ተከራያችን"

ክፍል፦፮

ደራሲ፡ሶፊ

ሰሞኑን ፀባይዋ ተቀይሮብኛል ነው ወይስ እኔ ነኝ የተቀየርኩት? እንደበፊቱ አብረን አናመሽም ወይ እኔ ወይ እሷ ስራ አምሽተን እንመጣለን።ማታ ሳንተያይ።ቀን እንዴት ነሽ ብዬ ሳልደውል የምውልባቸው ቀናትም መጡ...እንደተቀራረብነው ሳይታሰበኝ እየተራራቅን መጣን...ለሁሉም ጊዜ አለሁ ይል አይደል መፅሐፉ።እኔን ለማግኘት ምክንያት እንዳልፈለገች፤እንገናኝ ስላት ምክንያት መደርደር ጀመረች...ቢሮዋ አካባቢ ሄጄ ምሳ እንብላ ስላት "ውይ አሁን እኮ በላሁ ብዙ ስራ ስላለኝ ወዲያው ወደ ቢሮ ተመለስኩ...በቃ ማታ በጊዜ እመጣለው" ትለኛልች ግን አትመጣም።በግማሽ ልቤ የእናቴን ወግ እየሰማው፤በግማሽ ልቤ በሯ ሲከፈት ድምፅ ለመስማት ጆሮዬን እጥላለሁ... አንዳንዴ እንዲውም የእናቴን ወግ አልሰማትም ።

ምን ተፈጥሮ እንደሆነ ባልገባኝ ምክንያት ንፋስ የማያስገባ የነበረው ቅርበታችን፤ስንዝር ክፍተትን ፈጠረ ቀጥሎም ፍፁም እየተራራቅን መጣን መሀላችን ደግሞ ሁለታችንም መሻገር የከበደን ገደል ዝምታ አለ።
አንድ ቀን ቢሮ ቁጭ ብዬ እያሰብኳት ስተክዝ ይሄን ግጥም ፃፍኩላት...

ርዕስ፦ስፈልግ አጣዋት

የፍቅሬ መጠኑን ልኬቱን አስልታ
እንዳትወጣ ስታውቅ ከልቤ ውስጥ ገብታ
ኩራት አሰከራት
ማፍቀሯን አስረሳት
ፍቅሬንም ዘንግታው ልመና መሰላት
ስትፈልገኝ እንጂ ስፈልግ አጣዋት።

ምን ሆና ነው ለሚለው ጥያቄ መልስ ሳላገኝ ቀናት፣ሳምንታት ነጎደው አንድ ወር ተቆጠረ።ግራ ገባኝ...አንድ ቀን እንደምንም እንድንገናኝ አግባባዋት በፊት የምንገናኝበት መጠጥ ቤት ቀጠረቺኝ...ደነገጥኩ መጠጣት ጀመርሽ እንዴ? አልኳት። መልስ አልሰጠችኝም 12:30 እንዳታረፍድ አለችና ስልኩን ዘጋችው። አእምሮዬ ሌላ ጥያቄን ያግተለትልብኝ ጀመር።እንቆቅልሽ!
30 ደቂቃ ቀደም ብዬ ደረስኩ።እሷ 30 ደቂቃ አርፍዳ መጣች።ሌላ ሰው መስላለች ለፕሮግራም ካልሆነ በስተቀር እንዲህ ሜካፕ ስትለቀለቅ ተመልክቼ አላውቅም።ሹራብ፣ከሹራቡ በላይ ኮት፣ጥብቅ ያለ ጅንስ፣ቀይ ክፍት ሂል ጫማ...
እንዲህ ሆና አይቻት አላውቅም።ብሽቅ አልኩ ልታቅፈኝ ጎንበስ ስትል እጄን ዘረጋውላት...የእጆቿ ጥፍሮች ተንጨፋረዋል(ድሮም ጥፍር ሲረዝም ያስጠላኛል።)...የአውሬ እንጂ የሰው ጥፍር አልመስልህ አለኝ...ስንት ጎዳና ላይ እጆቿን ይዤ በኩራት እንዳልተጓዝኩ ይዞ ጥቂት መቆየት ዘገነነኝ ቆሎ ለቀቅኳት።እኔ የወደድኩትን ማንነቷን ልታጠፋ የምትታገል መስሎ ታየኝ...ልክ ከማህበረሰቡ ጋር እንደተጣላች ከእኔም ጋር ግልፅ ጦርነት የጀመረች መሰለኝ...ደግሞ እኔ ምን አደረኳት?
የቀጠለችው ዊግ ቀለሙ ቀይ ነው...አይኗን ቀይ ቀለም ተለቅልቃዋለች...ከንፈሯ ደማቅ ቀይ ሊፒስቲክ...ቀይ የጥፍር ቀለም...ሁሉንም አልወደድኩትም።ወንበሩን አስተካክላ እየተቀመጠች...ኮቷን በሁለት እጆቿ ያዝ አድርጋ "እ እንዴት ነኝ ? አላማረብኝም?" አለችኝ።እንደተናደድኩ በሚያሳብቅ ድምፀት "በእውነት ምንም አላማረብሽም! የህፃናት የስህል ደብተር መስለሻል።ምንድነው የተለቀለቅሽው? መልክሽ ምናለሽ? " ተነጫነጭኩ። በድል አድራጊነት ተመለከተቺኝ።
ምን ልጠይቃት እንደቀጠርኳት እንኳን ጠፋብኝ።
"ምን ሆነሽ ነው? "
"ምን ሆንኩ
"ይገባሻል አይደል ምንም እንደድሮው አይደለሽም።አንድ ጊቢ ሆነን አንገናኝም።ስቀጥርሽ ምክንያት ታበዣለሽ።አይመችሽም። ያደረኩሽ ነገር አለ? የእኔ ይሁን እሺ እማዬን እንኳን ሰላም ካልሻት ቆይቷል።ምንድ ነው የተፈጠረ ነገር አለ? "
ስልክ በላይ በላይ ይደወልላታል ያወራሁትን ትስማ አትስማ እንኳን አላውቅም። ልክ ስጨርስ ጠብቃ ስልኩን አነሳችው።
ስልክ ወዬ እንዴት ነህ?...እሺ...እ...እሺ...ይሆናል...አይደል...
.
.
.
.
ኧረ እየሰማሁ ነው።በፍቅር እያወራሁ ነው።
እሺ ወይ እንድዛ እናድርግ እኔ እደውላለሁ።"
አለችና አስተናጋጁ ልምዷን ስለሚያውቅ ፍቃዷን ሳይጠይቅ ያመጣውን ቢራ ግጥም አድርጋ ጠጣችና። " እያልከኝ ምን ነበር? "

መድገም እየቀፈፈኝ እንደምንም ስሜቴን ታግዬ..."ምን ሆነሽ ነው የጠፋሽው? " አልኳት።


ይ~ቀ~ጥ~ላ~ል።

50 ሲያልፍ ቀጣዩን እለቀዋለሁ።

"Someday you will wake up and ask yourself this question:
Where are the peoples i used to know?"

@bestletters
183 views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ