Get Mystery Box with random crypto!

12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት | Skyline media

12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ፈቀደ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል።

በአዲስ ክልል እንዲደራጁ ምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳብ ተቀብሎ የወሰነላቸውም የዎላይታ ዞን፣ የጋሞ ዞን፣ የጎፋ ዞን፣ የደቡብ ኦሞ ዞን፣ የጌዴኦ ዞን፣ የኮንሶ ዞን፣ እንዲሁም የደራሼ ልዩ ወረዳ፣ የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ የቡርጂ ልዩ ወረዳ፣ የአሌ ልዩ ወረዳ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ መሆናቸው ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ቀሪዎቹ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር የሚገኙ የሀድያ ዞን፣ ሀላባ ዞን፣ ከንባታ ጠንባሮ ዞን፣ ጉራጌ ዞን ስልጤ ዞን እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ ክልል እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።