2022-11-26 07:15:32
መለያየት ከአዕምሮ ይጀምራል። ዘፈኖች ቀድመው ይታወሳሉ። ያሳለፍናቸው ኹነቶች፣ የሕይወት ክስተቶች፣ ኑረቶች የሚታወሱት ቀድመው በዘፈን፣ ደግመው በሙዚቃ፣ ሠልሰው በዜማ ነው። ዜማ ኃይል፣ ሙዚቃ ቁርኝት፣ ዘፈን አብሮነት አለው። ሲያለያዩም እንዲሁ ነው። የቁርኝታቸውን ያኽል አይፋቱም። በመልካምም ይቆራኛሉ፤ በመጥፎውም ይቆራኛሉ።
“የሠርጉ ዕለት ጥሪው ሲደርስ” ማሰብ ነው። ማሰብ ብቻውን በቂ ነው። አዕምሮን ያደክማል፤ ልብን ይሠብራል፤ ጉልበትን ያልፈሰፍሳል። “ሰው መክሮት ይኾናል” ሆድ እያወቀ፣ ልብ እየመረመረ፣ አዕምሮ እያስታወሰ! እርሱ እንደሚሠራው እየታወቀ ማሰብን ለማቆም፣ ማሰላሰያን ለመሸወድ “ሰው መክሮኽ ይኾናል” ብሎ መጃጃልም አለ። ራሳችንን ስናጃጅል አንደኞች ነን። የሠርጋቸው ዕለትም እንጠ’ራለን። ሰውም አልመከራቸውም። በኹለታም ያስሔዳል። ደግሞ’ኮ “አለኝ ድርሻ ላንተ መጨረሻ” ብለን እንሰናበታለን። ይኼም ስንብት፤ “ድርሻ አለኝ” ብሎ መንቧቸት እንጂ ድርሻውስ ተበልቷል፤ የምንለው ስለምናጣ ብቻ ነው።
4 views04:15