Get Mystery Box with random crypto!

ትዳር ውበትሽ ነው ስለገረመኝ ነው የአኼራ እህቴ መልስን በመፈለግ ጥያቄ ማንሳቴ ከቁርዓን ከሀዲስ | ትዳር የአማኞች ምሽግ

ትዳር ውበትሽ ነው

ስለገረመኝ ነው የአኼራ እህቴ
መልስን በመፈለግ ጥያቄ ማንሳቴ
ከቁርዓን ከሀዲስ መረጃሽን ስጪኝ
መዋብሽ ማጌጥሽ ለማነው ንገሪኝ
ከቤት ስትወጪ መኳኳል ሽቶ መነስነሱ
ለህዝቡ ነው እንዴ ለጅን ለኢንሱ?
አባያ ቀሚሱን ፋሽን ተቀምሮ
ወገብ ከደረትሽ የፊጥኝ ታስሮ
ቅርፁ ጎልቶ ወጣ መሰለ ማሰሮ
ይህ ሁሉ ጋጋታ ማንን ለመማረክ
ባልሽን ነው ህዝቡን ማንን ለማንበርከክ?
የት ጠፋ ተቅዋሽ ሀያእን ምን በላው
ለባል ሳትዋቢ ለህዝቡ ምንድ`ነው?
መደሰት ያለበት መማረክ ያለበት
የመልክ ቁንጅና ባልሽ ነው ባለቤት
መዋብሽ ማጌጥሽ ከሆነ ለህዝቡ
እሱን ችላ ብለሽ ከወጣሽ ከልቡ
ትዳርም ፈርሶ ቤቱም ይበተናል
ነገም በአኼራ ለችሎት ይቀርባል
ሳይረፍድ ንቂና ፍቅራቹ ይታደስ
መዋብ ለባል ሆኖ ሂጃቡ ይለበስ
እኔ ልምረጥልሽ ሸሪዓን ያሟላ
መሆንን ከፈለግሽ የዲንሽ ከለላ
ኢስላማዊ ውበት አጃኢበ^ረቢ
በጅልባብ በኒቃብ ድመቂ ተዋቢ
https://t.me/SileTidarEnmekaker