Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ለሁሉም የአዲስ አበባ ተማሪዎች ተቃውሞ ከመጀመራቹህ በፊት ህብረት ፍጠሩ። አንድ | Sheger student Union( የአዲስ አበባ ተማሪዎች ህብረት)

ይድረስ ለሁሉም የአዲስ አበባ ተማሪዎች

ተቃውሞ ከመጀመራቹህ በፊት ህብረት ፍጠሩ። አንድ ላይ ሁናቹህ ድምፃቹህን አሰሙ። በተናጠል የሚባል ነገር እንዳይኖር ሁላቹህም አንድ ላይ ማበር አለባቹህ። እናንተ አንድ ላይ ከጠነከራቹህ ማንም አይነካቹህም።


ሲቪል ከለበሱ ሰላዮች፣ ጋውን ሁሉ ለብሰው ሊመጡ ስለሚችሉ ተጠንቀቁ። ማንም ተማሪ መያዝ የለበትም።

ትግላችን የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እስኪወርድ ነው። እኛ መዘመር የምንፈልገው አባቶቻችን ለሞቱላት ለኢትዮጵያችን ብቻ ነው።

አትፍሩ አንድ ላይ ካበራቹህ እናንተን ነው የሚፈሩት። ይሔን ነገር እንደቀላል እንዳታዩት ዛሬ ዝም ካልናቸው ኢትዮጵያችንን ከአዕምሯችን ፍቀው አዲስ አበባችን ላይ ይጨፍሩበታል። ስለዚህ እኛ በዚህ ተቃውሟችን አዲስ አበባ የራሷ ልጆች እንዳሏት እናሳያቸዋለን።

በሁሉም ትምህርት ቤት ግሩፕ ሼር ይደረግ !

ኢትዮጵያ ብቻ
@Sheger_student_union
@Sheger_student_union
Join and Share
የአዲስ አበባ ተማሪዎች ህብረት