Get Mystery Box with random crypto!

ማስራብ›› የአሸባሪው ህወሓት የትግል ስልት አሸባሪው ህወሓት ከወራት በፊት ወደ  አፋርና አማራ | Skyline media

ማስራብ›› የአሸባሪው ህወሓት የትግል ስልት

አሸባሪው ህወሓት ከወራት በፊት ወደ  አፋርና አማራ ክልል ያደረገው ወረራ ተቀልብሶ በመቀሌ ከመሸገ ወዲህ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚላከውን የእርዳታ እህል ከዜጎች በመንጠቅ ለቀጣይ ግዳጅ የመለመላቸውን ታጣቂዎች ሲቀልብ የከረመ ሲሆን፤ በዚህም የተነሳ ሕዝቡ  በከፋ ረሐብ እየማቀቀ ይገኛል፤ መከራውም በዝቷል፡፡

ደብረጽንም በቅርቡ በውጭ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር በዙም ያደረገውና አፈትልኮ በወጣው ምስጢራዊ ውይይት ‹‹በቂ የሰብአዊ አቅርቦት ካለ የትግራይ ሕዝብ አሁንም ለምን በችግር ይማቅቃል፤ የእርዳታ እህል ለታጣቂዎች ታከፋፍላላችሁ የሚባለው እውነት ነው?›› የሚል ጥያቄ ቀርቦለት በሰጠው ምላሽ ‹‹አዎ የእርዳታ እህል ለታጣቂዎች እናከፋፍላለን፡፡ ታዲያ ምን እንቀልባቸው፡፡ ሰው ሳይበላ አይዋጋም፡፡ ጦርነት አይቀሬ ነው፡፡ ከጦርነት ውጪ አማራጭ የለንም፡፡ ህጻናትም አዛውንትም በግንባር ይሰለፋሉ፡፡›› በማለት ምላሽ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

ታዲያ ቃል በተግባር እንዲሉ፤ ሕዝብን ሆን ብሎ በማስራብ፤ ቁጭ ብለህ ከምትራብ ደግሞ ዝመት የሚል ስልት በመጠቀም ህጻናትና አዛውንትን ሳይቀር በጦርነት እየማገዱ የሚገኙት የአሸባሪው ቡድን መሪዎች ዛሬም ወረራውን ከማስፋት አልተቆጠቡም፡፡ ትናንት ምንም ውጤት ያላስገኘውን ጦርነት በመድገምም ሕዝብን ለከፋ ሰቆቃና ረሐብ እየዳረጉ ነውና ሕዝቡም በቃችሁ ሊላቸው ይገባል፡፡