Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች የከተማ አስተዳደሩ ተጠያቂ ነው ሲል እንባ ጠ | Sheger student Union( የአዲስ አበባ ተማሪዎች ህብረት)

በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች የከተማ አስተዳደሩ ተጠያቂ ነው ሲል እንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ

ከኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ መሰቀል እና መዝሙር መዘመር ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ለሚፈጠሩ ችግሮች ብቸኛው ተጠያቂ የከተማ አስተዳደሩ ነው ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ተማሪዎችን ለማስገደድ በሚፈፀሙ ድርጊቶች በተማሪዎች እና በትምህርት ቤት ንብረቶች ላይ ለሚደርሱ ጥፋቶች “ተጠያቂው የከተማ አስተዳደሩ እንጂ ሌላ ውጫዊ አካል” አይደለም ብሏል።

እንባ ጠባቂ ተቋሙ አክሎም የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ የሚያገኛቸው ልዩ ጥቅሞች እና የአፈፃፀም ስርዓት በልተቀመጠለት ሁኔታ የክልሉ ባንዲራ እና መዝሙር በከተማዋ እንዲፈፀም የሚያስገድዱ “ግለሰብ ባለስልጣናት” በመኖራቸው የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ የአንድ አካባቢ ችግር በድርድር ከተፈታ ለሌላ አካባቢ የማይሰራበት እንዲሁም የአደረጃጀት ጥያቄ የአንዱ በህገ መንግስቱ ተፈቶ የሌላው የማይፈታበት ምክንያቶች አይኖሩም ብሏል።


ኢትዮጵያ ብቻ
@Sheger_student_union
@Sheger_student_union
Join and Share
የአዲስ አበባ ተማሪዎች ህብረት