Get Mystery Box with random crypto!

የቴዲ አፍሮ መልዕክት! የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገ | Amhara times

የቴዲ አፍሮ መልዕክት!

የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ 127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ነው::

      የዘንድሮውን የ127ኛው የአድዋ ድል በአልን ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደ ሀገር የመቀጠል እጣዋ ከፍተኛ አደጋ ላይ የወደቀበት ወቅት መሆኑን አፅንኦት በመስጠት እና ቀደምት አባቶቻችን በታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት ያቆዩልንን የጋራ ሀገራችንን ከመቼውም ጊዜ በላቀ የመጠበቅ እንዲሁም ከገጠማት እጅግ ፈታኝ የህልውና አደጋ የመታደግ ታላቅ ታሪካዊ ሃላፊነት እና አደራ በኛ ትውልድ ትከሻ ላይ መውደቁን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊሆን ይገባል::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)