Get Mystery Box with random crypto!

የሆሣዕና ዑደቱና ሥርዓቱ ቀዳሚው የሌሊት ጸሎትና ምንባብ እንደተፈጸመ ይኸውም ከቅዳሴ በፊት በ | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

የሆሣዕና ዑደቱና ሥርዓቱ

ቀዳሚው የሌሊት ጸሎትና ምንባብ እንደተፈጸመ ይኸውም ከቅዳሴ በፊት በማዕረግ የሚበልጥ ካህን ወይም አበምኔት አቡነ ዘበሰማያት በማስከተል የኑዛዜ ጸሎት ያድርግ፡፡ የተዘጋጀውንም ዘንባባ ይባርክ ከባረከ በኋላም ለካህናት ያበርክት ራሱም ከመጀመሪያው ካህን ይቀበል ካህናቱም የዘንባባውን ቅጠል በመየዝ መጀመሪያ ለዲያቆናት ለመዘምራን እና ለሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን እየሰጡ በአራቱም ማዕዘናት ይዙሩ በየአቅጣጫውም የሚገባውን ጸሎት ያድርሱ። የጸሎቱንም ሥርዓት በቤተ መቅደስ ይጀምሩ፡፡ ካህኑም የዘንባባውን ቅጠል እንዲህ እያለ ይስጥ ይ.ካ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ በፍሥሐ ወበሰላም። ይ.ሕ አሜን እያሉ ይቀበሉ።

አዘጋጅ ዲያቆን ፍቅረ አብ

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube ቻናል ተከታታዮች የተዘጋጀ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   


     join