ዐርብ በአስራ አንድ ሰዓት ክፍል አስራ ስድስት አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ንዜኑ (፫) ዘአምላክነ ኂሩተ ትሕትና ወየውሃተ ዘእንበለ ዐቅም ዬ ዬ ዬ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐሎሙ እንዘ ያሐምምዎ ኢተቀየሙ። በዚህ ሰዓት "ለከ ሃይል ፣ ኪርያላይሶንና መልክዐ ሕማማት" የለም። የሰዓቱን ምንባባትም በቅዳሜ ሌሊት ማንበብ ይቻላል። ሥርዓተ እግዚኦታ ካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ሥርዓተ ግንዘትን ይስሩ : ሦስት ካህናትም ሥርዓተ ግንዘቱን በእጃቸው አቅፈው ይያዙት : አንድ ካህን መስቀልና ጽንሐሕ ይዞ በኋላቸው ይከተል : አንድ ዲያቆን ደግሞ መስቀልና መብራት በመያዝ ፊት ለፊት ይምራ : በምዕራብ በኩል ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ይቁሙ : ከዚህ በኋላ በአራቱም ማዕዘናት እየዞሩ እግዚኦታ ያድርሱ አደራረሱም ካህናቱና ሕዝቡ በግራና በቀኝ በአራቱም አቅጣጫ በአራት ተመድበው በመቆም:- በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ : በንዑስ ዜማ ባለአምስቱን ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ : እንደገና በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ : በንዑስ ዜማ በእንተ ማርያም ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ። ምሕላው ከተፈጸመ በኋላ ካህኑ "አቡነ ዘበሰማያት" ይስጥ : እስከ ትንሣኤ ድረስ የኑዛዜ ጸሎት ስለሌለ ካህኑ ፵፩ ጊዜ ኪርያላይሶን ይበል : ሕዝቡም እንደርሱ ይበሉ። #ከዚህ_በኋላ_በቅኔ_ማኅሌት_ሁሉም_ይሰብሰቡ_መቋሚያ_ይዘው_በመካከላቸው_ጧፍ_አብርተው_ይያዙ_የዳዊትንና_የነቢያትን_ጸሎት_እየተቀባበሉ_ያንብቡ_አንብበው_ሲጨርሱ_በመካከላቸው_ያለውን_መብራት_በያዙት_መቋሚያ_ያጥፉት_የዲያቢሎስ_ገዢነት_መደምሰስ_ምሳሌ_ነው_ከዚያም_መዘምራን_ንሴብሖን_ይዘምሩ_ካህናትም_ሕዝቡን_በወይራ_ቅጠል_እየጠበጠቡ_እና_ስግደት_እያዘዙ_ወደ_ቤታቸው_ይሸኟቸው። አዘጋጅ #ዲያቆን ፍቅረ አብ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!! https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw #subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ @seratebtkrstian @seratebtkrstian @seratebtkrstian join 728 viewsⒻⓔⓚⓡⓔ 🇦 🇧 🇪, 08:07