Get Mystery Box with random crypto!

*ከመረጥሁት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ*። መዝሙረ ዳዊት 89 : 3 *በዚህች ዕለት እግዚአብሔር | ስንክሳር በየቀኑ

*ከመረጥሁት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ*።
መዝሙረ ዳዊት 89 : 3

*በዚህች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ ለእናትነት ለመረጣት ለንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም የገባላትን የምህረት ቃል ኪዳን እንዘክራለን። በእውነቱ እመብርሃንን ስለተቀበለችው ፍጹም ቃል ኪዳን በየወሩ 16ኛ ቀን ኪዳነ ምህረት ብለን በቅድስት ቤተክርስቲያን በክብር እንዘክራታለን።*

*እውነት ነው እግዚአብሔር አምላካችን ቃል ኪዳን የገባው ለመረጣቸው ብቻ ነው። የኪዳነ ምህረት መመ ረጥ ደግሞ ልዩ ነው: ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ብሎ እንደዘመረላት፦*

*እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦*

*ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።*
    መዝ 131(132)

*እንግዲህ የምህረት ቃል ኪዳንን ታላቅ እውነት እንረዳና እንጠቀምበት ዘንድ ከዚህ በታች ያለውን ምንባብ ከልባችን በማንበብ እንድንገነዘበው ቅድስት ሥላሴ ምስጢሩን ይግለጡልን።*

   *ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።*
ኦሪት ዘፍጥረት 9 : 16

*እግዚአብሔርም ኖኅን በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው ሁሉ መካከል ያቆምሁት የቃልኪዳን ምልክት ይህ ነው አለው* ።
ኦሪት ዘፍጥረት 9 : 17

*ከመረጥሁት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ፥ ለባሪያዬም ለዳዊት ማልሁ* ።
መዝሙረ ዳዊት 89 : 3

*እውነት ነው አምላካችን እግዚአብሔር ከመረጣቸው ጋር ቃል ኪዳን ገብቷል። ለምሳሌ ለአባታችን ለአብርሃም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶለታል፦*

(ዘፍጥ 12 )
------------
1 *እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።*

2 *ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤*

3 *የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ።*

*ይገርማል* !

*እግዚአብሔር አምላክ ለአብርሃም ይህን የመሰለ ታላቅ ቃል ኪዳን የገባለት ለምንድን ነው? መልሱ፦ አብርሃም የእግዚአብሔር ሰው ስለ ነበረ ነው።*

*እመቤታችን  ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የአብርሃም አምላክን 9 ወር ከ5 ቀን በማህጸኗ የተሸከመች ናት! የአብርሃም አምላክን የወለደች ናት! የአብርሃም አምላክን ጡት ያጠባች ናት! የአብርሃም አምላክን በጀርባዋ አዝላ፣ በክንዷ ታቅፋ ጉንጮቹን እየሳመች በመአዛው ፍጹም ደስታ እያደረገች ያሳደገች ናት! የአብርሃም አምላክን 3 ዓመት ከ6 ወር በጀርባዋ አዝላ ከእስራኤል ወደ ግብጽ ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ የተሰደደች ናት! የአብርሃም አምላክን 33 ዓመት ከ3ወር አብራው የኖረች ናት! የአብርሃም አምላክ በመስቀል ሲሰቅል መስቀሉ ስር ተገኝታ በመሪር የሀዘን ጦር የተወጋች ቃል ኪዳንም የተቀበለች ናት!*
*ይህ ሁሉ የሆነው ቅዱስ ዳዊት በትንቢት እንደተናገረ በእርሱ በእግዚአብሔር ከአለም ሁሉ ተለይታ የተመረጠች ስለ ሆነች ነው።*

*እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታል  ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወዷታል* ::
መዝሙረ ዳዊት 132 : 13

*እናም ለተመረጠች እናቱ እግዚአብሔር አምላክ የገባላት ቃል ኪዳን ለአብርሃም ከገባው ቃል ኪዳን የላቀ ነው። እርሷ ከአብርሃም ትበልጣለችና! በስምሽ ለተራበ ያበላ፣ ለተጠማ ያጠጣ፣ ለታረዘ ያለበሰ፣ ቤተ ክርስቲያን ያሳነጸ፣ የታመመውን የታሰረውን የጎበኘ፣ ለቤተ ክርስቲያን ጧፍ እጣን ዘቢብ እና ንዋየ ቅድሳት የሰጠ እምርልሻለሁ የዘላለም ህይወት እሰጠዋለሁ: ብሎ ታላቅ የምህረት ቃል ኪዳን ገብቶላታል።*

*እናም እግዚአብሔር ለመረጣት ቅድስት እናቱ የምህረት ቃልኪዳን ( ኪዳነ ምህረት ) እያሰብን፤  ፍጹም ቃል ኪዳን በገባላት በተወደደ ልጇ ፊት ከፍጥረት ሁሉ የተመረጠች እናታችን ኪዳነ ምህረት በአማላጅነቷ እንድትቆምልን በዚህች ወርሃዊ የኪዳነ ምህረት በዓል በፊቷ እንቁም:: ሀገራችን፣ ቤተ ክርስቲያናችን እና ህዝበ ክርስቲያኑ ከገባንበት ታላቅ ፈተና እናታችን ኪዳነ ምህረት በተወደደ ልጇ ፊት ቆማ ምህረቱን ታሰጠን::                     በርትተን በኪዳነ ምህረት ፊት ቆመን እንጸልይ ዛሬም ያለንበት ወቅት እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ከባድ ወቅት መሆኑን ዛሬም ደግሜ አሳስባለሁ።*

*ብሩህ  ቀን*