Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀብት 1.1 ተሪሊዮን ደረሰ ለሃገር መከላክያ ሠራዊትና ለጸጥታ ኃይሎች | ሸገር NEWS

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀብት 1.1 ተሪሊዮን ደረሰ

ለሃገር መከላክያ ሠራዊትና ለጸጥታ ኃይሎች 800 ሚሊዮን ብር ሰጠ

የኢትዮያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ሀብት ከ 1.1 ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡ የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ አቢ ሳኖ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣የባንኩ ሀብት ከ1.1 ትሪሊዮን ብር በላይ የደረሰው የ2013 በጀት ዓመት መጣናቀቂያ ድረስ መሆኑን ተናገረዋል፡፡

እንደ ፕሬዝደንቱ ገለፃ፣ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን የጠቆሙት አቶ አቢ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የክልል የጸጥታ ኃይሎች ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ የሃገርን ህልውና ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለመደገፍና በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች፣ ባንኩ 300 ሚሊዮ ብርና ሠራተኛው 500 ሚሊዮን ብር በድምሩ 800 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

@shegernewsbot
@shegernewsETH