Get Mystery Box with random crypto!

ሻሚል - shamil

የቴሌግራም ቻናል አርማ shamilunkamil — ሻሚል - shamil
የቴሌግራም ቻናል አርማ shamilunkamil — ሻሚል - shamil
የሰርጥ አድራሻ: @shamilunkamil
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 940
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ፊት!
ልቅና እና ክብር ለአሏህ ፣ ለመልክተኛው እና ለሙእሚኖች ይሁን።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-26 09:52:38 እንዲዚህ አይነት ጓደኛ ካለህ እንዴት ደስ ይላል...!
ይመራሃል...
ይመክራሃል...
ጉደለቶችህን ያሳያሃል...
ያዳምጣሀል...
ችግሮችህን ለመፍታት ጥረት ያደርጋል...
በጥሩ ስራ ላይ ያግዝሀል...
ሸይጧንን በመዋጋት ላይ ይረዳሃል...
በሚስጥርህ ላይ ታምነዋለህ...
ምክሮችህን ይሰማል...
ለአንተም ለዲህንህም ይፈራልሃል...

ጓደኛ ወይ ወደ ጀነት ወይ ወደ ጀሀነም የሚወስድ ነው።
ሙእሚን የሙእሚን ወንድም ነው።
ሙእሚን የወንድሙ መስታውት ነው።
ሙእሚን ለሙእሚን እንደ ግንብ ነው አንዱ አንዱን ያጠነክራል።

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil

https://t.me/shamilunkamil
88 viewsedited  06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 21:30:08 መውሊድን ማክበር እንደሚፈቀድ እና በማክበሩም ምንዳ እና አጅር እንዳለው የሚገልፅ ብያኔ
(ክፍል 10
)

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil

https://t.me/shamilunkamil
77 viewsedited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 21:10:31
መውሊድን ማክበር እንደሚፈቀድ እና በማክበሩም ምንዳ እና አጅር እንዳለው የሚገልፅ ብያኔ

(ክፍል 10
)

እንደዚህ አይባልም «መውሊድ መልካም ሱና ነው ይባላል እንጂ፤ መውሊድ መልካም ስራ ቢሆን ኖሮ ነቢያችን ﷺ ኡመቶቻቸውን ያመላክቱ ነበር አይባልም»።


ቁርኣንን በአንድ ሙስሐፍ መሰብሰብና ነጠብጣብ ሆነ ተሽኪል ማድረጉ መልካም ስራ ነው። ሆኖም ግን ነቢያችን ﷺ እንዲደረግ አልጠቀሱም ፣ እሳቸውም አላደረጉትም። እነዚያ መውሊድ መልካም ስራ ቢሆን ኖሮ የአሏህ መልክተኛ ﷺ ያመላክቱን ነበር በማለት መውሊድን ማክበር የሚከለክሉ እራሳቸው ነጠብጣብና ተሽኪል ያለበትን ቁርኣን የሚያነቡ ናቸው በመሆኑም ከሁለት ነገሮች ውስጥ አንዱ ላይ ይወድቃሉ።

አንደኛው አማራጭ «ቁርአንን ነጠብጣብና ተሽኪል ማድረግ የአሏህ መልክተኛ ስላላደረጉት አድርጉትም ብለው ኡመታቸውን ስላላመላከቱ መልካም ስራ አይደለም፤ ሆኖም ግን እኛ እናደርገዋለን» ሊሉ ይችላሉ።

አልያም የቀራቸው አማራጭ «ቁርኣንን ነጠብጣብና ተሽኪል ማድረግ የአሏህ መልክተኛ ባያደርጉትም፤ አድርጉትም ብለው ኡመቶቻቸውን ባያመለክቱም መልካም ስራ ነው ለዚህም ነው እኛ ምናደርገው» በማለት ሁለት አማራጭ ብቻ ይኖራቸዋል።

በሁለቱም አማራጮች ግን ከራሳቸው ጋር ይጋጫሉ። (ማለትም ንግግራቸው እንደ ማስረጃ አድርገው ካቀረቡት ጋር ይጋጫል።)

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil

https://t.me/shamilunkamil
465 views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 13:07:56
ልዩ ውድርድር! ወሀቢያዎች ሊመልሱት የማይችሉት ጥያቄ ነው፡፡መውሊድን ለመከልከል የሚያስቀምጧቸው ትክክል ያልሆኑ ጥያቄዎች አሉ፡፡አንዱ "መውሊድ አክብሩ የሚል አንቀጽ ወይም ሐዲስ ወይም የሶሐባ ንግግር ቃል በቃል አሳየኝ አራቱ መዝሀቦች ያሉትን አምጣ" የሚል ነው፡፡ እናንተ ጠማማ ወሀቢያዎች ሆይ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ቢጠይቃችሁ ወለም ዘለም ሣትሉ ምን ልትመልሱ ይሆን? #ቁርኣን ውስጥ #ቃል_በቃል "ተውሒድ…
129 views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 13:02:27 ልዩ ውድርድር! ወሀቢያዎች ሊመልሱት የማይችሉት ጥያቄ ነው፡፡መውሊድን ለመከልከል የሚያስቀምጧቸው ትክክል ያልሆኑ ጥያቄዎች አሉ፡፡አንዱ "መውሊድ አክብሩ የሚል አንቀጽ ወይም ሐዲስ ወይም የሶሐባ ንግግር ቃል በቃል አሳየኝ አራቱ መዝሀቦች ያሉትን አምጣ" የሚል ነው፡፡ እናንተ ጠማማ ወሀቢያዎች ሆይ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ቢጠይቃችሁ ወለም ዘለም ሣትሉ ምን ልትመልሱ ይሆን?

#ቁርኣን ውስጥ #ቃል_በቃል "ተውሒድ ለ 3 ይከፈላል"የሚል አለ ወይ?
#መልሱ_የለም!
1)
ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በየትኛው ሐዲስ ላይ ነው ቃል በቃል "ተውሒድ በ 3 ይከፈላል እነሱም ተውሒድ አል ኡሉሂያ፣አሩቡቢያ፣አልአስማእ ወሲፋት"ያሉት?ኩቱቡ ሲታ ውስጥ ካለ የሐዲስ ቁጥር መጥቀስ እንዳይረሳ?
#መልሱ_አንድም_ሐዲስ_የለም
2)#ሰዪና_አቡበክር ረዲየሏህ ዐንሁ
#ሰዪዱና_ዑመር_ኢብኑል_ኸጧብ ረዲየሏህ ዐንሁ
#ሰዪዱና_ዑስማን ረዲየሏሁ ዐንሁ
#ሰዪዱና_አሊይ_ኢብኑ_አቢጧሊብ ረዲየሏህ ዐንሁ በየትኛው ንግግራቸው ላይ ነው ቃል በቃል ያሉት?የዘጋቢውን ስም ከነሰነዱ ማስቀመጥ እንዳይረሳ?
#መልሱ_አላሉም
3)ሰዪደቱና ዓኢ
ሻ ረዲየሏሁ ዐንሀ በየትኛው ንግግሯ ላይ ነው #ቃል_በቃል ያሉት?ዘጋቢውን ከነሰነዱ ማስቀመጥ እንዳይረሳ?
#መልሱ_አላሉም
4)#አል_ኢማም_አቡሐኒፋ ረዲየሏህ ዐንሁ;
#አል_ኢማም_ማሊክ ረዲየሏህ ዐንሁ;
#አል_ኢማም_አሻፊዒይ ረዲየሏህ ዐንሁ;
#አል_ኢማም_አሕመድ_ኢብኑ_ሐንበል ረዲየሏህ ዐንሁ በየትኛው ንግግራቸው ላይ ነው ቃል በቃል ያሉት? የኪታባቸውን ስም ከነገጹ ማስቀመጥ እንዳይረሳ?
#መልሱ_አላሉም ነው።

በነገራችን ላይ አንድም መልስ ማምጣት አይችሉም፡፡ይህ #ኢብኑ_ተይሚያ እና #ሙሐመድ_ኢብኑ_ዐብዲል_ወሃብ(ላዕናቱሏሂ አል ሙተታሊያቱ ዐለይሂማ) ያመጡትን ተውሒድን ወደ ሶስት የመክፈል እና ተወሱል የሚያደርጉ ሙስሊሞችን የማስከፈሪያ መንገዳቸው መጥፎ ቢድዐ ሆኖ ሳለ ስለ መውሊድ ተነስተው ሊቀባጥሩ ይነሳሉ፡፡ለኛ ጊዜ ሲሆን ነብዩ ብለውታል?ሶሐባ ሰርተውታል?አራቱ መዝሀቦችስ? ይላሉ ለነሱ ሲሆን ግን እነዚህ ጥያቄዎች መነሳት የለባቸውም...ሃሃሃሃ ሲፈልጉ ቢድዐ ሲፈልጉ ሐላል ሲፈልጉ ሐራም እያሉ ጥቅማቸውን በማይጎዳ መልኩ ፍርዶችን ይሰጣሉ።ትላንት እኛን ሲወቅሱባቸው እና በሽርክ ሲፈርጁብን የነበሩ ነገራቶችን ዛሬ ላይ መሪዎቻቸው ሲሰሩት ይስተዋላል።ይህን ልብ ብሎ እንዚህ ሰዎች ልቦናቸውን ተከታይ ጠማሞች እንጂ ወደሐቅ መሪ አለመሆናቸውን የሚገነዘበው ግን ጥቂት ነው።ቡዙው በጭፍን ሳያስተነትን የሚከተል ነው።ስንት ቢድዐዎችን እየሰሩ መውሊድ ሲሆን ይንጨረጨራሉ።

ትንሽ እንጨምርላቸው ምን ይላሉ"መውሊድ ቢቻል ኖሮ ሶሐቦች ባደረጉት በተናገሩት ነበር አንተ ከእነሱ የበለጠ ስለ እስልምና አውቀህ ነው?እነሱ ያላሉትን ያልሰሩትን……መውሊድ የምትለው"

እስኪ ጥያቄውን እናዙረው እና መውሊድ ማክበራችን በእናንተ ቤት ስለ እስልምና ከሶሐቦች ከሰለፎች የበለጠ እኛ እናውቃለን ማለትን ያሲዛል የምትሉ ከሆነ(እውነታው ግን ጭራሽ አያሲዝም ነው።) እናንተ ተውሒድን ስትከፋፍሉ ከሶሐቦች ከሰለፎች የበለጠ ተውሒድን እናቃለን ማለታችሁ ነው ወይ?ብለን እንላቸዋለን።መልስ የላቸውም!

በእርግጥ የጥመታቸው ድርብርብ ሶሐባን እስከማስከፈር እንደደረሰ በኪታቦቻቸው ላይ ተቀምጧል።አሏህ ከጥመት ይጠብቀን!

ኧረ ረቢዑ ሊገባ ነው ሞቅ ሞቅ አድርጉት!

በ ኢብኑ ሀበሺይ

tg.me/shamilunkamil
690 viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 19:33:32 አሳዛኝ ዜና
የመውሊዱን ፕሮግራም መሰረዝን ስለማሳወቅ
•••••••••••••••••••••
ህገወጡ የአዲስ አበባ መጅሊስ የሚሊኒየሙን መውሊድ አስቁሙልን ብሎ ለአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ መሰረት፣ መስከረም 4/2015 ከንቲባ ፅህፈት ቤቱ በደብዳቤ የፈቀደውን የመውሊድ ፕሮግራም ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤቱ በቃል ደረጃ የጸጥታ ችግር ስላለ አቁሙ የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል። ነጃሺ እስላማዊ ማህበር እስከዚህ ሰአት ድረት በደብዳቤ የተፈቀደ ፕሮግራም በደብዳቤ ከልክላችሁ አሳውቁን ብሎ እየጠየቀ ያለበት ሁኔታ ላይ ቢሆንም ከሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።

በመሆኑም አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ በማየት እና ማህበረሰባችን ላይ ሊደርስ ከሚችለው ጉዳት አንፃር በጥልቀት በማየት እና በመወያየት የነገው የመስከረም 15/2015 የሚሊኒየም መውሊድ ፕሮግራም መሰረዙ ለማህበረሰባችን ደህንነት የተሻለ መሆኑን ስላመንን በአስገዳጅ ሁኔታ የነገውን የመውሊዱን ፕሮግራም መሰረዛችንን ለመግለፅ ተገደናል።

ስለሆነም በነገው እለት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ባለመሄድ ከፀጥታ አካላት ጋር በሚደረግ ግጭት በማህበረሰባችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ማስቆም ግዴታችን በመሆኑ የአሽረፈል ኸልቅ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ወዳጆች ነገ ጠዋት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ባለመሄድ እንድትተባበሩን በእጅጉ እንማፀናለን።

የተሰረዘው የመውሊድ ፕሮግራም የረቢእ አልአወል ወር ሳይወጣ በተለዋጭ ቀን ማድረግ የምንችልበትን መንገድ ሁሉ የምንሞክር ሲሆን ተለዋጭ ቀኑ ካልተሳካ ከማህበረሰባችን በቲኬት ሽያጭ የተሰበሰበው ገንዘብ ተመላሽ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን። ቀጣይ ሂደቶችን በትእግስትና፣ በዱዓ እና በተጠናከረ የትግል ወኔ ፀንታችሁ እንድትጠብቁን አጥብቀን እንጠይቃለን።

በረሱል ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፍቅር እና በዑለማኦቻችን መንገድ ሕያው ነን!

ሷሊህ አስታጥቄ

@shamilunkamil
636 viewsedited  16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 22:07:12የምስራች፥

አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ አህባቢ ቶታል በሚገኘው የሸይኽ ዐብዲላህ መርከዝ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከ8–10 ሰኣት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ደውራ ተዘጋጅቷል ሁላችሁም በመምጣት እንድትሳተፉ እጠይቃለው።

አዘጋጅ፦ኡስታዝ ሐምዛ
የሚቆይበተ ግዜ ፦አምስት ቀን
ሰኣት፦8–10
ፆታ፦አይለይም
እርዕስ፦ስለ ሙስሊሞች ዐቂዳህ


ሼር አድርጉት

ለበለጠ መረጃ፦

@nadiyanaduu
@nadiyanaduu



https://t.me/asedullahh
201 views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 08:09:35 ማለትም እኛ ሙስሊሞች የሀዘን ቀን አውጀን ማክበርን እስልምና አላስተማረንም በተቃራኒው አሏህ ለዋለልን ፀጋ ግን ደስታችንን መግለፃችንና በተለያዩ ዒባዳዎች ምስጋናን ማድረስ በሸሪዐው የመጣ ነው።
አቤት አገላለጽ!አል ሓፊዙ አስሲዩጢይን አሏህ ይዘንላቸውና ባጭር ገለፃ ግልጥልጥ አረጉልን፡፡
እና የመውሊድ ናፋቂዎች...መውሊድን ስናከብር የውልደታቸውን እንጅ የሞቱበትን እንዳልሆነ ለታች ሰፈሮች አስረዱልኝ!

#መስከረም 15 በሚሊኒየም አዳራሽ ሚሊዮኖች ሆነን እናከብረዋለን!

በኢብኑ ሀበሺይ
197 views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 08:07:02
ወሀቢያዎች መውሊድን በተለያዪ መንገዶች ለመቃረን ጥረዋል ከአመት አመት የተለያዪ እዚህ ግባ የማይባሉ ጥያቄዎችን በማሰራጨት እውቀት የሌለውን ከመውሊድ ከማራቅም ሞክረዋል።

በርግጥ ጥያቄዎቻቸውን ካየን ካለፉት መሪዎቻቸው የያዟቸውና ለነሱም የኢስላም ልሒቃኖች በማያዳግም ሁኔታ መልስ ሰጥተውባቸው ያለፉባቸው ሆነው እናገኛቸዋልን።ከነዚህ ጥያቄዎቻቸው መካከል የሞቱበትን ነው ምታከብሩት ብለው ግግም የሚሉበት ይገኛል።

አጂብ ነው ሰይዳችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በረቢዕ አል አወል በ12ኛው ቀን በመወለዳቸው ደስታችንን ለመግለፅና ቀኑን አስበን ለአሏህ ምስጋናን እያቀረብን የምናሳልፈውን አይ የሞቱበትን ነው ብለው ሲሞግቱ ማግኘት ይደንቃልም ያስገርማልም።እስኪ ከታላላቅ የኢስላም ምሁራን አንዱ የሆኑት የፊቅህ የተፍሲር የቋንቋ የሐዲስ እና የሌሎች ብዙ ፈኖች ምጡቅ እውቀት ባልተቤት የሆኑት አልሓፊዙ አሲዩጢይ ወሀቢያዎች ዛሬ ላይ ለሚያነሱት ጥያቄ ከዛሬ 500 አመት በፊት ገደማ የሰጡትን መልስ እንመልከት……

አል ሓፊዙ አሲውጢይ ሑስኑል መቅሲድ ፊ ዐመሊል መውሊድ የሚል ስያሜን የያዘ ኪታባቸው ላይ በመውሊድ ዙሪያ ተጠይቀው የመለሷቸውን መልሶች ሲጠቅሱ የሞቱበትን ነው ወይስ የተወለዱበትን የምታከብሩት የሚለው ጥያቄ መነሳቱን ጠቅሰው እንዲህ ሲሉ ይናገራሉ:
#"የነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም መወለድ ለኛ እጅጉን ታላቅ ፀጋ ነው የእርሳቸው ሞት ደግሞ በኛ ላይ እጅጉን ከባድ ሙሲባ ነው ሸሪዐ ደግሞ ለጸጋዎችና ለረሕመቶች አሏህን እንድናመሰግንና እንድንደሰት ያነሳሳን ሲሆን ሐዘንና ሙሲባ ባጋጠመን ሰዐት ግን ሶብር ማድረግና ቻል ማድረግን አስተምሮናል!"
187 views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 10:25:53 ጤንነት ሲጣላህ ሲያሳስርህ በሽታው
የሚያሽርህ ጌታህ መሆኑን ሳትስተው
« ሃኪም ቤት አድርሱኝ፤ መድሃኒት አቅምሱኝ»
የሚባል ቅኔህን እስኪ አንተው ፍታው

አሏህ ነው የሚያድን ስትል እንዳልነበር
  በመሸም በነጋ
ምነው ታየህሳ ክኒን ስትወስድ መርፌም ስትወጋ
 
እውነተኛው ፈዋሽ አሏህ ነው አምናለሁ  
ግንስ ሰበብ ላደርስ ክኒን እወስዳለሁ
ሲል ሰጠኝ ምላሹን

ታዲያ እኔን ሲያመኝ በሽታ ሲያፍነኝ
ከልቤ እያመንኩኝ እርሱ እንደሚያድነኝ
  የመሻሬ ሰበብ እንዲሆኑኝ ብዬ
  በክኒኑ ፈንታ ነቢዬን መጥራቴ
  አሽሮኝ ተገኝቷል ሆኖኝ መድኀኒቴ
 
በኡስታዝ ሰዒድ አህመድ

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil
https://t.me/shamilunkamil
791 views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ