Get Mystery Box with random crypto!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሮም እየተካሄደ ባለው የልማት እና የፍልሰት ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተ | Skyline media

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሮም እየተካሄደ ባለው የልማት እና የፍልሰት ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጣልያን ሮም እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የልማት እና የፍልሰት ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፉ ነው።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ካላት ስትራቴጂካዊ አቅም አንጻር የስደት ምንጭ መሸጋገሪያ እና መድረሻ መሆኗ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ የስደት አስተዳደርን ለማጎልበት፣ ሕገ ወጥ ስደትን እና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመፍታት በርካታ የፖሊሲ፣ የሕግ እና ተቋማዊ እርምጃዎችን መወሰዷን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡