Get Mystery Box with random crypto!

ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ!         የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር  | Skyline media

ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ!
       
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር  ከነሐሴ 26/ 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም  ባለው ጊዜ ውስጥ  መስፈርቱን የሚያሟሉ  ወጣቶችን መልምሎ በመደበኛ ሰራዊትና በእጩ መኮነንነት በማሰልጠን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል ማድርግ ይፈልጋል ፤

የመመልመያ መስፈርቶች ፦

1. ህገ- መንግስቱን የተቀበለ/ች ለዚህ በፅናት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች

2. በብሔር-ብሔረሰቦችን እኩልነት የሚያምን /የምታምን

3. ከአሁን በፊት የፖሊስ ወይም የመከላከያ አባል ያልነበረ/ች

4. ከወንጀል ነፃ የሆነ የፍርድ ቤት ቀጠሮና ክርክር የሌለበት/ባት

5. ከማንኛውም ሱስና አጉል ልማድ የፀዳ/ች እና ሙሉ ጤንነት ያለው/ያላት

6. በመከላከያ ለ7 ዓመት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች በማንኛውም ቦታ ተመድቦ መስራት የሚችል/የምትችል

7. ፆታ፡- አይለይም

8. ኢትዮጵያዊ የሆነ/ች በሚኖርበት ቀበሌ 2 ዓመት የኖረ/ች

9. ዕድሜ፡- ከ18-25 አመት ፤ ቁመት ለወንድ 1.60 እና ከዚያ በላይ ፣ ለሴት ደግሞ 1.55 እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች

10. ክብደት፡-ለወንድ ከ50-75 ኪ.ግ የሆነ ለሴት ደግሞ 45-66 ኪሎግራም የሆነች፣

11. የትምህርት ማስረጃ፦ ለወንድ 6ኛ ክፍል ያጠናቀቀ እና ለሴት እወቅና ካለው የትምህርት ተቋም ዲፕሎማ ወይም በሌቭል ያጠናቀቁ እና ከዚያ በላይ የሆኑ የ 8ኛ ክፍል የሚኒስቲሪ ካርድ ማቅርብ የሚችሉ ፣

12. ያላገባ/ችና ያልወለደ/ች

13. ደመወዝ በመከላከያ ስኬል መሰረት ሆኖ ጥቅማጥቅም የመኖሪያ ቤትና ህክምና አገልግሎት በነፃ የሚያገኙ  ሲሆን በመከላከያ ዕቅድና ፍላጎት መሰረት በትምህርት ተቋም ገብተው የመማር ዕድል አላቸው፣

14. የምዝገባ ቦታ ፦ በሁሉም የክልል ከተሞች የፀጥታ ተቋማት ቢሮ( ሚሊሻ ፤ ፖሊስ ፤ ሰላምና ደህንነት ቢሮዎች )

15. የምዝገባ ቀን፡-  ከነሐሴ 26/2014 ዓ/ም ጀምሮ   አስከ መስከረም 10/2015 ዓ/ም  ዘወትር በሥራ ስዓት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ

ማሳሰቢያ፡- በምዝገባ ወቅት መቅረብ የሚገባቸው ማስረጃዎች የቀበሌና የፖሊስ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የትምህርት ማስረጃ ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የቀበሌ መታወቂያ በዘመኑ የታደሰ ያስፈልጋል።

https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777