Get Mystery Box with random crypto!

ከጎንደር የተለያዩ አቅጣጫዎች ተነስተው ወደ ባህር ዳር የተጓዙ በሽህ የሚቆጠሩ የፋሲል ከነማ ደጋፊ | VIP ቤቲንግ TIPS 🇪🇹

ከጎንደር የተለያዩ አቅጣጫዎች ተነስተው ወደ ባህር ዳር የተጓዙ በሽህ የሚቆጠሩ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ወደ ስታዲዮም እንዳንገባ በመንግስት የጸጥታ አካል ክልከላ እና ወከባ እየገጠመን ነው አሉ።

"አርበኛ ዘመነ ካሴ እና ፋኖ እያላችሁ ትጨፍራላችሁ እና አትገቡም" ተብለናል የሚሉት ወጣቶች ከጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች ተነስተው ዘንዘልማን አልፈው ቅዱስ ገብርኤል መድረሳቸውን ይናገራሉ።

ባህር ዳር ሊገቡ ቅዱስ ገብርኤል አካባቢ እንደደረሱ የሬዲዮ መገናኛ የያዙ የልዩ ኃይል አመራሮች ከ10 እስከ 15 በሚደርሱ ተሽከርካሪዎች የመጡ ደጋፊዎችን ሁሉ በማስቆም እና በማስወረድም ጭምር ወደ ስታዲዮም መግባት አትችሉም ብለው እንደከለከሏቸው ገልጸዋል።

ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርገውን አምስተኛ ሳምንት ጨዋታውን ለመደገፍ እና ለመከታተል እንጅ እነሱ እንደሚሉት ለሌላ አላማ አይደለም ብለዋል ቅሬታ አቅራቢዎቹ።

አሁንም እየፈጸሙት ያለውን ያልተገባ እንግልት አቁመው እንድንገባ ቢያደርጉ መልካም ነው ሲሉ ጠይቀዋል።
Amm

@shewapress