Get Mystery Box with random crypto!

* መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም * ታሪክን የኋሊት ' … ምንም እንኳ በኢትዮጵያ ታሪክ | በራሪ ሐሳቦች

* መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም *

ታሪክን የኋሊት

" … ምንም እንኳ በኢትዮጵያ ታሪክ ለረዥም ጊዜ የኖረውን ዘውድ ሕዝቡ በቅን ልቦና የአንድነት ምልክት ነው ብሎ የሚያምንበት ቢሆንም ከሃምሳ ዓመት በላይ በአልጋ ወራሽነት ጀምረው ሀገሪቱን ሲመሩ ከሕዝብ የተሰጠዎትን ክቡር ሥልጣን አለአግባብ በልዮ ልዮ ጊዜ ለራስዎና በአካባቢዎ ለሚገኙት ቤተሰቦችዎና የግል አሽከሮችዎ ጥቅም በማዋል ሀገሪቱን አሁን ካለችበት ችግር ላይ እንድትወድቅ ከማድረግዎም በላይ ዕድሜዎ ከ82 ዓመት በላይ በመሆኑ በአካልም ሆነ በአእምሮ በመድከምዎ ከእንግዲህ ወዲህ ይህን ከፍተኛ ኃላፊነት ሊሸከሙ አይችሉም።" ሻለቃ ደበላ ዲንሣ

ንጉሡ የተነበበውን ከሰሙ በኋላ እንዲህ አሉ…

" ያላችሁትን በጥሞና አዳምጠናችኋል። ለአገር በጎ አስባችሁ ከተነሳችሁ የአገርን ጥቅም ከራስ ጥቅም ማስቀደም አይቻልም። እኛ እስከዛሬ አገራችንንና ሕዝባችንን አቅማችን በፈቀደውና በምንችለው ሁሉ አገልግለናል። አሀን ተራው የኛ ነው ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ።"

ብለዉ በቮልሳቸዉ ከቤተመንግስት ወጡ ይሄ ህዝብ የሰገደላቸዉን መሪ ሌባ ሌባ ሌባ እያለ ሸኛቸዉ

በኢትዮጵያ ታሪክ ረዥሙን ዘመን ያስቆጠረው ዘውዳዉ አገዛዝ ያለ ደም መፋሰስ ያበቃበት ቀን ነበር የዛሬው ቀን።

በመቀጠል

ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ
ላገር ብልጽግና ለወገን መከታ
ያለምንም ደም
ኢትዮጵያ ትቅደም! !!!
ኢትዮጵያ ትቅደም! !!!

ብሎ የተነሳዉ አቢዮታዊ የደርግ መንግስት በ ማግሥቱ… እነዚያ ለሀገራቸው የለፉትንና የደከሙትን መጦር የሚገባቸዉን አዛውንቶች በመረሸን አገሪቷ ላይ ቀዳሚዉን የደም ጎርፍ አፈሰሰ።

በመቀጠል የደም ጎሮፉ የገዛ አባልና መስራቹን ተፈሪ ባንቲን ም ወሰደ።

ደርግን ከጥንስሱ የመሰረተዉ ወታደሮችን አደራጅቶ ንጉሱን የገለበጠዉ ፡፡ የደርግ እናትም አባትም ኢትዮጲያ ትቅደም የሚለዉን ባንዲራ በየ ክፍለሃገሩ የበተነ መሬት ላራሹ ያለዉ ኮሮኔል አጥናፉ አባተ ነበር።
ኮሮኔል አጥናፉ አባተ እና መንግስቱ ኋይለማርያም ከዉትድራና ካንፕ አንስቶ እስከንጉሱን ግልበጣ የቤተመንግስት ዙፋን ላይ እስኪቀመጡ የማይለያዩ የፀኑ ወዳጆች ናቸዉ። ኮሮኔል አጥናፉ አባተ እንደ ጓድ መንግስቱ አደበተ ርቱ ከሰዎችጋር የመግባባት ባህሪያቸዉ አነስ ያለ በመሆኑ የጠቅላይ ሚኒስተራቸዉን ስልጣን በገዛ ፍቃዳቸዉ ለ ጓድ መንግስቱ አስረክበዉ እሳቸዉ ምክትል ሆነዉ በየክፍለሃገሩ እየተዘዋወሩ ጉዳዮችን ያስፈፅማሉ።

ሚስቶቻቸዉ በአንድ ቡና ሚጠጡ ፡ ልጆቻቸዉ አብረዉ ያደጉ፡ አብረዉ የተማሩ፡ አብረዉ የተጫወቱ ናቸዉ። የጓደኝነት ትስስራቸዉ ከሁለቱ አልፎ ለቤተሰብም ያጠመረ ስለነበረ በፍፁም የመከዳዳት እና መሳሪያ ለመማዘዘዝ ያደርሳል ተብሎ ለመገመት ይከብድ ነበረ።።።

የሆነዉሆኖ በመሃል የሁለቱ ጓዶች ያለመስማማት፡ የሃሳብ ልየነቶች፡ ግጭት ተፈጠረ ትልቁ ምክንያት
ሶሻሊዝም ለኢትዮጵያ ህዝብ ለአማኝ ህዝብ አይሆንም ይቅርብን
ያለፍርድ የንጉሱ ባለስልጣናት መገደል
የንፁሐን ደም ከንጉሱ ጋር ንኪኪ ነበራቸዉ በመባል መታሰር ወዘተ ነበረ ፡፡ ኮሮኔል አጥናፉ አባተን ያስቆጣዉ ሆኖም ሆኖ ግን እሱም ከተቆረቆረላቸዉ ሰዉች አይነት ቅጣት አልዳነም፡፡ መጨረሻ እጣዉ ለኮሎኔል አጥናፉም ደረሰ

አቢዮት ልጆችዋን ቅርጥፍ አድርጋ በላች!!!!!

ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም ያለዉ አቢዮቱ የተማሩ የኢትዮጵያ ልጆቿን በብዛት ቀጠፈ ለቁጥር እስኪታክት አስክሬኖች በጅምላ ተቀበሩ ፀጉራቸዉን ያጎፈሩ ወጣቶች ሁሉ እንደወጡ ቀሩ ኢትዮጵያ በልጆቿ ደም ታጠበች ።

ያ ትዉልድ የሀገሪቷ እጥፋት የጀመረበት ዘመን ነበር እዚህ ጋር የኮ/ል ፍስሀን ንግግር እንስቼ ፁፌን እቋጫለሁ

"…የኢሕአፓ ቆራጥነት፣ የመኢሶን የርዕዮተ-ዓለም ብስለትና የደርግ ሀገር ወዳድነት ተጣምሮ አገሪቱን ወደ ላቀ ደረጃ ሊያደርስ ይችል የነበረ ኃይል በአመራሮቹ ስህተት ያለአግባብ እርስ በርሱ ተጨራርሷል።”