Get Mystery Box with random crypto!

ሸገር NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ shegernewseth — ሸገር NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ shegernewseth — ሸገር NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @shegernewseth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.74K
የሰርጥ መግለጫ

የሚያምኑት መረጃ!!
እጅግ ፈጣንና ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰጣጣችን ይረካሉ አሁኑኑ የቤተሰባችን
አባል ይሁኑ #ሸገር የናንተ #ሸገር የኛ

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-08-29 13:55:58
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለስራ ጉብኝት ኡጋንዳ ናቻው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ኡጋንዳ ገብተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ግብዣ ወደ ሀገሪቱ ማቅናታቸው ታውቋል።

ኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በትዊተረ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍም በዛሩው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መቀበቻለውን እና እየተወያዩ መሆኑን አስታውቀዋል።

[Alain]
@shegernewsBot
@shegernewsETH
18.4K viewsedited  10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-27 20:20:00
#Breaking News

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ለማምራት መስማማቱን ክለቡ በይፋ አሳወቀ!

ከአስራ ሁለት ዓመታት በኋላ ፖርቹጋላዊው የ ባሎን ዶር አሸናፊ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ልጅነት ክለቡ ማንችስተር ዩናይትድ መመለሱ እውን ሆኗል።
20.2K views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-16 17:32:47
አሽራፍ ጋኒ ሀገር ለቀው ሲወጡ የያዙት ብር መጠን ከተሳፈሩበት ሂሊኮፕተር በላይ በመሆኑ የተወሰነ ገንዘብ ኤየር ፖርት ውስጥ ጥለው ለመሄድ ተገደዋል::

ትናንት ታሊባንን ሸሽተው ሀገር ለቀው የሄዱት የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት በአራት መኪና ብር አጭቀው ቢወጡም የተሳፈሩበት ሂሊኮፕተር የያዙትን ብር ባለመቻሉ የተወሰነ ብር ኤየር ፖርት ትተው ሄደዋል ሲል በካቡል የሚገኘው የራሺያ ኢምባሲ ዛሬ ገልፇል።
የብሩን መጠን ግን ኢምባሲው አልገለፀም።

@shegernewsbot
@shegernewsETH
27.0K viewsedited  14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-15 21:32:44
23.2K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-07 12:13:19 መንግሥት በአገሪቱ የሚገኙ ቅዱሳ ቦታዎች እና ተቋማትን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ይህን ያለው ለቅዱሳን ቦታዎች እና ተቋማት የሚደረግ ጥበቃን በተመለከተ የፕሬስ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።

የውጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው በቅርቡ በተወሰኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች አሸባሪው የህወሃት ቡድን በከፈተው ጥቃት የኢትዮጵያ ህዝብ የባህል፣ የእምነት እና የማንነት መገለጫ በሆኑ እድሜ ጠገብ ቅርሶች ላይ የደህንነት ስጋት ደቅኗል ብሏል፡፡

ስጋቱ ቡድኑ ባለፉት ስምንት ወራት ከፈጸመው መሰል ዝርፊያና ዉድመት ተግባሩ የሚመነጭ ነዉ ያለው።

የሽብር ቡድኑ በአዋሳኝ ክልሎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር የእርዳታ አቅርቦትን በማስተጓጎል ሚሊዮኖችን አደጋ ላይ ጥሏል።

አሸባሪው ህወሓት ቡድን መንግሥት እርዳታ ተደራሸ እንዲሆንና አርሶ አደሩ የዝናብ ወቅቱ ን በመጠቀም የግብርና ስራዉን እንዲያከናዉን በማሰብ የወሰደዉ የተናጠል የተኩስ አቁም ዉሳኔን ወደ ጎን በመተው እንዲሁም በአለም አቀፉ ማህበረሰብ የቀረበለትን የተኩስ አቁም ጥሪ ቸል በማለት ትንኮሳውን ቀጥሏል።

በመሆኑም በአገሪቱ የሚገኙ ቅዱሳ ቦታዎች እና ተቋማትን ደህንነት ለመጠበቅ መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም የአሸባሪውን ቡድን የጥፋት ድርጊት እንዲያወግዝ መንግስት ጥሪ ያቀርባል።

Via #AMN
@shegernewsBot
@shegernewsETH
27.0K views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-03 22:24:33
የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር ድርድር እንደማያደርግ ገለጸ

የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት አመራሮች ጋር ድርድር እንደማያደርግ የአገሪቱ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ዛዲግ አብረሃ ለቢቢሲ ተናገሩ።

በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል የሚገኘውን አብዛኛውን የትግራይ ክልል ከተቆጣጡሩት ከህወሓት አማጽያን ጋር ለወራት በዘለቀ ጦርነት ውስጥ የቆየው የኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ካለው ቡድን ጋር እንደማይደራደር አስታውቋል።

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ከቢቢሲ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ከአማጺው ኃይል አመራሮች አንዱ የሆኑት ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ ያቀረቡት ቅድመ ሁኔታ ተቀባይነት አግኝቶ የተኩስ አቁሙ እንዲደረግና ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ ውይይት ተደርጎ የሽግግር ሂደት መጀመር አለበት ማለታቸው ይታወሳል።

በዚህ ላይ ለቢቢሲ ምላሽ የሰጡት የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብረሃ መንግሥት ከህወሓት አመራሮች ለድርድር እንደማይቀመጥ ገልጸዋል።

አሁን በሰሜኑ የአገሪቱ አካባቢ ያለውን ሁኔታ በሚመለከትም መንግሥት በተናጠል ተኩስ አቁም ውስጥ መሆኑን ጠቅሰው "አሁን በህወሓት በኩል የሚታየው ነገር ራስን አጋኖ ከማየት የመነጨ ነው" ብለዋል።

ነገር ግን መንግሥት ትዕግስቱ ሲሟጠጥ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ "አቅማችንን ማየት ከፈለጋችሁ የተወሰኑ ሳምንታት መጠበቅ ይኖርባችኋል። ትዕግስታችን የተሟጠጠ ዕለት እንዴት ከእያንዳንዱ ከተማና መንደር ጠራርገን እንደምናስወጣቸው ታያላችሁ። ጦርነት ከሆነ ፍላጎታቸው....ያገኙታል" ሲሉ ተናግረዋል
27.9K views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ