2022-08-06 13:34:10
☞ ኢስላም ከሁሉም ሃይማኖት በተለየ መልኩ ወደ ጋብቻ ይጣራል፣
ከላጤነት ይከለክላል።
☞ ጋብቻ በኢስላም እይታ የነፍስ ማረፊያ፣ የቀልብ
መርጊያና መርኪያ፣ የሕሊና መረጋጊያ ነው።
ሁለቱ ጾታዎች በፍቅር፣ በመተዛዘን እና በመተባበር፣ በመቻቻልና በመመካከር የሚኖሩበት ተቋም ነው።
በእንዲህ ዓይነቱ ሰላማዊና የተረጋጋ ተቋም ኢስላማዊ ቤተሰብ ይመሠረታል። ደስተኛና ጤነኛ ልጆች ይፈልቃሉ።
☞ ጋብቻ የነብያቶችና ፣ የመልዕክተኞች ሱና ወይም ፈለግ ነው።
﴿ ﻭَﻟَﻘَﺪْ ﺃَﺭْﺳَﻠْﻨَﺎ ﺭُﺳُﻼً ﻣِّﻦ ﻗَﺒْﻠِﻚَ ﻭَﺟَﻌَﻠْﻨَﺎ ﻟَﻬُﻢْ ﺃَﺯْﻭَﺍﺟﺎً ﻭَﺫُﺭِّﻳَّﺔً
﴾ ﺍﻟﺮﻋﺪ: 38
« ከአንተ በፊትም መልዕክተኞችን በርግጥ ልከናል፤ ለእነሱም ሚስቶችና ልጆች አደረግንላቸው።» ረዕድ፤ 38
ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ: « ﺃﺭﺑﻊ ﻣﻦ ﺳﻨﻦ
ﺍﻟﻤﺮﺳﻠﻴﻦ: ﺍﻟﺤﻨﺎﺀ، ﻭﺍﻟﺘﻌﻄﺮ ، ﻭﺍﻟﺴﻮﺍﻙ ، ﻭﺍﻟﻨﻜﺎﺡ »
የአላህ መልክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋሉ፦ « አራት ነገሮች ከነብያቶች ሱና (ፈለግ) ናቸው ፤ ሂና ፣ ሽቶ፣መፋቂያና
ኒካህ(ጋብቻ)።»
ﻭﻗﺎﻝ ﺍﻟﺮﺳﻮﻝ ﺃﻳﻀﺎ : « ﻳﺎ ﻣﻌﺸﺮ ﺍﻟﺸﺒﺎﺏ ﻣﻦ ﺍﺳﺘﻄﺎﻉ ﻣﻨﻜﻢ
ﺍﻟﺒﺎﺀﺓ؛ ﻓﻠﻴﺘﺰﻭﺝ ﻓﺈﻧﻪ ﺃﻏﺾ ﻟﻠﺒﺼﺮ ﻭﺃﺣﻔﻆ ﻟﻠﻔﺮﺝ، ﻭﻣﻦ ﻟﻢ
ﻳﺴﺘﻄﻊ؛ ﻓﻌﻠﻴﻪ ﺑﺎﻟﺼﻮﻡ، ﻓﺈﻧﻪ ﻟﻪ ﻭﺟﺎﺀ » ، ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ
የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋሉ፦ « እናንተ
ወጣቶች ሆይ! ከእናንተ ውስጥ የትዳርን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ።
ትዳር የአይን መስበሪያ፣ የብልት መጠበቂያ ነው።
የትዳርን ጣጣ ያልቻለ ሰው ፆም ይፁም፣ ፆም ጋሻ ነው።»
አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦
﴿ ﻭَﻣِﻦْ ﺁﻳَﺎﺗِﻪِ ﺃَﻥْ ﺧَﻠَﻖَ ﻟَﻜُﻢ ﻣِّﻦْ ﺃَﻧﻔُﺴِﻜُﻢْ ﺃَﺯْﻭَﺍﺟﺎً ﻟِّﺘَﺴْﻜُﻨُﻮﺍ ﺇِﻟَﻴْﻬَﺎ
ﻭَﺟَﻌَﻞَ ﺑَﻴْﻨَﻜُﻢ ﻣَّﻮَﺩَّﺓً ﻭَﺭَﺣْﻤَﺔً ﺇِﻥَّ ﻓِﻲ ﺫَﻟِﻚَ ﻟَﺂﻳَﺎﺕٍ ﻟِّﻘَﻮْﻡٍ ﻳَﺘَﻔَﻜَّﺮُﻭﻥَ
﴾ ﺍﻟﺮﻭﻡ 21
«ለእናንተም ከነፍሶቻቹ (ከጎሶቻቹሁ) ሚስቶችን፣ ወደ እነሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመሃከላቹ ፍቅርና እዝነት
ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው።
በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ተአምራት አለው።» አል ሩም 21
ታድያ በኢስላም ጋብቸ ታላቅ ሽልማት ያለው የነብዩ ሱና ነው።
ቁርዓን እና ሱና በእጅጉ ወደ ጋብቻ ይጣራሉ።
አማኝ ሰው የነብዩን ፈለግ ከመከተል ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም ስለዚህ ትዳር ሙስሊሞች ዘንድ እጅግ አስፈላጊ
ነገራት ውስጥ አንዱና ዋናው ነው።
የትዳር አጋራችንን በምን መመዘኛ እንምረጥ።
---------------
ትዳር ትልቅ ሃገር የሚገነባበት መሰረት ነው፣ መሰረቱ ያላማረ ነገር እድሜ የለውም ቶሎ ነው የሚፈርሰው
ስለዚህ ኢስላም የትዳር መሰረቱ ጠንካራና በቀላሉ የማይፈር
ለማድረግ መሰረቱን በዲን ላይ እንዲገነባ ያስተምራል።
በርግጥ የትዳር መሰረቶች የተለያዩ ናቸው ነገር ግን ከዲን ውጪ ያሉት መሰረቶች እድሜ የሌላቸው
የትዳር ጠንቅ ናቸው። ነገር ግን ዲን
የተቀሩትን መሰረቶች ይዞ ይመጣሉ።
ﻭﻗﺪ ﺃﺧﺒﺮ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ، ﻋﻦ ﺫﻟﻚ ﺑﻘﻮﻟﻪ : «
ﺗﻨﻜﺢ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻷﺭﺑﻊ ﺧﺼﺎﻝ : ﻟﻤﺎﻟﻬﺎ، ﻭﺟﻤﺎﻟﻬﺎ، ﻭﻟﺤﺴﺒﻬﺎ،
ﻭﻟﺪﻳﻨﻬﺎ، ﻓﺎﻇﻔﺮ ﺑﺬﺍﺕ ﺍﻟﺪﻳﻦ ﺗﺮﺑﺖ ﻳﺪﺍﻙ »
ረሱል (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋሉ፦ “ሴት ልጅ ለአራት ነገሮች ትገባለች።
☞ለገንዘቧ፣
☞ለዘር ክብሯ፣
☞ለውበቷና
☞ለዲኗ።
የዲን ባለቤት የሆነችውን ምረጥ።
(ይህን ካላደረግክ) እጅህ አመድ አፋሽ ትሁን።” (ቡኻሪና ሙስሊም)
ﺃﻓﻀﻞ ﻣﺎ ﻳﻨﺒﻐﻲ ﺗﻮﻓﺮﻩ ﻓﻲ ﺍﻟﺰﻭﺟﻴﻦ، ﻣﻠﺘﺰﻣﺎ ﺑﺸﺮﺍﺋﻊ ﺍﻹﺳﻼﻡ
ﻓﻲ ﺣﻴﺎﺗﻪ ﻓﻼ ﻳﻈﻠﻢ ﺯﻭﺟﺘﻪ، ﻓﺈﻥ ﺃﺣﺒّﻬﺎ ﺃﻛﺮﻣﻬﺎ ﻭﺇﻥ ﻟﻢ
ﻳﺤﺒﻬﺎ ﻟﻢ ﻳﻈﻠﻤﻬﺎ ﻭﻟﻢ ﻳُﻬﻨﻬﺎ
እጅግ በላጩ ምርጥ ባል ማለት የአላህ ዲን በሚገባ የሚያውቅና ስነ ምግባሩ ያማረ ነው።
ዲኑን የሚያውቅ ካገባሽ ከወደደሽ በእጅጉ ያከብርሻል፤
የማይወድሽ ከሆነ አያዋርድሽም ክብርሽን በሚገባ ይጠብቅልሻል። ስለዚህ ዲን ያለው የስነ ምግባር ባለቤት
ምርጫሽ ሊሆን ይገባል።
በዲናቸው እኩል የሆኑ ሰዎች ለትዳር እጅሽን ከጠየቁ ቤተሰቦቹ መልካም የሆኑትን ምረጪ ምክኒያቱም የእሱ
ቤተሰቦች ወደ አንቺ የቀረቡ ናቸውና።
ﻟﻘﻮﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﻣﺤﻤﺪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ : (ﺧﻴﺮ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ﻣﻦ
ﺇﺫﺍ ﻧﻈﺮﺕ ﺇﻟﻴﻬﺎ ﺳﺮﺗﻚ، ﻭﺇﺫﺍ ﺃﻣﺮﺗﻬﺎ ﺃﻃﺎﻋﺘﻚ، ﻭﺇﺫﺍ ﺃﻗﺴﻤﺖ
ﻋﻠﻴﻬﺎ ﺃﺑﺮﺗﻚ، ﻭﺇﺫﺍ ﻏﺒﺖ ﻋﻨﻬﺎ ﺣﻔﻈﺘﻚ ﻓﻲ ﻧﻔﺴﻬﺎ ﻭﻣﺎﻟﻚ ) {
ﺃﺧﺮﺝ ﺍﻟﻨﺴﺎﺋﻲ .
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
“ከሴቶች ሁሉ በላጯ የትኛዋ ናት?” ተብለው ተጠይቀው “
ሲያያት የምታስደስት፣
ሲያዛት የምትታዘዝ፣
በነፍሷም በገንዘቡም እርሱ የማይፈልገውን የማትፈጽም” ሲሉ መለሱ።
ጋብቻ በቀላል ጥሎችና አለመግባባቶች መሠረቱ የማይናጋ ጠንካራና ጽኑ ይሆን ዘንድ
√ የአእምሮን፣
√የመንፈስን እና
√የነፍስን ፍላጎት ሊያሟላ በሚችልበት
መልኩ እንዲታነጽ የመልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፍላጎት ነው።
★ትዳር ልክ እንደ ሁለት እጅ ነው።
√አንድ እጅ ብቻውን
አያጨበጭብም ስለዚህ የጭብጨባው ድምፅ ፈፅሞ ወደ ልብ አይደርስም፣ ሁለቱም በጋራ ከተደጋገፉ ግን ፈፅሞ
ሊጠፋ የማይችል የደስታ ድምፅ በልባቸው ይገባል፣
በደምስራቸው ይዞራል።
ነገ ለሚፈጠረው ጀግና ትውልድ
ዛሬ ላይ የሁለታቹ ትልቅ ተፅኖ እጅግ አስፈላጊ ነው።
ትዳር እስከ ቅርብ ጊዜ የንትርክና የጭቅጭቅ ምሳሌ ተደርጎ
እንሰማ ነበር፣ በጭቅጭቅ መሃል «አቦ ትዳር አትሁንኝ»
የምትል አረፍተ ነገር እንሰማ ነበር።
ይህ እጅግ የተዛባና የተበላሸ አመለካከት ነው።
ትዳር የጭቅጭ መፍትሄ፣ከጭንቀት ማረፊያ የአይምሮ ሰላም ነው።
ስለዚህ ውዶቼ ትዳር እጅግ ከሚያስፈልገን ከዱንያ ነገሮች
አንዱ በመሆኑ በፍጥነት ለትዳር እጅ ልትሰጡ ይገባል።
ትዳር (ኒካህ) እጅግ ቀለል ያለ እራስን ከዝሙት የመጠበቂያ መንገድ ነው። ይህ መንገድ ብሩህ ከማንኛውም ነውጥ የፀዳ ሰላማዊ ነው።
አንድ አንድ ወንድሞች «ኒካህን ደፈርካት» የሚለው ንግግራቸው
እጅግ የተሳሳተ ነው። ባይሆን «ነፍስያዬ አሸንፌ ወደ ትዳር ገባሁ» ማለት ነው ያለበት እንጂ ትዳር መመስረት እጅግ
ቀላል ነው፣ ዘላቂ ለማድረግ ግን ከፍተኛ ትግል ያስፈልጋል. ስለዚህ ትዳራችን ስኬታማ እንዲሆን ከላይ
የተዘረዘሩትን የዲን መሰረቶች ተግባራዊ ማድረግ አለብን።
ይቀላቀሉ
ሊንኩን እንዲነሳ አንፈቅድም
https://t.me/SileTidarEnmekaker
668 viewsedited 10:34