Get Mystery Box with random crypto!

ከባለፈዉ የቀጠለ የመፅሐፍ ቅዱስ ስሞች #ክፍል 2 1 ባሮክ ፡ ብሩክ ማለት ነዉ 2 ሮቤል፦እነሆ | Shega info

ከባለፈዉ የቀጠለ የመፅሐፍ ቅዱስ ስሞች #ክፍል 2

1 ባሮክ ፡ ብሩክ ማለት ነዉ
2 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው።
3 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል ማለት ነው።
4 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ ማለት ነው።
5 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና ማለት ነው።
6 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው።
7 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ ማለት ነው።
8 እስጢፋኖስ፦አክሊል ማለት ነው።
9 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ ማለት ነው።
10 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ ማለት ነው።
11 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ ማለት ነው።
12 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል ማለት ነው።
13 ዮርዳኖስ፦ወራጅ ውሃ ማለት ነው።
14 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
15 ገነት፦የአትክልት ስፍራ ማለት ነው።
16 ፊልድልፍያ፦የወንድማማች ፍቅር ማለት ነው።
17 ዲና፦ፈረደ ማለት ነው።
18 ማኑሄ፦እረፍት ማለት ነው።
19 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
20 ራማ፦ከፍታ ማለት ነው።
21ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
22 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ ማለት ነው።
23 ሕርያቆስ፦ኅሩይ ምርጥ ማለት ነው።
24 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ ማለት ነው።
25 ቶማስ፦ፀሐይ ማለት ነው።
26 ታዴዎስ፦እሸቱ ማለት ነው።(ግብራዊ ትርጓሜ)
27 ማትያስ፦ፀሐይ ወይም ምትክ ማለት ነው።
28 ቀሌምንጦስ፦ግንብ ማለት ነው።
29 አቤል፦በግ ወይም ደመና ማለት ነው።
30 ኖኅ፦ደስታ ማለት ነው።
31 ሴም፦ተሾመ ማለት ነው።
32 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም ይሳቅ ማለት ነው።
33 ሙሴ፦የውሃ ልጅ ማለት ነው
34 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ ማለት ነው።
35 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለት ነው።
36 እሴይ፦ዋጋየ ማለት ነው።
37 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ ማለት ነው።
38 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ ማለት ነው፣
39 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ ማለት ነው።
40 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ ማለት ነው።
41 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው ማለት ነው፣
42 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
43 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ ማለት ነው።
44 ራኄል፦በግዕት ማለት ነው።
45 ዕዝራ፦ረዳቴ ማለት ነው።
46 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች ማለት ነው።
47 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ ማለት ነው።
48 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ ማለት ነው።
49 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ ማለት ነው።
50 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት ማለት ነው።
51 ሶምሶን፦ፀሐይ ማለት ነው።
52 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
53 ማርታ፦እመቤት ማለት ነው።
54 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር ማለት ነው።
55 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው ማለት ነው።
56 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች ማለት ነው።
57 ታዴዎስ፦ተወዳጅ ወይም ፍቁር ማለት ነው።(ቃላዊ ትርጓሜው)
58 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር ማለት ነው።
59 ሄኖስ፦ሰው ማለት ነው።
60 ሰሎሜ፦ሰላም ማለት ነው።

ማስታወሻ፦ከላይ ከጻፍኳቸው ውስጥ አንዳንድ ስሞች ከ81ዱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኙ ከሌሎች የታሪክ እና የገድል መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ስሞች መሆናቸውን ማሳወቅ እፈልጋለሁ።

በትረማርያም
#ሼር

የ ሙሉ ትንተና ዮቲዮብ ቻናላችን ይቀላቀሉን
https://m.youtube.com/channel/UCHYsjv2HLu-K6e0C7MxxVmA/featured