Get Mystery Box with random crypto!

​​' ትክክለኛ እውቀት ማለት የራስን የድንቁርና መጠን አልያም ስፋት ማወቅ ነው። ' / ኮንፊሽየስ | የደምቢ ልጆች ጥበብ ስራዎች

​​" ትክክለኛ እውቀት ማለት የራስን የድንቁርና መጠን አልያም ስፋት ማወቅ ነው። "
/ ኮንፊሽየስ
ዕውቀት ውጪያዊ የሆነና ከውጪ የምንቃርመው የሚመስለን ብዙዎቻችን ነን.
ግን የእውቀት ባለቤት እኛው ነን.
'የሰው ልጅ የሚማረው........
#የጠፋበትን_አእምሮ_ለማስመለስ_ነው
የምትል የቆየች አባባል አለች።
እውቀትን እና የእውቀትን ፍለጋ ይሄ በሚገባ የሚገልጸው ይመስላል።
መረጃ የእውቀት ግብአት ቢሆን እንጂ በራሱ እውቀት አይሆንም፣ ምክንያቱም መረጃ ማለት ከውጪ የምትሰበስበው ውጫዊ ነገር ነውና።
ትምህርት ማለት ልክ ያንቀላፋ አዕምሮን እንደማንቃት ነው።
ይህ ማለት ግን አንቀላፍተን ተፈጥረናል ማለት አይደለም፣ ማሰብ እንደምትችል ያወቅህ እና ያሰብህ ሰዓት የሁሉም ነገር መነሻው ያንተ አእምሮ እንደሆነ ትደርስበታለህ።
ማይምነትን ልትፈራው እንጂ ልትጠላው አይገባም።
ማይምነትህ መነሻህ ነውና ማይምነትህን ካላወቅህም ወደማወቅ መንገድ አትጀምርምና።
ስንጠቀልለው..........
"የራስህን የድንቁርና መጠን ስታውቅ ያኔ ትክክለኛ እውቀት ይኖርሃል" ሲል ነዉ ኮንፊሺየስ ያስቀመጠው።
በተለይ ቁንፅል መረጃን እና እውቀትን ያደባለቁ ሰዎች ፣ ወይም የራሳቸው ማይምነት ወደ እውቀት የመራቸው መሆኑን የዘነጉ ሰዎች ፣ ወይም በሌላ አገላለፅ ጥራዝ ነጠቅ ወሬን እንደ ጥልቅ እውቀት ቆጥረው ሰው ላይ የንቀት እና የስድብ አጀብ የሚያወርዱትን አዋቂ መሳዮች መጀመርያ የራሳችሁን ድንቁርና እውቁት ሲላቸው ነው።
ምንጭ ፦ Philosophical Megazines
"
"
@hollypoem
@hollypoem
@hollypoem