Get Mystery Box with random crypto!

ኤርትራ ከኢትዮጵያ እና ከጅቡቲ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች ኤርትራ ከኢትዮጵያ እና ጅቡቲ | Skyline media

ኤርትራ ከኢትዮጵያ እና ከጅቡቲ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች

ኤርትራ ከኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ጋር የሚያገናኟትን አካባቢዎች ዘግታለች ሲል የብሪታንያ መንግስት ማስታወቁን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል። በኤርትራ የሚገኙ የታላቋ ብሪታንያ አካል የሆኑ ሀገራት ዜጎችም ሀገሪቱን ለቅቀዉ እንዲወጡ አሳስቧል።

ኤርትራ ድንበሯን የዘጋችበትን ምክኒያት ያላሳወቀዉ የብሪታንያ መንግስት ፤ ከሱዳን ጋር የሚያዋስናት ድንበር ክፍት መሆኑን እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚደረግበት እንደሆነ ገልጿል።

ኦም ሀጀር የተሰኘዉ እና ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያዋስነዉ ቦታ ከተዘጉት አካባቢዎች አንዱ ሲሆን በሰሜኑ ጦርነት ወቅትም ሆነ ከጦርነቱ በኋላ ክፍት የነበረ መሆኑ ይታወቃል። የብሪታንያ መንግስት እንዳስታወቀዉ ከሆነ ግን ኤርትራ በዚሁ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ጨምሮ በባድመ እና አዲ ክዋህላ የተሰኙ አዋሳኝ ቦታዎችም ዘግታለች ብሏል።

የብሪታንያ መንግስት ዜጎቹ ከኤርትራ ድንበር 25 ኪሎሜትር ርቀት ባላቸዉ ማንኛቸዉም አካባቢዎች እንዳይንቀሳቀሱ መክሯል። በኤርትራ የሚገኙ ዜጎቹም ሀገሪቱን በአፋጣኝ ለቅቀዉ እንዲወጡ ፤ ወደ ሀገሪቱ ለመጓዝ ያሰቡም ጉዟቸዉን እንዳያደርጉ መምከሩን ዳጉ ጆርናል ከመግለጫው ተመልክቷል።

የብሪታንያ መንግስት ክልከላዉን ለማድረጉ ያስቀመጠው ምክኒያት ባይኖርም በኤርትራ ግን የሽብር ጥቃት ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋት እንደሌለዉ ባወጣዉ መግለጫ ተናግሯል።