Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ የባህር ሃይል ያሰለጠናቸውን ባህረኞች እያስመረቀ ነው የኢትዮጵያ የባህር ሃይል | Skyline media

የኢትዮጵያ የባህር ሃይል ያሰለጠናቸውን ባህረኞች እያስመረቀ ነው

የኢትዮጵያ የባህር ሃይል በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን ባህረኞች እያስመረቀ ነው።

በመርሃግብሩ የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ፣ ጀነራል መኮንኖች፣ የነባር ባህር ሃይል አባላት፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና የተለያዩ አገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የኢፌዴሪ አየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ከ30 አመት በላይ ተገለው እና አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ጀልባዎችን ዘመኑ የሚጠይቀውን የፈጣን ተዋጊ ጀልባ ቴክኖሎጂ እና መሳሪያዎች በመግጠም ለግዳጅ ዝግጁ ማድረግ መቻሉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።