Get Mystery Box with random crypto!

#ተስፋ ማለት #በድቅድቅ ጨለማ ጭላንጭል ብርሃን እንደማየት ነው። ፀሀይዋ ስትጠፋ አትፍራ ምክ | Shega info

#ተስፋ ማለት #በድቅድቅ ጨለማ ጭላንጭል ብርሃን እንደማየት ነው።

ፀሀይዋ ስትጠፋ አትፍራ ምክንያቱም ከዋክብት ይወጣሉና።

አለም አትችልም! ተስፋ ቁረጥ ስትልህ
ተስፋ ግድ የለህም አንድ ጊዜ ሞክር ይልሀል።

ቀና አስተሳሰብ ነገሮች እንዴት በተለየ መልኩ እንደሚከናወኑ መጠየቅ ነው።

በአሉታዊ አስተሳሰብ ራስህን አትሙላ። ይህ የተሸናፊዎች መንፈስ ነው።

ተስፋ ማታደርግ ከሆነ ከተስፋህ በስተጀርባ ምን እንዳለ ማየት አትችልም።

ህይወትን አትፍራት ልትኖራት ነው የተፈጠረቺው። ሊያኖርህ እሚችለው ስንቅ ተስፋህና እምነትህ ነው።

ዛሬም አዲስ ጅማሮ ፡ አዲስ ቀን ነው። በጥልቅ ተንፍስ፡ ትናንት ካልተሳካልህ ዛሬን ፈገግ በልና እንደገና ጀምር።

ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱ ያቺ ህይወትህን ሙሉ ስትፈልጋት የነበረችው ቀን ዛሬ ልትሆን ትችላለችና።

ተስፋ አድርግ፤ ቁጭ ብለህ ግን አትጠብቃት፡ በጥረትህ ልታመጣት ሞክር።

የሰው ልጆች ልዩ ሚያረጋቸው እማይቻለውን ለመቻል ስለሚጥሩ ነው

እዛ ሚያደርሳቸው ደግሞ ከልባቸው ውስጥ እሚንቀለቀለው ተስፋቸው ነውና ተስፋ አድርግ።
@shegainfom
ፍቅር : ሰላም : ለምድራችን !