Get Mystery Box with random crypto!

የአርቲስት ሒሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር የፊታችን ሰኞ ይፈጸማል *********************** | Skyline media

የአርቲስት ሒሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር የፊታችን ሰኞ ይፈጸማል
*****************************

የአርቲስት ሒሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር ከነገ በስቲያ ጉለሌ በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር እንደሚፈጸም የቀብር ስነ ስርዓት አስፈጻሚ ኮሚቴው ገለጸ።

ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ፣ የሒሩት በቀለ አስከሬን የፊታችን ሰኞ ሻላ መናፈሻ ጀርባ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ሽኝት ከተደረገለት በኋላ ወደ ወዳጅነት አደባባይ እንደሚያመራ ገልጿል።

በወዳጅነት አደባባይ በሚኖረው መርሐ-ግብር በመሰረተ ክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያን አማካኝነት የፀሎት ስነ ስርዓት፣የአበባ ማስቀመጥና የታዋቂ ሰዎች ንግግር እንደሚደረግ ኢዜአ ዘግቧል።

በመጨረሻም፣ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጉለሌ በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ስርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸም ኮሚቴው አስታውቋል።