Get Mystery Box with random crypto!

Addis Brand Bonda Collections: አዲስ ቦንዳ

የቴሌግራም ቻናል አርማ sinqneh — Addis Brand Bonda Collections: አዲስ ቦንዳ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ sinqneh — Addis Brand Bonda Collections: አዲስ ቦንዳ
የሰርጥ አድራሻ: @sinqneh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 186
የሰርጥ መግለጫ

📌ለእርሶ የሚሆኑ ኦርጅናል አልባሳት👕👖👗👚👜፣ጫማዎች👞👟👠👢፣ የመዋቢያ እቃዎችወ.ዘ.ተ⌚👓🎸አሉን።
ይደውሉ ☎ 📞📲 090 4654118
Inbox @addissbonda
❤️❤️❤️ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁ ሼር በማድረግ የዚህ ቻናል አባል ያድርጓቸው!!!

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-02-26 21:03:56 ወገን ከሥልጣን የተነሱ ወይም የሚቀነሱ አመራሮች መጪውን ጊዜ በግልጽ ሲነግሩህ ‹‹ለምን አሁን ተናገሩ?›› ብለህ በማናናቅ ፈንታ ‹‹ለምን ተባረሩ?›› ብለህ ጠይቅ፡፡
ምክንያቱም ያለንበት ወቅት የአማራን ሕዝብ ማጥፋት የሚሹ ሃይሎች ሥልጣን የያዙበትና የእኒህን ሃይሎች ዙፋን ማስቀጠል የሚሻ ድርጅት የተሸከምንበት በመሆኑ ከአመራርነት የሚያስባርረው ሙሠኞችን መዋጋት እንጂ ሙሥና መብላት ሊሆን አይችልም፡፡ የሕዝብ ተቆርቋሪ እና የወገን ጠባቂ ሆኖ መገኘት ካልሆነ በቀር ሕዝብን ለጥቃት ዳርጎ የቤተሰብን ምቾት ማረጋገጥ ከሹመት የሚያስነሳ አይሆንም፡፡

➔ከበላይ አካል አንድ ትዕዛዝ ሲመጣ ‹‹ታዛዥ ነኝ›› በማለት ፈንታ ‹‹ተቃውሞ አለኝ›› ያልክ ቀን ግን ገሸሽ ትደረጋለህ፡፡
➔የምትመራውን ሕዝብ ለጉዳት የሚዳርግ እቅድ ሲሰጥህ ‹‹ጠቃሚ ነው›› በማለት ፈንታ ‹‹አውዳሚ ነው›› ያልክ ቀን ጥርስ ውስጥ ትገባለህ፡፡

➔የሚሰጥህን ተልዕኮ ያለ ምንም ጥያቄ ተቀብለህ ሕዝብህ ላይ እየጫንክ ከርስህን እና ኪስህን ከመሙላት ይልቅ የኅሊናህ ተገዥ ሆነህ መቃወምና መጠየቅ የጀመርክ እለት ከጎናቸው ፈቀቅ ትደረጋለህ፡፡

ይሄን ስልህ ግን የሚሰናበተው አመራር ሁሉ ጤነኛ ነው እያልኩህ አይደለም፡፡ በተለያዩ የሥልጣን ሽኩቻዎችና በጥቅም ቅራኔዎች የሚባረሩ ብዙ ጥቅመኞችን ጎጠኞች ይኖራሉ፡፡

በብአዴን መዋቅር ውስጥ ከጎጠኝነት በላይ አማራዊ ስሜት፣ ከተላላኪነት ይልቅ እንቢተኝነት፣ ከአድፋጭነት ይልቅ ተሟጋችነት ከሥልጣን ያስባርራል ማለቴ እንጂ…

አማራን ለማጥፋት ከሚሹ አሸባሪዎች ጋር አብረው ሲሠሩ ከተገኙ ቅጥረኞች በላይ ‹‹ፋኖ ይክስም፣ ልዩ ሃይሉ ይዳከም›› የሚል ትዕዛዝ ሲተላለፍ ‹‹አይሆንም›› ብለው የሚቃወሙ አመራሮች በአሽከሮች ፊርማ ይባረራሉ ማለቴ እንጂ…

ከዚህ ባለፈ ደግሞ…
በሥልጣኑ ሲባልግና ሢሞስን ተገኝቶ በጥፋቱ የተባረረ ወይም ደግሞ ከመናኛ ወንበር ላይ የተወረወረ አመራር ባለመታሰሩ አምላኩን እያመሰገነ አርፎ ይቀመጣል እንጂ ደረቱን ነፍቶ ከሥልጣኑ የተነሳበትን ምክንያትና ባንተ ላይ የተደቀነውን ስጋት አይነግርህም፡፡

በተረፈ ለአንድ ቀን ደፈር ብለው ሐቅን የተናገሩና ጠቃሚ ነገር የሠሩ ብሎም በሕዝብ ዘንድ ትንሽ ሥም ያፈሩ ከዙፋኑ ገሸሽ ሲደረጉ….ለመጣ ለሄደው ‹‹እሺ›› እያሉ ሕዝባቸውንና ኅሊናቸውን የሚሸጡት ግን ወንበሩ ላይ ለሽሽ ብለው ታገኛቸዋለህ፡፡
114 views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 20:53:44 #ASTU #AASTU

ሁለቱ የኢትዮጵያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስገባ ነጥብ ያዝመዘገቡ ተማሪዎችን ለመቀበል በዛሬው ዕለት ጥሪ አቅርበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ አውጥተዋል።

የመመዝገቢያ መስፈርቱ የሲቪክስ ትምህርትን ሳይጨምር የስድስት ትምህርት ድምር ውጤት ከዚህ በታች እንደተገለፀው ነው።

• ለታዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤ/ጉሙዝ ፣ ጋምቤላ) ፦

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 395 ለሴት 390
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 385 ለሴት 380

• ለሌሎች ክልሎች ፦

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 400 ለሴት 395
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 390 ለሴት 385

የምዝገባ ጊዜው ከየካቲት 21 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ሲሆን ምዝገባው የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል ተብሏል።

ከላይ የተቀመጠውን የምዝገባ መስፈርት የሚያሟሉ ተማሪዎች በማንኛውም ስፍራ ሆነው በኢንተርኔት www.aastu.edu.et እና www.astu.edu.et ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

ፈተናው መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚሰጥ ተነግሯል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@sinqneh
86 views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-22 16:41:37 ደስታ እና ነፃነት የሚመነጨው አንዳንድ ነገሮች በቁጥጥራችን ስር፤ አንዳንድ ነገሮች ደግሞ ከቁጥጥራችን ውጭ መሆናቸውን በግልፅ ከመረዳት ነው!
-- Epictetus --


JOIN US
@sinqneh
75 views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 22:41:31 ከለውጥ ይለቅ ባሉበት መቆየት ቀላል ነው፤ ነገር ግን አንዴ መለወጥ ከጀመርን፤ ምን እንዳቆየን ራሱ ማስታወስ ከባድ ነው!
-- Susan Sontag --

JOIN US
@sinqneh
62 views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 18:50:33 ብቸኝነት የሚመጣው በዙሪያችን ሰዎች ባለመኖራቸው ሰይሆን ለራሳችን ጠቃሚ ከሆኑ ነገሮች ወይም በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት አይኖራቸውም ብለን ከያዝናቸው ሃሳቦቻችን ጋር መግባባት ባለመቻል ነው!
-- Carl Jung --

JOIN US
61 views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-21 00:52:32 ሁልጊዜም የሌሎችን እንከን የሚፈልጉ ሰዎች፤ ተመሳሳይ ናቸው። የራሳቸውን ለመመልከት ዓይን የላቸውም !
-

JOIN US
60 views21:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 20:35:35 ቀን እስኪያልፍ ያባቴ ባሪያ ያግባኝ
66 views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-12 08:40:08 ለባለጌ ገድሉ ውርደቱ
79 views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-11 08:31:59 አንተ ነህ ባለ ...
82 views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-10 18:47:31 ተተናገረ አያባራ አፋቸው ከያዘ አይለቅ እጃቸው
79 views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ