Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ህይወት ቃል... 1ኛ ዮሐንስ 1:1

የቴሌግራም ቻናል አርማ slehiywet — ስለ ህይወት ቃል... 1ኛ ዮሐንስ 1:1
የቴሌግራም ቻናል አርማ slehiywet — ስለ ህይወት ቃል... 1ኛ ዮሐንስ 1:1
የሰርጥ አድራሻ: @slehiywet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.22K
የሰርጥ መግለጫ

1ኛ ዮሐንስ
1 ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመርያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤
2 ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ህይወት እናወራችኋለን፤
#creater 👉 @Beki_Christian

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-05 08:29:37 ለመልካም ስራ ስትነሳ ሁሌ አንድ ነገር እራስህን ጠይቅ
ሀሳቡ ከልቤ የመነጨ ነው ወይስ ከሰው ዘንድ ከበሬታን ፈልጌ?
ሰዎች መልካም እንዲሏችሁ ከሆነ
1. በመጀመሪያ ከሰማያዊ በረከት ተካፋይ አትሆኑም ምክንያቱም ክፍያችሁን ከሰዎች አግኝታችኋል
2. መነሻችሁ እራሱ ከሰው ምስጋናን ለማትረፍ ነው እንጂ ከልባችሁ ስላልሆነ ራስ ወዳድ ያስብላችኋል
3. ሰው የማያያችሁ ቦታ ላይ ስትሆኑ መልካም አታደርጉም።

ወዳጆቼ ፍቅራችን ያለ ግብዝነት ይሁን። የሰውን ሙገሳ የለመደ በዛው አፋቸው መርዝ ሲረጭበት ሚገባበት ይጠፋዋል
ሁልጊዜ መልካምነታችን እንዳይቆም ጥሪያችንም በክርስቶስ ሆነን ይኸንኑ ለማድረግ ነውና።


“እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።”
— ኤፌሶን 2፥10

@slehiywet
598 viewsedited  05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:36:37 #ቁጥር_አንድ

ድንቅ ታሪክ አዳምጡት

@slehiywet
708 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 15:56:32 አስተውላችሁ ከሆነ ከእግዚአብሔር የምናገኛቸው ነገሮች ሁሉም ነፃ ናቸው።
ፀሀይ፣ ዝናብ፣ አየር...
አያችሁ የዘላለም ህይወት ና ፅድቅም ከእግዚአብሔር ስለሆኑ የምናገኛቸውም በነፃ ነው። ከእኛ ምንም ክፍያ አያስፈልግም!

@slehiywet
959 views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 08:31:25 ጌታ ሆይ በፊትህ እንደሚገባ እንድንመላለስ እርዳን። ወደ አንተ በመጠጋት ይበልጥኑ በህልውናህና በአብሮነትህ መኖር ይሁንልን። አንተን በማወቅ ባርከን። በምሕረትህ እና በቸርትህ መኖር ይሁንልን። "መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው" ተብሎ እንደተፃፈ በአንተ መኖር ይሁንልን። በአንተ ስንኖር ሰላም፣ እረፍት፣ ፍሰሀ፣ እምነት፣ ደስታ፣ ትግስት፣ ትህትና ፣ፍቅር ፣ተስፋን የመንፈስ ፍሬን አናፈራለንና ከግንዱ ጋር መጣበቅ ይሁንልን። ቀልባችንን አንተው ውሰደው። በእድሜያችን ጠዋት ይህ የዘላለም ህይወት መንገድ የሆንከውን ኢየሱስ በማወቅ ነፍሳችንን ከመቅበዝበዝ ስለመለስካት እናመሰግንሃለን ።

@slehiywet
@slehiywet
1.3K views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 22:59:11 የኢየሱስ ወታደር መሆናችን ከሌሎች ወታደሮች ለየት የሚያደርገን ሰውን ምንማርከው በጠመንጃ ሳይሆን በፍቅር ና በየምስራች ቃል መሆኑ ነው።

@slehiywet
759 views19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 19:43:39 ምን አጣችሁ?
ገንዘብ?
ጤና?
ጓደኛ?
ስራ?
ትዳር?
ልጅ?
ክብር?

ምን አላችሁ?
እዚህ ጋ አንድ መስፈርት ብቻ ነው ሚያስፈልጋችሁ እሱም ኢየሱስ የሚል ነው።
እሱ ካላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ
እሱ ሳይኖር ሌላው ቢኖራችሁ ግን ከሰራችሁ።

ኢየሱስ ይኑረን።

@slehiywet
741 views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 16:46:42 ሰዎችን ከማገልገልህ በፊት፣ #መድረክ ላይ ከመቆምህ በፊትህ፣ #ከመፀለይህ በፊት፣ #ከመምከርህ በፊት፣ #ወንጌል ከመናገርህ በፊት፣ #መንፈሳዊ ስራን ለመስራት ቢሮ ከመግባትህ በፊት፣ #ለመምከር ሆነ ለመገሰፅ ከመነሳትህ በፊት፣ #ከመፃፍህ በፊት፣ #ከወንድሞችህ ጋር አብረህ ከመሰባሰብህና ከመጨዋወትህ በፊት፣ #ስጦታን ከመስጠትህ በፊት #ከሁሉ በፊት ቆም ብለህ #ልብህን መዝነው፣ በውስጥህ #ፍቅር ከሌለህ ምንም አታድርግ #ኢየሱስ ከፍቅር ውጪ ምንም አድርጎ አያውቅም እኛንም ምንም እንድናደርግ አይፈልግም


@slehiywet
868 views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 09:40:20 ኢየሱስ ከሞት የሚያድነው
ኢየሱስ ያድናል እንዲባል ሳይሆን
እኛ እንድንድን ና እርሱ አዳኝ ስለሆነ ነው።

@slehiywet
818 views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:29:06 #አዲስ_ነገር

አነጋጋሪ የነበረው የዘማሪ ሳሙኤል አበበ ነገር መፍትሔ ያገኘ ይመስላል....

" ቤተክርስቲያን እና ህዝቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ " ዘማሪ ሳሙኤል አበበ

ሙሉ መረጃውን በAudio ተያይዞል ይመልከቱ።
442 views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:21:08 እግዚአብሔር ይመስገን
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር በፍጥነት ይመልሳል።

ወንድማችን ቢመለስም ባይመለስም ምክሩ ግን የሁላችንም ነው። በነፋስ አንወሰድ!
428 views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ