Get Mystery Box with random crypto!

እውነተኛ ፍቅር እውነተኛ ፍቅር ፈጣሪ ከገነት በታች ለሰው ልጆች የሰጠው ስጦታ ነው••• | የፍቅር አለም LOVES WORLD

እውነተኛ ፍቅር

እውነተኛ ፍቅር ፈጣሪ ከገነት በታች ለሰው ልጆች የሰጠው ስጦታ ነው•••

ለፍቅር ሁነኛ ማረጋገጫ #እምነት ነው•••

ማንም ሰው አይናችን ውስጥ ሊገባ ይችላል ፤ ነገር ግን ልባችን ውስጥ ዘልቆ የሚገባው አንድ ልዩ ሰው ነው•••

ራስህን እንድትሆን ለማይፈቅድልህ የፍቅር ወዳጅነት ራስን አሳልፈህ አትስጥ•••

በሌሎች የመፈቀርን ሀሰብ ከመውደድ በፊት ፤ መጀመሪያ ራስን መውደድን ተማር•••

በማይረባ ድንጋይ ጊዚያቸውን እንዳባከኑ ሲገባቸው በእጃቸው የነበረው እንቁ እንደነበር ይገነዘባሉ•••

አንድን ሰው ለመልኩ ብቻ አናፈቅረውም ፣ ለአለባበሱ ወይም ለምርጥ መኪናውም ልናፈቅረው አይገባም ፤ የምናፈቅረው እኛ ብቻ ልንሰማው የምንችለውን ዜማ ስለሚያቀነቅኑ ነው•••

ፍቅር ማለት ወሲብ አይደለም ፣ ወይም ጥሩ ምሽቶችን በጋራ ማሳለፍም አይደለም ፣ ወይም ተቃቅፎ መታየም ሳይሆን ማንም ሊያስደስታችሁ በማይችልበት መንገድ ደስታን ሊፈጥርላችሁ ከሚችል ሰው ጋር አብሮ መሆን ነው•••

ፍቅር እውር አይደለም ፣ ሌሎች በቀላሉ ሊያዩትን ያልቻሉትን ነገር እንዲያዩ የሚያስችል እንጂ•••

ፍቅር ይሻለናል

@silefikrr @manditua