Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተወሰኑ ተቋማት አገልግሎቶችን ለግል ተቋማት በውክልና አስተላልፎ | Skyline media

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተወሰኑ ተቋማት አገልግሎቶችን ለግል ተቋማት በውክልና አስተላልፎ ሊያሰራ ነው  

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ መስሪያ ቤቶች፤ የተወሰኑ ስራዎቻቸውን በውክልና ለግል ተቋማት አስተላልፈው (outsource) ሊያሰሩ ነው። በዚህ አሰራር ምክንያት ከስራቸው የሚነሱ የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞችን ወደ ሌሎች መስሪያ ቤቶች ለማዘዋወር እና “በሚፈልጉበት የስራ መስክ” እንዲሰማሩ ለመደገፍ መታሰቡም ተገልጿል።

አዲሱን አሰራር ተግባራዊ የማድረግ ሂደትን እየመራ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ነው። በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ መስሪያ ቤቶችን የአገልግሎት አሰጣጥ የመከታተል ኃላፊነት ያለበት ይህ ቢሮ፤ አዳዲስ አሰራሮችን የመዘርጋት ስልጣንም በአዋጅ ተሰጥቶታል። ቢሮው የተወሰኑ የመንግስት ስራዎችን ወደ ግል ተቋማት የማስተላለፍ እቅዱን በተመለከተ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ካሉ መስሪያ ቤቶች ጋር ዛሬ ሰኞ ግንቦት 21፤ 2015 ዓ.ም ውይይት አድርጓል።

ይህንን አሰራር በቅድሚያ እንዲጀምሩ በጥናቱ የተለዩ የከተማ አስተዳደሩ አምስት መስሪያ ቤቶች እና ስድስት ሆስፒታሎች መሆናቸው  በዛሬው ውይይት ላይ ተጠቅሷል። በቅድሚያ ወደ ተግባር ይገባሉ የተባሉት የንግድ፣ ትራንስፖርት፣ ገቢዎች እንዲሁም የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮዎች እና የአሽከርካሪ፣ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ናቸው። በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ውስጥ ያሉት የካቲት 12፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ፣ ዳግማዊ ሚኒሊክ፣ ዘውዲቱ፣ ጋንዲ መታሰቢያ እና ራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታሎች የተወሰኑ አገልግሎታቸውን ለግል አካላት ከሚያስተላልፉት ውስጥ ተመድበዋል።
ዝርዝር https://ethiopiainsider.com/2023/11062/