Get Mystery Box with random crypto!

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

የቴሌግራም ቻናል አርማ smu_gibi_gubae — ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ
የቴሌግራም ቻናል አርማ smu_gibi_gubae — ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ
የሰርጥ አድራሻ: @smu_gibi_gubae
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 696
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ማኅበረ ቅዱሳን አዲስአበባ ማዕከል የቅ/ማ/ዩ/ግ/ጉባዔ የቴሌግራም ቻናል ነው።
#በዚህ_ቻናል
👉ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ወቅታዊ መረጃዎችን ፣መዝሙሮችን ፣ትምህርታዊ ጽሁፎችን እንዲሁም ስለ ግቢጉባዔያችን መረጃዎች እና ማስታወቂያዎች ይደርሳችኋል።
ይህንን ሊንክ በመጫን ለወዳጅዎ ያጋሩ!!
👉 @smu_gibi_gubae
መልእክት፣አስተያየትና ጥያቄ ካሎት 👉@DnHaileBot ላይ ላኩልን።

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-10 20:19:03 ስልጠናው በሁለት ክፍል ባለማለቁ የመጨረሻ ክፍል 3 ስልጠና ነገ ነሐሴ 5 2014 ዓ.ም ይቀጥላል ሰዓት ከ6:00 - 7:15
ቦታ አዲሱ ቢጫ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ
111 views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 18:24:36 መግቢያና መውጫ በጀርባ በር
214 views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 18:23:12 ሰላም እንደምን ዋላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በነገው ዕለት ማለትም ነሐሴ 4(ዕሮብ) የአብነት ት/ት ጥናት ሰለሚቀጥል ከ6-7 በመገኘት እንድንማር ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ያልሰሙ እኅት ወንድሞቻችሁንም ወደ ግቢ ጉባኤያችን እንድትጋብዙ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ሠናይ ምሽት ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን!
ፀልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን !

ቦታ አዲሱ ቢጫ ህንጻ 4ተኛ ፎቅ ላይ ነው

ይህን መልዕክት ላልሰሙ ጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉላቸው
217 views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 17:00:38 ሰላም እንደምን ዋላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በነገው ዕለት (ማክሰኞ ) የኮርስ መርሐ ግብር ሰለሚቀጥል ከ6-7 በመገኘት እንድንማር ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን እንዲሁም ያልሰሙ እኅት ወንድሞቻችሁን ወደ ግቢ ጉባኤያችን እንድትጋብዙ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
መልካም የጾም ጊዜ
ፀልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን !



ቦታ 1. አዲሱ ህንጻ 4ተኛ ፎቅ ትንሹ ክፍል(2014 ባች)
2.አዲሱ ህንጻ 4ተኛ ፎቅ ትልቁ አዳራሽ (2013 ባች)
መግቢያና መውጫ በጀርባ በር (ቅዳሴ ስላለ)
236 views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 12:16:14 የሁለተኛ ዓመት ትምህርት ወደ አዲሱ ህንጻ 4ተኛ ዞሯል
229 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 21:00:16 ሰላም እንደምን ዋላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በነገው ዕለት (ሰኞ) የኮርስ መርሐ ግብር ሰለሚቀጥል ከ6-7 በመገኘት እንድንማር ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን እንዲሁም ያልሰሙ እኅት ወንድሞቻችሁን ወደ ግቢ ጉባኤያችን እንድትጋብዙ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ሠናይ ዕለተ ሰንበት



ቦታ 1.አዲሱ ህንጻ 4ተኛ ፎቅ(አንደኛ ዓመት 2014 ባች)
2. ጭቃው አዳራሽ(ሁለተኛ ዓመት 2013 ባች)
255 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 16:10:04 ሰአ(ዓ)ሊ ለነ ቅድስት

በቸርነቱ ብዛት በአንቺ ምልጃ ኃጢአታችንን ከሚያሥተሰርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፤ ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን፤ አዕምሮውን ጥበቡን ለብዎውን በልቡናችን ሳይልን አሳድሪልን። 'ለነ' ለእኛ ጥቅም ነውና። ሳይብን አሳድሪብን ሰ(ዓ)አሊ ብነ ቢሆን ነበር።

ቅድስት አለ፦ ንጽሕት ፣ ጽንዕት፣ ክብርት ልዩ ሲል ነው።

ንጽሕትም አለ፦ ሌሎች ሴቶች ከገቢር ቢነጹ ከነቢብ ከሀልዮ አይነጹም። ከነቢብ ቢነጹ ከገቢር ከሀልዮ አይነጹም። ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሀልዮ አይነጹም። እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር ከሀልዮም ንጽሕት ናትና።
"ወኢረኲሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በህሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ" እንዲል።

ጽንዕትም አለ፦ ሌሎች ሴቶች በድንግልና ቢጸኑ ለጊዜው ነው። በኋላ ግን ተፈትሖ ያገኛቸዋል። እርሷ ግን ቅድመ ጸኒስ፤ ጊዜ ጸኒስ፤ ድኅረ ጸኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፤ ጊዜ ወሊድ፤ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት ናትና።

ክብርትም አለ፦ ሌሎች ሴቶችን ብናከብራቸው ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ ጳጳሳትን፣ ነገሥታትን፣ ነቢያትን ሐዋርያትን ወለዱ ብለን ነው። እርሷን ግን ወላዲተ አምላክ ብለን ነውና።

ልዩም አለ፦ እናትነትን ከድንግልና፤ ድንግልናን ከእናትነት አስተባብራ የምትገኝ ከእመቤታችን በስተቀር ሌላ ሴት የለችምና።

ሰዓሊ ለነ ቅድስት
ዐይኑ 'ዓ' ቢሆን አዕምሮውን (እውቀቱን)፤ ለብዎውን ( ያወቅነውን ማስተዋሉን)፤ ጥበቡን (በተገቢው ጊዜ፣ ቦታና ሁኔታ በሕይወት መተርጎሙን) በልቡናችን ሳይልን አሳድሪልን።

ሰአሊ ለነ ቅድስት

አልፋው 'አ' ቢሆን፦ ለምኝልን ማለት ነው። ልመናስ በወዲያኛው ዓለም እንኳንስ በእሷ በሌሎችም ቅዱሳን የለባቸውም በቀድሞ ልመናዋ የምታስምር ስለሆነ እንዲህ አለ እንጂ።

'ሰአ(ዓ)ሊ ለነ ቅድስ'ን ማን ተናግሮታል ቢሉ፦
ቅዱስ ኤፍሬም ተናግሮታል። ይህማ እንዳይሆን በግብጻውያን በመጽሐፋቸውም በቃላቸውም አይገኝምሳ ብሎ ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መክፈያ ተናግሮታል። ቅዱስ ያሬድስ ከየት አምጥቶ ከሰው መጽሐፍ አስገብቶታል ተናግሮታል? ቢሉ፦ 'ሰአሊ'ን 'ሰአሊ ለነ ሀበ ወልድኪ ኄር መድኀኒነ' ካለው 'ቅድስት'ን 'ኦ ድንግል ኦ ቅድስት' ካለው አምጥቶ አስገብቶታል ተናግሮታል።
አንድም የኋላ ሊቃውን ተናግረውታል ይላሉ።

ይሄን ሲጨርስ በያዘችው መስቀለ ብርሃን ባርካው ታርጋለች። እርሱም ተባርኮ እጅ ነስቶ ይቀራል። በነገው እለት ትመጣለች።

"ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በእለተ..."
ይህ ጉባኤ ነው። ይቆየን!
አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮ ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን!

ነሐሴ 1/2014 ዓ.ም

Hailat ze Dingil ሥመ ጥምቀቱ ወልደ ሐና በጸሎታችሁ አስቡኝ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ ቤ/ክ ትምህርቶች ይተላለፉበታል።
" አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤"
(2ኛጢሞ 3፥14)
ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት
@DnHaile ወይም
@DnHaileBot ላይ ያስቀምጡልን
123 views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 17:36:58
261 views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 17:36:28 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳን ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ለሆነው ጾመ ፍልሰታ በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ።
በቅድስት ቤተክርስቲያናችን የአዋጅ ጾም የሚባሉት ሰባት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
1. ✣ ዐቢይ ጾም (ጾመ ኩዳዴ)
2. ✣ ጾመ ድኅነት (የረቡዕና ዐርብ)
3. ✣ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም)
4. ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)
5. ጾመ ነነዌ
6. ጾመ ጋድ
7. ጾመ ፍልሰታ

ጾመ ፍልሰታ
ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገን፤ ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የምንጾመው ታላቅ ጾም ነው።
(ጾመ ፍልሰታ) ፍልሰታ ፆም(ጾመ ለማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር የፍልሰታ ፆም ከነሐሴ 1 እስከ 15 ነው ቤተ ክርስትያናችን እደምትገለፀው "እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌቴሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል በ8ወር በነሀሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል በዚህ የቀብር ስነስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ እየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት እየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር አላቸው ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ"እመቤታችን ተነስታ አርጋለች ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን (ሰበኗን) አሳያቸው

ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታትነዋል በዓመቱ ትንሳዬሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን ብለው ከነሀሴ 1 ጀምሮ ሱባዬ ገቡ በነሀሴ14ቀንም ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው ከቀበሯትም በጟላ በነሀሴ16 ተነስታለች በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስትያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህች ጊዜ ትፆማለች

የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
267 views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 12:36:03 የመዝሙር ጥናት ወደ ጭቃው አዳራሽ ተቀይሯል
244 views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ